ፈልግ

ማርታ ማርታ ብዙ ትተጊያለሽ፣ ትጨነቂያለሽ፣ ትዘጋጂያለሽ፣ የሚበቃሽ ግን ነገር ጥቂት ነው! ማርታ ማርታ ብዙ ትተጊያለሽ፣ ትጨነቂያለሽ፣ ትዘጋጂያለሽ፣ የሚበቃሽ ግን ነገር ጥቂት ነው! 

ማርታ ማርታ ብዙ ትተጊያለሽ፣ ትጨነቂያለሽ፣ ትዘጋጂያለሽ፣ የሚበቃሽ ግን ነገር ጥቂት ነው!

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ማርታ ቤት በገባ ጊዜ ማርታ በደስታ ተቀበለችው፣ በሚገባ ምሳ ልታቀርብለት ወዲያ ወዲህ ትራወጥ ነበር። ለሥጋዊ ግዴታ ስትል የመንፈስ ግዴታዎችን ረሳች ችላ አለች፤ ማርያም እህቷ ግን የእየሱስን ፈቃድ አውቃና ተረድታ በአጠገቡ ቁጭ ብላ ቃሉን ትሰማ ነበር። ይህም ማርታን አስገርሟት ኢየሱስን “ጌታ ሆይ እህቴ ብቻዬን ስትተወኝ አላሳዝንህምን፣ እባክህ እንድታግዘኝ ንገራት´ ስትል ተናገረችው። ስለ እርሱ ታደርገው በነበረ የምግብ ዝግጅት የተደሰተ ቢሆንም ከእርሷ ይልቅ የማርያም ሥራ እንደሚበልጥ አስታወቃት። የእርሷ ዝግጅት የሚናቅ ባይሆንም የማርያም ሥራ ግን እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ገለጠላት።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

“ማርታ ሆይ ብዙ ትሠሪያለሽ፣ ትጨነቂያለሽ ለአላፊ ምግብ ዝግጅት ከባድ ጥረት ታደርጊያለሽ፤ ማርያምን ግን የበለጠውን ነገር መርጣለች፤ ከእርስዋ ዘንድ አይወሰድባትም” (ሉቃ 10፣ 38-42) አላት። ሁለቱ እህትማማች ኢየሱስን ስለሚወዱት በየበኩላቸው ሊያስደስትቱት ጥረት ያደርጉ ነበር። ማርያም እንደ ሐሳቡ ልታስደስተው ማርታ ደግሞ እንደ ሐሳቧና እንደ ስሜቷ ልታስደስተው ትፈልግ ነበር። “በመጠጥ በምግብ´ ልታስደስተው በጣም ጥረት ታደርግ ነበር። የኢየሱስን የዘለዓለማዊ ሕይወት ሐሳብና ፈቃዱን አልተረዳችም ነበር።

እኛም ብዙ ጊዜ በማርታ ዓይነት ስህተት እንወድቃለን፤ እግዚብሔርን ደስ በሚያሰኘን አግባብ ልናገለግለው እንፈልጋን። ለዚሀ ዓላማ በቁርጠኝነት ተነሣሥተን እንደክማለን። “እግዚአብሔር የሚወደውን ሥራ የትኛው ነው፣ በምን ዓይነት እንድናገለግለው ይፈልጋል፣ ብለን አስቀድመን በጸሎት ከጠየቅና ከእርሱ መልስ ጠብቀን ከመሥራት ይልቀ ዓይናችንን ጨፍነን ጆሮአችንን ደፍነን በስሜታችን እንመራለን። በመንፈሳዊ መንገድ ከምናከብረው ይልቅ በሥጋዊ መንገድና ስሜት ልናገለግለውና ልናከብረው እንወዳለን። ይህ አሠራር በተለይ በዐቢይ በዓላት ብዙ ጊዜ ይገጥመናል። በዓላት ከእግዚብሐር፣ ከማርያም፣ ከመላእክት፣ ከቅዱሳን ጋር በመንፈስ የምንገኝባቸው የምናመሰግንባቸው ቀናት ናቸው። ለእነርሱ ክብር ለእኛ ደግሞ በንፈስ ጠቃሚ ሊሆኑ የሚገቡ ቀናት ናቸው። መንፈሳዊ ግዴታችንን ካልተወጣን የመንፈሳዊ በዓል ሳይሆን ሥጋ የሚደሰትበትና ነፍስ የምታዝንበት በዓል ነው።

በዚህም ምክንያት መንፈሳዊውን በዓል በሥጋ በዓል እናደርገዋለን፤ መንፈሳዊ ተግባራትን ትተን በሥጋዊ ጉዳዮች እንጠመዳለነ። በዐበይት በዓላት ልናከብረውና ልናመሰግነው የሚገባንን እግዚአብሔርን እንረሳለን። መብልና መጠጥ ለማዘጋጀት ሥጋችንን ለማስደስት ስንል ከቤተክርስቲያን፣ ከጸሎት፣ ከቅዳሴ እና ከምስጢራት እንርቃለን። “በቤት ሥራ አለብኝ፣ አንድ ትልቅ እንግዳ ይመጣብኛል´ በማለት ጸሎታችንን ችላ እንላለን” መንፈሰዊ ጉዳያችንን በመተው ነፍሳችንን እንረሳለን። በበዓላት ብቻ ሳይሆን በሌላ ጊዜም ምግባራችን ማርታን እንመስላለን። ዋናውን መንፈሳዊ ጉዳይ ጸሎትና የእግዚአብሔርን መንግሥት ሐሳብ ትተን መጥፎ ተግባር ስናከናውን እንገኛለን።

“ልንሰብክ ትምህርተ ክርስቲያን ለልጆች ልናስተምር መንፈሳዊ ትዕይንት ሲኒማ ቲያትር ልንመለከት በሽተኞችን ልንጐበኝ ችግረኞችን ልንረዳ የተጣሉ ልናስታርቅ በድንገተኛ አደጋ ችግር ላይ የወደቁተን ነፍሳት ልንረዳ የተጣሉ ልናስታርቅ በድንገተኛ አደጋ ችግር ላይ የወደቁትን ነፍሳት ልንረዳ´ እያልን በማሳሰብ ጸሎትን እናስተጓጉላለን፡፡ ይህ ተግባር እኮ እራሱ ጸሎት ነው እያልን እንመጻደቃን፡፡ ኢየሱሱ እኛንም እንደ ማርታ ነው የሚለን፡፡ “ይህ ሥራ አዎ የሚወደድ ጥሩ ሥራ ነው ነገር ግን እኔ ከሁሉ የምፈልገው በይበልጥ የሚያስደስተኝ ጸሎት ነው፡፡ የመጀመሪያ የግድ ሌላው ይህንን ተከትሎ የሚመጣና የሚሆን ማሟያ ነው፣ «ከሁሉ አስቀድሞ በጸሎት ትጉ´ ይለናል፡፡ ለሕይወታችን በጣም አስፈላጊ የሆነውን ጸሎት ካጓደልን ምግብ እንዳጣ ሰውነት ነፍሳችን በረሃብና በመንፈሳዊ ጥም ትሞታለች፡፡ እንግድህ የበለጠ ጊዜያችንን በጸሎት እናሳልፈው፣ ሌላ ሥራ የቀረው ጊዜ ይበቃዋል፡፡ ኢየሱስ ራሱ ስብከቱን ከጀመሩ በፊት ጠዋት በጸሎት ጊዜ ያልፍ ነበር። እንደዚሁም ሥራውን ፈጽሞ ሲጨርስ የሚበልጠውን ጊዜ በጸሎት ያሳልፍ ነበር” (ማር. 6፣ 31-32) ፡፡

“ማርያም ማንም ሊነጥቃት የማይችለውን የበለጠ መልካሙን ነገር መረጠች” በሕይወታችን በሚገባ እግዚአብሔርን ልናገለግለው ከፈለግን እንደ ማርያም ሥጋዊውን ሥራ ችላ ብለን መንፈሳዊውን ሥራ እንድንወድ ወደ ጸሎት እንድናዘነብል ያስፈልጋል።

የጸሎታችንን ጉዳይ ሳናገባድድ ወደ ሌላ መልካ ሥራ አንሻገር። ጸሎታችን ችላ ብለን በዚህ ዓይነት ሥራ ብቻ መቆርቆር እግዚአብሔርን አያስደስተውም። ጸሎትን በመተካት የሚሠራ ሥራ ፍሬ አይገኝበትም። ሁል ጊዜ በእግዚአብሔር ፈቃድ እንድንመራ ስሜታችን የሚወደውን ሁሉ ትተን እግዚአብሔርን የሚያስደስት ሥራ እርሱ በሚወደው አኳኋን እንፈጽም።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከእዚህ በታች ያለውን የማጫወቻ ቁልፍ ይጫኑ!
09 June 2021, 11:26