ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው የሉርድ ማርያም ምስል ፊት ለፊት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው የሉርድ ማርያም ምስል ፊት ለፊት  

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ኤልሳቤጥን ጎበኘቻት

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቅቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የላቲን ስረዓተ አምልኮ በሚከተሉ ምዕመናን ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያክስቷ ልጅ የሆነችውን ቅድስት ኤልስቤጥን የጎበኘችበት ቀን እና የማርያም ወር በመባል የሚታወቀው የግንቦት በሚጠናቀቅበት በዛሬው ቀን የሰላም እናት የሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለዓለማችን፣ ለአገራችን፣ ልቤተሰቦቻችን እና እንድሁም ለራሳችን ጭምር ሰላም እና ጤና ከልጇ ዘንድ ታስገኝልን ዘንድ በማሰብ የመቁጠሪያ ጸሎት በመድገም ይህ ልዩ የማርያም ወር ዛሬ ይጠናቀቃል (ጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቅቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በሚከተሉ ምዕመናን ዘንድ ማለት ነው)።

የዚህ ዝግጅት አዘጋጅ እና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በሉቃስ ወንጌል በምዕራፍ 1፡39-56 ላይ እንደ ተጠቀሰው “ማርያምም በዚያው ሰሞን በፍጥነት ተነሥታ ወደ ደጋው አገር፣ ወደ አንድ የይሁዳ ከተማ ሄደች፤ ወደ ዘካርያስ ቤትም ገብታ ለኤልሳቤጥ ሰላምታ አቀረበች። ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ፣ ፅንሱ በማሕፀኗ ውስጥ ዘለለ፤ ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተሞላች፤ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች፤ ‘አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፤ የማሕፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። ለመሆኑ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እኔ ማን ነኝ? እነሆ፤ የሰላምታሽ ድምፅ ጆሮዬ እንደ ገባ፣ በማሕፀኔ ያለው ፅንስ በደስታ ዘሎአልና። ጌታ ይፈጸማል ብሎ የነገራትን ያመነች እርሷ የተባረከች ናት!”በማለት ኤልሳቤጥ ማርያምን በታላቅ ደስታ በቤቷ የተቀበልችበት ቀን የሚታሰብበት አመታዊ በዓል ነው።

እነዚህ ሁለት ሴቶች ማለትም ማርያም እና ኤልሳቤጥ በዝምድና የተሳሰሩ ቢሆኑም ነገር ግን በእድሜ፣ በባሕሪይ፣ በከባቢያዊ ሁኔታ የተለያየ ዓይነት ሕይወት የነበራቸው ሰዎች ነበሩ። እነዚህ ሁለት ሴቶች ማርያም እና ኤልሳቤጥ የየራሳቸው የሆነ የግል ምስጢር ደብቀው የያዙ ሴቶች ነበሩ። የማርያምን ጉዳይ በምንመልከትበት ወቅት ማርያም የዩሴፍ እጮኛ የነበረች ሴት እንደ ነበረች የሚታወቅ ሲሆን ነገር ግን መልኣኩ ገብሬል ከእግዚኣብሔር ተልእኮ የምስራቹን ቃል ካበሰራት በኃላ በሰው ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አርግዛ በመገኘቷ ይህ ሁኔታ ደግሞ በወቅቱ በነበረው የማኅበርሰብ ክፍል አንድ ከትዳር ውጭ ያረገዘች ሴት በድናግይ ተወግራ ትገደል የሚል ሕግ በመኖሩ የተነስ ተጨንቃ ነበር፣ እግዚኣብሔር በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በእርሷ ማደሩን በወቅቱ እርሷ ለሌሎች ማስረዳት የከበዳት ጉዳይ ነበር፣ በእዚህም ምክንያት ሁሉንም ነገር በልቧ እያሰላሰልች ይዛው ቆይታ ነበር።

ኤልሳቤጥም በበኩሉዋ አንድ ቀን ዘካርያስ በምድቡ ተራ፣ በእግዚአብሔር ፊት በክህነት በሚያገለግልበት ጊዜ፣ ዕጣን በሚታጠንበትም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ሆኖ ይጸልይ ነበር። የጌታም መልአክ ከዕጣን መሠዊያው በስተ ቀኝ ቆሞ ታየው። ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፤ በፍርሀትም ተዋጠ። መልአኩ ግን እንዲህ አለው፤ “ዘካርያስ ሆይ፤ አትፍራ፤ ጸሎትህ ተሰምቶአል፤ ሚስትህ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ። ዘካርያስም መልአኩን፣ “ይህን በምን አውቃለሁ? እኔ ሽማግሌ ነኝ፤ ሚስቴም በዕድሜ ገፍታለች” አለው። መልአኩም መልሶ እንዲህ አለው፤ “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ በማለት ምስቱ ኤልሳቤጥ በእስተ እርጅና ወንድ ልጅ እንደ ምትወልድ ባበሰረው መሰረቱ ሚስቱ ኤልሳቤጥ ታረግዛለች። ነገር ግን ኤልሳቤጥ በእድሜ በመግፋቷ የተነሳ ይህ እርግዝና ከፍተኛ የሆነ ምስጢር ሆኖባት ነበር።

ስለእዚህ እነዚህ ሁለት ሴቶች የሚያመሳስላቸው ነገር ቢኖር በውስጣቸው ደብቀው የያዙት አንድ ምስጢር መኖሩ፣ ሁለቱም አንድ ወንድ ልጅ እንደ ሚወልዱ እና ሁለቱንም ያበሰረው ደግሞ መልኣኩ ገብሬል መሆኑ ያመሳስላቸዋል።

በእዚህ አጋጣሚ ይህንን ማርያም ኤልሳቤጥን የጎበኘችበት ቀን በምንዘክርበት በዛሬው ቀን  ልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ፣ ፅንሱ በማሕፀኗ ውስጥ ዘለለ፤ ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተሞላች፤ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች፤ “አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፤ የማሕፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው፣ በማለት ገና በማሕጸኗ ውስጥ ያለውን ሕጻኑን ኢየሱስን እንዳመስገነች ሁሉ፣ እኛም ማርያም ልባችንን፣ ቤተሰባችንን፣ ሀገራችንን ኣና እንዲሁም ዓለማችንን እንድትጎበኝ እና በደስታ እና በሰላም፣ በመንፈስ የተሞላን ሆነን እንኖር ዘንድ እንድተረዳን በሕይወታችን ውስጥ ልንጋብዛት ያስፈልጋል ለማለት እንወዳለን።

31 May 2021, 14:29