ፈልግ

የአውሮፓ ፓርላማ የአውሮፓ ፓርላማ  

የአውሮፓ ብጹዓን ጳጳሳት የአውሮፓ ፓርላማ ያጸደቀው ውሳኔ ያሳሰባቸው መሆኑን ገለጹ

የአውሮፓ አገሮች ብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የአውሮፓ ፓርላማ በጤና እና ስነ ተዋልዶን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ባጸደቀው ሕግ ላይ አስተያየታችውን ገልጸዋል። የብጹዓን ጳጳሳት የምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ክቡር አቶ ባሪዮስ ፕሬቶ፣ ፓርላማዉ ያሳለፈው ውሳኔ ሕሊናን የሚቃረን አሳሳቢ እና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አስረድተው፣ ገና ያልተወለዱ ልጆችም ቢሆኑ በሕይወት የመኖር መሠረታዊ መብት አላቸው ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ክርስቲያናዊ መሠረት ያለው፣ ከሁሉ በፊት ለሰብዓዊ ክብር እውቅናን የሰጠ፣ የሰውን ልጅ ሕይወት ከአደጋ ለመከላከል የቆመ አውሮፓ ጽንስን ማስወረድ እንዴት እንደ መብት የመለከተዋል በማለት የአውሮፓ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ክቡር አቶ ባሪዮስ ፕሬቶ ጥያቄአቸውን አቅርበዋል። የአውሮፓ ፓርላማ ያቀረበው ሪፖርት የኅብረቱ አባል አገራት ጳጳሳትን ያሳሰባቸው መሆኑን ክቡር አቶ ባሪዮስ ፕሬቶ ገልጸው፣ ፓርላማው ጤናን፣ ስነ-ተዋልዶን እና ጾታን አስመልክቶ ያቀረበው “የማቲክ ሪፖርት” የሴቶችን ጤና ሁኔታ ያላገናዘበ ነው በማለት አስረድተዋል።    

የ “ማቲክ ሪፖርት”

አባል አገራትን ያማያስገድድ የጽሑፍ ሰነዱ ያቀረበው ሪፖርት፣ ጽንስን ማስወረድ መሠረታዊ የሰውን ልጅ መብት የሚቃረን እና የአንዳንድ የአውሮፓ አባል አገራት ሕግንም የሚጻረር መሆኑ ታውቋል። በአውሮፓ ፓርላማ ውስጥ 378 የድምጽ ድጋፍ፣ 255 ድምጸ-ተቃውሞን እና 42 ድምጸ-ተዓቅቦን በማግኘት የጸደቀው የፓርላማው ውሳኔ ሁሉም የአውሮፓ ኅብረት አገራት ለጽንስ ማስወረድ መብት እና የሰቶችን መብት የሚያጠብቅ እውቅና ብቻ ሳይሆን ማረጋገጫንም የጠየቀ መሆኑ ታውቋል።

“ከባድ ስህተት”

በውሳኔው የአውሮፓ ፓርላማ ሃላፊነትን እንዲወስድ ጠይቀናል ያሉት ክቡር አቶ ባሪዮስ ፕሬቶ፣ ውሳኔውን እንደገና መመልከቱ ጾታዊ ጤናን እና ስነ ተዋልዶን ብቻ የሚመለከት ሳይሆን፣ የጤና መብት ሁላችንም እንዲከበር የምንፈልገው መሠረታዊ መብት ነው ብለው፣ በተለይም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ሊከበር እንደሚገባ፣ በተለይም ለሴቶች ማግኘት ያለባቸው የጤና መብት የበለጠ ሊከበርላቸው ያስፈልጋል ብለዋል። ቤተክርስቲያን የሰዎች የጤና መብት እንዲከበር በማለት ድምጽ የምታሰማው በዚህ መክንያት ነው ብለው፣ በዚህ የጤና መብት መካከል ጽንጽን ማስወረድ እንደ መሠረታዊ መብት መጠቀሱን ቤተክርስቲያን የማትቀበለው መሆኗን የብጹዓን ጳጳሳቱ የምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ክቡር አቶ ባሪዮስ ፕሬቶ አስረድተዋል።

ጽንስን ማስወረድ የሚደግፍ ሕግ የለም

በአለም አቀፍ ሕግ ውስጥ ጽንስን የማስወረድ መብት የሚያስጠብቅ ሕግ አለመኖሩን የገለጹት ክቡር አቶ ባሪዮስ ፕሬቶ፣ በፓርላማው በጸደቀው ውሳኔው ውስጥ ጽንስን የማስወረድ መብትን ሕጋዊ የሚያደርግ ስምምነት መኖሩን ገልጸዋል።

የህሊና ነፃነት ሁል ጊዜ ሊከበር ይገባል

በአውሮፓ ፓርላማ ውሣኔ ውስጥ በአንዳንድ አባል አገራት መካከል የሚደረገው የተለመደ ተግባር የህክምና ባለሙያዎችን እና አንዳንዴም አጠቃላይ የህክምና ተቋማት የህሊና ተቃውሞ እየተባለ በሚጠራው አካሄድ መሰረት የህክምና ተቋማቱ የጤና አገልግሎቶችን እንዲያቀርቡ የሚያስችላቸው ቢሆንም ይህ የሴቶችን  ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥል እና መብታቸውንም የሚጻረር መሆኑን ክቡር አቶ ባሪዮስ ፕሬቶ ገልጸው፣ የህሊና ተቃውሞ የአንድ ጤና ባለሞያ መብት ብቻ የሚያካትት ሳይሆን ነገር ግን የራሱ ተልእኮ እና ጥሪ ያለው፣ ከመሠረታዊ መርሆዎቹ የተለየ እንዳይሆን የሚጥረውን ተቋም መብት ያካተተ መሆን አለበት ብለዋል።

የአስተሳስብ ለውጥ መፈጥሩ ያሳስባል

የሚያሳስበው በአውሮፓ ፓርላማ ቀርቦ አዎናትዊ ወይም አሉታዊ ድምጽ የተሰጠበት ሪፖርት ሳይሆን፣ በማኅበረሰብ ሕይወት ውስጥ የተፈጠረው የአስተሳሰብ ለውጥ መሆኑን ክቡር አቶ ባሪዮስ ፕሬቶ ገልጸው፣ የአውሮፓ ፓርላማ ያጸደቀው ደንብ የአውሮፓ አገራት ካቶሊካዊ ብጹዓን ፓጳሳትን የሚያሳስብ፣ ገና ያልተወለዱ ልጆች እንደ ማንም ሌላው ሰው በሕይወት የመኖር መሠረታዊ መብታቸውን የሚጻረር መሆኑን የአውሮፓ አገሮች ብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ክቡር አቶ ባሪዮስ ፕሬቶ ገልጸዋል። 

26 June 2021, 16:39