ፈልግ

ኢየሱስ ሽባውን ሰው ፈወሰው ኢየሱስ ሽባውን ሰው ፈወሰው  

ክፉ ልምድ

ከአንድ መንደር የመጡ ሰዎች ወደ ኢየሱስ በአልጋ ተሸክመው አንድ ሽባ ሰው አመጡ፡፡ ኢየሱስም እምነታቸውን ተመልክቶ ሽባውን ሰውዬ «አይዞህ ኃጢአትህ ተደምስሶልሃል ተነስና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ´ አለው፡፡ እርሱም ሰዎች እየተደነቁ ብድግ ብሎ አልጋውን ተሸክሞ ወደ ቤቱ ሄደ (ማቴ. 9፣1)፡፡ የመጥፎ ልምድ ባርያዎች ከሆንን ይህን ሽባ እንመልሳለን፡፡ ይህ በበሽታው ምክንያት መንቀሳቀስ አቅቶት ሌት ተቀን የአልጋ ቁራኛ ሆኖ ያሳለፈው ኑሮ መጥፎ ነበር።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን 

አንድ ጊዜ በመጥፎ ልምድ አመል ከወደቅን ተብትቦ አስሮ ይይዘናል፡፡ ከዚህ ከኃይለኛ ማሰሪያ ሳንላቀቅ እንዲሁ ለሁል ጊዜ ታስረን እንቀራለን፡፡ አመልን በመጀመሪያ መተው ቀላል ሲሆን ሥር ከሰደደ ከበረታብን ትልቅ አደጋ ስለሚያስከትልብን ብርቱ ፈቃድ ያስፈልገዋል፡፡ መጥፎ ልምድ የመንፈስ አደገኛና ድንገተኛ በሽታ ነው፡፡ ሽባው በዚህ ከፉ በሽታ ሳይለከፍ በጤናው ጊዜ ራሱን ችሎ አውጡኝ አውርዱኝ ሳይል ተደስቶ ይኖር ነበር፡፡ መጥፎ በሽታ ከለከፈው በኋላ ግን በሰው ተደግፎ እንዲኖር ግድ ሆነበት፡፡

በመጥፎ ልማድ ከመውደታችን በፊት በንፈስ ብርቱዎች ነበርን፡፡ ምክንያቱም ከእግዚአብሔር የሚመጣ ኃይልና ጸጋ አለንና፡፡ በዚህ ተደግፈን ደግሞ ከኃጢአት እንድንርቅና ወደ መልካ ነገር ልናዳላ እንችላለን፡፡ ክፉ አመል በላያችን ከነገሠና ሥር ከሰደደ ግን መንፈሳዊ ኃይል ስለሚጐድለን በሁሉ ሰነፎች ሆነን እንገኛለን፣ ቀላል ፈተና ይጥለናለ፡፡ በመሆኑም አነስኛ ፈተና ሲቀሰቀስብን ፈጥነን እንሸነፋለን፡፡ በጠላቶቻችን እጅ ወድቀን እንማረካለን፡፡ ደጋግመን በኃጢአት ከባድ ባርነተ በመውደቃችን ለመናዘዝ እንሄዳለን፡፡ በኑዛዜም ብዙ አንጸናም፡፡ ተመልሰን እንዳንወድቅ ቁርጥ ፈቃድ ብናደርግም መንፈሳዊ ኃይላችን ስለደከመ እንደገና ወደ መጥፎ አመላችን እንመለሳለን፡፡ መጥፎ ልምድ እያደረ ያዳክመናል፡፡ የዛሬ የነገም ሕይወታችን ኃጢአት ብቻ ይሆናል፡፡ በዚህ አኳያ ክፉ ልማዳችን እየቀጠለ ይሄዳል፡፡

ክፉና አጸያፊ የመንፈስ ሕመም ፈቃዳችንን ያዳክማል፡፡ አእምሮአችግን ያደነዝዛል፣ ጉልበታችንን ያሽመደምዳል፡፡ መጥፎ አመል በባርነት ሰንሰለት አሥሮ ከጐተተን የግድ በመንፈስ እንቀዘቅዛለን፡፡ ያን ጊዜ ያለ ፍራቻና ይሉኝታ ኃጢአት በኃጢአት ላይ እየጨመርን እናከማቻለን፡፡ በዚህ ሁኔታ መንፈሳዊ ሕይወታችን እየከፋ ይሄዳል፡፡ በዚህ ዓይነት ስንት መንፈሳዊ ጉደት ይደርስብናል; ከእግዚአብሔር እንርቃን፣ ወደ ጥፋት እንመራለን፣ መጥፎ ልማድ በኃይለኛ መርዙ ሕይወታችንን ብቻ ሳይሆን በመጨረሻ ሞታችንንም ያበላሽብናል፡፡

በሕይወት ስንኖር ብቻ ሳይሆን ስንሞትም ልማዳችንን ለመተው ያለ መጠን ያስቸግረናል፡፡ ብዙዎች በሕይወታቸው ዘመን ማሸነፍ ያቃታቸው ክፉ ልማድ በሞታቸው ጊዜም ማሸነፍ አቅቶአቸው ይዞአቸው ጠፋ፡፡ በፍጹም ጉዳት ተደናግጠን በእርሱ እንዳንወቅ እንፍራ፣ አስቀድመን ከእርሱ አንሽሽ፣ በቸልተኝነት ጊዜ ብንሰጠው ብርቱ ሥር ተክሎ እስከሚያሸንፈን ብንተወው እንደ ሽባው ሰውዬ ሮጠን ወደ ኢየሱስ ሄደን ከክፉ ልማድ አስር የምንፈታበት ጸጋ እንዲሰጠን እንለምነው፡፡

14 April 2021, 12:04