ፈልግ

የፈርዖን ልብ ደነደነ (ማቴ. 11፣12) የፈርዖን ልብ ደነደነ (ማቴ. 11፣12) 

የፈርዖን ልብ ደነደነ (ማቴ. 11፣12)

እግዚብሔር በሙሴ በኩል ፈርኦንን የእስራኤል ልጆች ከግብፅ እንዲወጡ እንዲለቃቸው አስታወቀው፡፡ ፈርኦን አግዚአብሔር ቅጣት ሊፈርድበት ሲል ንስሐ ይገባ ነበር፡፡ በቅጣት ተገዶ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም እሺ ይል ነበረ፡፡ ቅጣቱ ካለፈ በኋላ ግን ወደ ድሮው እምቢኞነቱ በመመለስ የገባውን ቃል በመጣስ ይክድና ያፈርስ፣ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ መፈጸም አሻፈረኝ ይል ነበር፡፡ ከጸጸት ወደ ኃጢአት ከመነሳት ወደ መውደቅ እየተገላበጠ ብዙ ዘመን አሳለፈ፡፡ ሲጨንቀው እሺ ሲመቸው ግን እምቢ ይል ነበር፡፡ ፈጽሞ በመጥፎ ሐሳቡ ጸንቶ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መከተል እምቢ አለ፡፡

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ውሎ አድሮ ፈርኦን እልክ በመግባቱና ልቡንም በማደንደኑ እግዚአብሔር በጣም አዘነበት፡፡ ሙሴ «የፈርኦን ልብ ደነደነ´ እያለ ተናገረው፡፡ እግዚአብሔርም የተለያየ ቅጣትና ፈተና አወረደበት፡፡ መጀመሪያ ምናልባት ከተመለሰ ብሎ ጥቂት ፈተና አውርዶ አስጠነቀቀው፡፡ ነገር ግን ፈርኦን ሐሳቡን አልለወጠም፡፡ ይህንን አይቶ እግዚአብሔር በበኩሉ ጨከነ፣ በመጨረሻም ብርቱ መዓት አወረደበት፡፡ ከወታደሮቹ ጋር በቀይ ባሕር ውስጥ ሰምጠው እንዲቀሩ አደረጋቸው፡፡ በልባችን መንደንደን እያወቅን በኃጢአት ጸንተን እንቀራለን፡፡ ሕሊናችን እያወቀው እግዚአብሔር እየገሰጸን ልባችንን እናጠነክራለን፣ ከኃጢአት መመለስ እምቢ እንላለን፡፡ በኃጢአት ጸንተን በቀረን መጠን በዚያው ልክ የኃጢአት ኃይል ይስበናል፣ ማሸነፍ ያቅተናል፣ የልባችን መደንደን፣ በወደቅንበት ጸንተን መቅረት የባሰ ውድቀት ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ትልቅ በደል ለእኛም ደግሞ ትልቅ ጉዳት ነው፡፡ በክፋት ጸንተን ስንቀር እግዚአብሔር ከእኛ ይርቃል፡፡ ልባችን ከደነደነ እርሱ ደግሞ በበኩሉ አይራራልንም፣ ይጨክንብናል፡፡ በደካማነታችን ኃጢአት ስናደርግ እግዚአብሔር ስንፍናችንን አውቆ አይፈርድብንም፡፡ አውቀን በወደቅንበት ኃጢአት ጸንተን ስንቀር ግን ይፈርድብናል፣ ብዙ ቢታገሰንም በኋላ ይቀጣናል፡፡

እግዚአብሔር እስራኤልን «ልባችሁን አታደንድኑ´ እያለ ያስጠነቅቃቸው ነበር፡፡ መስማትን እምቢ ብለው ልባቸውን ያደነድኑ የነበሩትን አበርትቶ ይቀጣቸው ነበር፡፡ ፈርኦን ልቡን ማደንደን ስላበዛ ብርቱ መቅሰፍት አወረደበት፡፡ በነዚህ አብነቶች ልብ ገዝተን ልባችንን አናጠንክር፡፡ የባሰ ቅጣትና መቅሰፍት እንዳይመጣብን በኃጢአት ጸንተን ልባችን በደንዳናነቱ ጸንቶ እግዚአብሔር ወይም ሞት ቢመጣብን ጠፋን ማለት ነው፡፡

03 March 2021, 11:01