ፈልግ

የካቶሊክ እርዳታ ድርጅት (CRS) በመቀሌ ለሰባ ሺህ ሰዎች የሚሆን የዕለት ደራሽ ድጋፍ አከፋፈለ የካቶሊክ እርዳታ ድርጅት (CRS) በመቀሌ ለሰባ ሺህ ሰዎች የሚሆን የዕለት ደራሽ ድጋፍ አከፋፈለ 

የካቶሊክ እርዳታ ድርጅት (CRS) በመቀሌ ለሰባ ሺህ ሰዎች የሚሆን የዕለት ደራሽ ድጋፍ አከፋፈለ

የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የእርዳታ ድርጅት (CRS) ከተለያዩ የትግራይ ከተማዎች እና ገጠራማ አካባቢዎች ተፈናቅለው በመቀሌ ለተጠለሉ አንዲሁም በከተማዋ እና በዙሪያዋ ለሚኖሩ ሰባ ሺህ ሰዎች የዕለት ደራሽ ድጋፍ አድርገዋል። በድጋፉም ለእያንዳንዱ ሰው 15 ኪ.ግ. የስንዴ ዱቄት፣ ግማሽ ኪ.ግ. ቦሎቄ እና ግማሽ ሊትር ዘይት ለአንድ ወር ተመድቦ በአንድ ጊዜ የሁለት ወር ራሽን ታድሏል። ድጋፉ የተደረገው በካቶሊክ እርዳታ ድርጅት (CRS) ሲሆን እንዲሁም በአሜሪካ እርዳታ ድርጅት (USAID JEOP) በኩል ከአሜሪካ በተገኘ ድጋፍ መሆኑንታውቋል።

በአዲግራት ሀገረስብከት ከጥር 4 እስከ 6 2013 ዓ.ም. ጉብኝት አድርገው የተመለሱት የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ልዑካን እንደገለጹት  በመላው ትግራይ የሚገኙትን የጦርነት ተጎጂዎች በአፋጣኝ ለመድረስ እንዲቻል ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል። በውይይቱም ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ክቡር ዶ/ር ሙሉ ነጋ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ክቡር አቶ አብርሃ ደስታ ጊዜያዊ  ምክትል አስተዳደር እና ክቡር አቶ አበበ ገብረሕይወት የተገኙ ሲሆን በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ በኩል ክቡር ዶ/ር አባ ተሾመ ፍቅሬ ጠቅላይ ጸሐፊ፣ ክቡር አቶ በቀለ ሞገስ የማሕበራዊ ልማት ዳይሬክተር፣ የካቶሊክ እርዳታ ድርጅተከፍተኛ የሥራ  ኃላፊዎች እንዲሁም ከአዲግራት ሀገረስብከት ክቡር አባ አብርሃ ሐጎስ  የአዲግራት ካቶሊካዊ ሰበካ ዳይሬክተር፣ ክቡር አባ ወልደማርያም የመቀሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና ሲስተር መድኅን ተስፋዬ የፍቅር ሥራ እህቶች የፕሮጀክት አስተባባሪ ተገኝተዋል።

በተከታታይ ባደረጓቸው ሁለት ስብሰባዎችም በቀጣይ በመላው ትግራይ የሚገኙ ተጎጂዎችን በአፋጣኝ መድረስ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ በዝርዝር በመወያየት ለዚሁ ዓላማ ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ የጋራ ግብረሃይል አቋቁመዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በበኩሉ የክልሉን ሰላም እና መረጋጋት ከማስጠበቅ ጎን ለጎን  መሰረተ ልማቶችን  በመጠገን በአፋጣኝ ወደ ሥራ ለማስገባት በሙሉ ኃይሉ እየሠራ መሆኑን አሳውቋል። የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ተወካዮችም ለምግብ እና ለመድኃኒት ድጋፍ የሚሆኑ ግብይቶችን ለመፈጸም እና ከቦታ ቦታ በአፋጣኝ ለማጓጓዝ እንዲቻል የባንክ አገልግሎት ማነቆ እንዳይሆን እና የገንዘብ ዝውውርም ለጊዜውም ቢሆን በልዩ ሁኔታ መስተናገድ የሚችሉባቸውን ሁኔታዎች ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር እንዲያመቻቸ አሳስበዋል።

22 January 2021, 12:41