ፈልግ

ኢየሱስ ማዕበሉን ጽጥ አደረገው ኢየሱስ ማዕበሉን ጽጥ አደረገው  

የኀዳር 20/2013 ዓ.ም ሰንበት ዘምኩራብ /ዘአስተምሕሮ 3ኛ/ እለተ ስንበት አስተንትኖ

የእለቱ ምንባባት

1.     ዕብ 12፡25-29

2.     ያዕ 3፡ 4-12

3.     ሐዋ. 21፡27-40

4.     ማቴ 8፡23-34

የእለቱ ቅዱስ ወንጌል

ኢየሱስ ማዕበሉን ጸጥ አደረገ

ከዚያም ኢየሱስ ወደ ጀልባ ገባ፤ ደቀ መዛሙርቱም ተከትለውት ገብተው ሄዱ። ድንገት ኀይለኛ ማዕበል በባሕሩ ላይ ተነሥቶ ጀልባዪቱን እስኪሸፍን ድረስ አወካቸው፤ በዚህ ጊዜ ግን ኢየሱስ ተኝቶ ነበር። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው ቀሰቀሱትና፣ “ጌታ ሆይ! ጠፋን፤ አድነን” አሉት።

ኢየሱስም፣ “እናንተ እምነት የጐደላችሁ፤ ለምን ይህን ያህል ፈራችሁ?” አላቸው፤ ከዚያም ተነሥቶ ነፋሱንና ማዕበሉን ገሠጸ፤ ወዲያውም ጸጥታ ሰፈነ። ሰዎቹም፣ “ነፋስና ባሕር እንኳ የሚታዘዙለት፣ ይህ እንዴት ያለ ሰው ነው?” እያሉ ተደነቁ።

ከርኩሳን መናፍስት ስለ ተፈወሱ ሁለት ሰዎች

ባሕሩን ተሻግሮ ጌርጌሴኖን ወደሚባል አገር እንደ ደረሰ፣ አጋንንት ያደሩባቸው ሁለት ሰዎች ከሚኖሩበት የመቃብር ቦታ ወጥተው ተገናኙት። በዚያ መንገድ ሰው ማለፍ እስከማይችል ድረስ እጅግ አደገኞች ነበሩ። እነርሱም “የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ፤ ከእኛ ምን ጕዳይ አለህ? ጊዜው ሳይደርስ ልታሠቃየን መጣህን?” እያሉ ጮኹ። ከእነርሱ ትንሽ ራቅ ብሎ፣ የብዙ ዐሣማ መንጋ ተሰማርቶ ነበር። አጋንንቱም ኢየሱስን፣ “የምታስወጣን ከሆነ ዐሣማዎቹ መንጋ ውስጥ እንድንገባ ፍቀድልን” ብለው ለመኑት። ኢየሱስም፣ “ሂዱ!” አላቸው። አጋንንቱም ከሰዎቹ ወጥተው ዐሣማዎቹ ውስጥ ገቡ፤ ዐሣማዎቹም በሙሉ ከነበሩበት አፋፍ እየተጣደፉ ባሕሩ ውስጥ በመግባት ውሃው ውስጥ ሰጥመው ሞቱ። የዐሣማዎቹ ጠባቂዎችም ሸሽተው ወደ ከተማ በመሄድ፣ የሆነውን ሁሉና በአጋንንት ተይዘው በነበሩት ሰዎች ላይ የተደረገውን ነገር አወሩ። እነሆም፤ መላው የከተማ ነዋሪ ኢየሱስን ለመገናኘት ወጣ፤ ባዩትም ጊዜ አገራቸውን ለቅቆ እንዲሄድ ለመኑት።

የእለቱ አስተንትኖ

በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ዛሬ በዚህ ሰንበት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃሉ አማካኝነት ያስተምረናል በቃሉም ይመግበናል፡፡ በሐይወታችን አዲስ መንፈሳዊ ጉዞ እንዲጀምር የእርሱን ጸጋና ኃይል ያላብሰናል፡፡

በኦሪት ዘመን እግዚአብሄር ለእስራኤላውያነ ከሲና ተራራ ይናገር ነበር እነርሲ ግን የእርሱን ቃል ከመከተልና ከመፈፀም ይልቅ ኀጢአትን በመሥራ እግዝአብሔርን አሳዘኑ፡፡ በስተመጨረሻም አንደያ ልጁን ልኮ በእርሱ አማካኝነት ቢናገርም እርሲንም አልተቀበሉትም ይባስ ብለው በመስቀል ላይ ሰቀሉት፡፡ ዛሬም ቢሆን እግዚአብሔር በተለያየ መልኩ ይናገራል፡፡ በተለያ መልኩ ልጆቹን ያስተምራል፡፡ እግዚአብሔር ሲያስተምረን የእርሱን ቃል አንሰማም ብንል ልክ እንደ አይሁዳውያኑ ከቅጣት አናመልጥም ዕብራውያን 3፡7-10 እንዲህ ይላል፡፡ ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሚል ዛሬ ድምጹን ብትሰሙ በምድረ በዳ በፈተና ቀን አመፅ እንዳደረጋችሁት ልባችሁን አታደንድኑ አባቶቻችሁ በዛ ተፈታተኑኝ መረመሩኝ ያደረግሁትንም ሁሉ ለዓርባ ዓመት አዩ በዚህም ትውልድ ላይ የተቆጣሁት ለዚህ ነበር እንዲህም አልሁ ልባቸው ሁልጊዜ ይስታል መንገዴንም አላወቁም ስለዚህ በቁጣዬ እንዲህ ብዬ ማልሁ ወደ ዕረፍቴ ከቶ አይገቡም

የእግዚአብሔር ቃል ኃይል አለው የእግዚአብሔር ቃል ሰማይና ምድርን ያናውጣል /ዘፀ 19፡18/ የእግዚአብሔር ቃል አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ያፈጥራል /ራዕይ 21፡1/ ስለዚህ እኛም በእግዚአብሔር ቃል ሰምተን የምንኖር ከሆነ ልክ እንደ ሰማያዊቷ እየሩሳሌም ምንም ሳንናወጥ ጸንተን እንኖራለን፡፡ በቃሉ ፀንተው የሚኖሩ ሁሉ ምንም እንኳን የሚያቃጥለው እሳት ወደ እነርሱ ሲጠጋ ልክ እንደ ወርቅ የበለጠ እየጠሩ ወርቅነታቸውን እያስመሰከሩ ይኖራሉ፡፡ በቃሉ ጸንተው የማይኖሩ ደግሞ የሚያቃጥለው እሳት ከነ ክፉ ምግባራቸው ይበላቸዋል፡፡ / ዕብ. 12፡29/       

በሁለተኛው ንባብ ቅዱስ ሐዋርያው ያዕቆብ በምዕራፍ 3 ላይ እንደበታችን ዘወትር የታረመና ንጹህ መሆን እንዳለበት ይመክረናል፡ ምክንያቱም በአንደበታችን አማካኝነት እግዚአብሐርንም ሆነ ብዙ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን ልናሳዝን እንተላለንና ነወ፡፡ አንድ ፈረስ በትንሽ ልጓም እንደሚመራ እንዲሁ ደግሞ አንድ ግዙፍ መርከብ በትንሽ መሪ እንደሚመራ ሁሉ እንዲሁ መላ ሰውነታችን በሕይወታችን ላይ ትልቅ ለውጥ ለማምጣት በመትችለው በትንሿ አንደበታችን ይመራል፡፡ ትንሿ እሳት አገር የሚያህልን ጫካ ማቃጠል እንደምታትለው እንዲሁ ክፉ አንደበት ቤተሰብን ለመበተን፣ ጓደኛሞችን ለማጣላት፣ ሐሜትንና ሐሰትን በማውራት በቤተክርስቲያንም ውስጥ ትልቅ ቀውስና መለያየትን ትፈጥራለች፡፡

አንደበታችን ልክ እንደ እሳት ነው ሰይጣንም ይህንን ስለሚያውቅ አንደበታችንን አብዛኛውን ግዜ ይጠቀምበታል፡፡ በአንደበታችን አማካኝነት ሁለእንተናችንን ያረክሳል፣ የተስተካከለ አካሄዳችንን ያበላሻል፣ ከእግዚአብሔርና ከሰዎች ጋር ያለንን መልካም አካሄድ መልካም ግንኙነት ያደፈርሳል፣ ሁሌም ወደ ጥፋትና ክፋት ጐዳና ይመራናል፡፡

መዝሙር 140፡3 እንዲህይላል እግዚአብሔር ሆይ ከክፉ ሰዎች አድነኝ ከአመፅኞችም ሰዎች ጠብቀኝ እነርሱ በልባቸው ክፉ ነገርን ያውጠነጥናሉ በየዕለቱም ጦርነት ይጭራሉ ምላሳቸውን እንደ እባብ ያሾላሉ ከንፈራቸውም በታች የእፋኝት መርዝ አለ፡፡

ቅዱስ ሐዋርያው ያዕቆብ ሁለት ምላስን ይዞ መጓዝ እንደማይገባ ያሰምርበታል ጸሎትን ስናደርስና በእግዚአብሔር ፊት መልካም ቃላትን እናወራለን እንዲሁም በሰዎች ፊት መልካም ለመምሰል መልካም ቃላትን እንደረድራለን እናወራለን ሥራችንንና ከቤተክርስቲያን ውጪ ደግሞ አካሄዳችንንና ተግባራችን መልካም ካልሆነ ይህ አካሄዳችን ፍጹም የታረመ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም የምንናገረውን መልካም ቃል ኃላ በተግባራችን ብናፈርሰው እውነተኛ ክርስቲያኖች እንዳልሆንን በተግባራችን እያስመሰከርን ነው ማለት ነው፡፡ 

በተፈጥሮ ከአንድ ምንጭ የሚፈልቅ ውሃ ጣዕሙ አንድ ዓይነት ነው ከአንድ ምንጭ ሁለት ዓይነት ጣዕም ያለው ውሃ አይፈልቅም እንዲሁ ደግሞ በአንድ ሰው ውስጥ ሁለት የተለያየ ነገር የሚያወራ ምላሥ ሊኖር አይገባም ፡፡  ሁልጊዜ መልካም ነገር የሚያወራ ምላስ ምግባሩም እንዲሁ መልካም ሊሆን ይገባል በተመሳሳይ መልኩ ከአንድ ዛፍ ላይ አንድ አይነት ጣዕም ያለው ፍሬ ይለቀማል እንጂ ጣፋጭና ጐምዛዛም ፍሬ እንደማይለቀም ሁሉ እንዲሁ ከአንድ ሰው ገንቢም አፍራሽም ሃሳቦች ሊቀርቡ አይገባም ፡፡

በሐዋርያት ሥራ 21፡ 27-40 አይሁዳውያን እንዴት በሃሰት ሐዋርያው ጳውሎስን እንደከሰሱት እናያለን፡፡ ይህ ተመሳሳይ ክስ በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ላይ ተግባራዊ እንዳደረጉት እንዲሁ ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስንም አስወግደው አስወግደው እያሉ ጮሁ ምክንያቱም አይሁዳውያን በሕጋቸው ማንም አይሁዳዊ ያልሆነ ሰው ወደ ቤተመቅደስ ቢገባ ቤተመቅድሱ ረክሷል ብለው ስለሚያምኑ ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ ሌሎች አይሁዳዊ ያልሆኑ ሰዎችን ወደ ቤተመቅደስ አሰገብቷል ብለው በሐሰት አንደበት መሰከሩበት፡፡ ይህ ደግሞ እግዚአብሔር ራሱ ለአይሁዳውያን በሙሴ በኩል የሰጣቸውን ትዕዛዝ ተላለፉ በሐሰት አትመስክር ዘፀአት 20፡16፡፡ ሰው በሃሳት የሚመስክረው በአንደበቱ ነው ስለዚህ ዘወትር አንደበታችን በምትፈጥረው የሐሰት ክስ የጻድቁን ሕይወት ወደ ሞት እንወረውራለንና ዘወትር አንደበታችን የታረመና ሐቅን ብቻ የሚመሰክር እንዲሆን ይገባዋል፡፡

እኛ ሁል ጊዜ አንደበታችን የታረመ እንዲሆንና ሁሊጊዜ አውነትንና ሐቅን ብቻ እንዲያውራ መልካም የሆነን ነገር እንደያወራ ራሳችንን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ያስገዛን መሆን ይገባናል፡፡ ምን አለበት በዚህ ድክመት ውስጥ ካለን ደግሞ ጌታችን እየሱስ ክርስትስ ድክመታችንን ሊያስወግድልን ካለንበት የኃጢያት ቀንበር ሊያወጣን ዘወትር ወደ እኛ ይቀርባልና እኛም ወደ እርሱ እንድንጠጋ ያስፈልጋል፡፡

በዞሬው ወንጌል ማቴዎስ 8፡23-3 እንዳደመጥነው ነፋስና ባሕር እንኳን የሚታዘዙለት አምላካችን በውስጣችን ያለውን የክፋት ዝንባሌ ፈንቅሎ ያወጣልናል፡፡ ነገር ግን  ለዚህ ሁሉ የእኛ በእርሱ ያለን መተማመንና እምነት ከፍተኛ ቦታን ይይዛል፡፡

ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በዚሁ ወንጌል ቁጠር 26 ላይ ደቀ መዛምርቱን በእምነታቸው ጐደሎ መሆን ሲገስፃቸው እናያለን እናንተ እምነት የጐደላችሁ ይህን ያህል ለምን ፈራችሁ ስለዚህ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በእርሱ ላይ እምነታትንን ሙሉ በሙሉ ከጣልን የፈለግነውን ሁሉ ሊሰጠንና ሊያደርግልን ዝግጁ ነው፡፡

ጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ማወቅ ብቻ ብቁ አየደለም ካወቅነው በኋላ እንድንወደው ከዛም በኋላ ትዕዛዙን መፈፀመ ይገባል፡፡ በዚሁ በማቴዎስ ወንጌል ከቁጠር 28 ጀምሮ ጌትችን እየሱስ ክርስቶስን በሰውዬው ያደረው እርኩስ መንፈስ እንደወቀው እናያለን ለዚህም ነው በቁጥረ 29 ለይ የእግዚአብሐር ልጅ ሆይ ከእኛ ምን ጉደይ አለህ ጊዜው ሰይደርሰ ልታሳቃየን መጣህን ብሎ የተናገረው፡፡ በነገራችን ላይ ይህንን ተመሳሳይ ወንጌል ወንጌላዊው ማርቆስ ልክ እንደ ወንጌላዊው ማቴዎስ ሁለት አጋንንት ያደሩባቸው ሰዎች ሳይሆን አንድ ሰው እንደሆነ ይገልፃል የሆነ ሆኖ ታሪኩ ያው ስለ አንድ ጭብጥ ያወራል ጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ከማወቅ አልፈን በእርሱ አምነን እስካልታዘዝነው ድረስ እምነታችን ከንቱ ነው እርሱን መከተላችን ከንቱ ነው፡፡

ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በሰውየው ያደረው እርኩስ መንፈስ እንዲተወው ቢለምነውም ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ግን እንዲወጣ አዘዘው፡ በቃሉም  ገሰፀው፡፡ በአጠገብ በነበሩት አሳማዎች ለመግባት ስለለመኑት ፈቀደላቸው ይህም የማያሰየን በመጀመሪየ ደረጃ አጋንንት ሁለጊዜ ከአንድ አካላዊ ነገር ውጪ ለመኖር በጣም የስቸግራቸዋል ስለዚህም ለዚህ ነው ቢቻል ከእነርሱ ሰይጣናዊ አስተሳሰብ ጋር የሚሄድ ሰው በመፈለግ በውስጡ የሚሰፍሩት እግዚአብሔር ከዚህ ከሰይጣን ማረፊያነት መጠለያነት ይሰውረን፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የሚያስተምረን በአግዚብሔር ፊት የአንድ ሰው ሕይወት ከብዙ ሺህ አሳማኞች እንደሚበልጥ እንረዳለን፣ በእግዚአብሔር ዘንድ የአንድ ሰው ሕይወት ከብዙ ሺህ ከሚቆጠሩ አሳማዎች ዋጋ እንዳለው እንረዳለን በሉቃስ ወንጌል 15፡17 እንዲህ ይላል ንስሃ ከሚያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሃ በሚገባ አንድ ኃጢያተኛ በሰማይ ታላቅ ደስታ ይሆናል ይህም እግዚአብሔር ለእያንዳዳችን ሕይወት ምን ያህል እንደሚጨነቅና እኛም ሁልጊዜ ደስታ የተሞላበት ሕይወት አንዲኖረን እንደሚሠራ ያስተምረናል፡፡ በሶስተኛ ደረጃ  ደግሞ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስን የማዳንን ብቻ ሳይሆን ሰይጣንና ሰራዊቱን ሁሉ ለማጥፋት ትልቅ ኃይል እንዳለው እንረዳለን፡፡

በስተመጨረሻም በሉቃስ ወንጌል 8፡38 ላይ ባለው ተመሳሳይ ታሪክ ውስጥ ይህ አጋንንት ያደረበት ሰው ጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ጥያቄ አንስቶ ነበር ነገር ግን ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ አልፈቀደለትም ይልቁንም ወደ ቤተሰቦቸ ተመልሶ እግዚአብሔር ያደረገለትን ታላቅ ነገር እንዲመሰክር አዘዘው ይህም የሚያስተመረን ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት መጀመር ያለብን በገዛ ቤታችን፣ በገዛ ቤተሰባችን፣ መሆን እንዳለበት ነው፡፡ ሰው ሁልጊዜ ያለውን ይሰጣልና በገዛ ቤቱ በገዛ ቤተሰቡ ውስጥ እውነተኛ ምሥክርነት የሚሰጥ ሰው በውጪም እንዲሁ ሳይናገር ይህን አኗኗሩን የሚመለከት ሁሉ እውነተኛ የክርስቶስ ወዳጅ መሆኑን ይመሰክሩለታል፡፡ ነገር ግን በወጪ መልካም ክርስቲያን መስሎ በቤቱ ውሰጥ ግን ሌላ ሰው ሌላ መጥፎ ገፀ ባህሪ ካለው ይህን ዓይነቱ ሰው ዛሬ በቅዱስ ያዕቆብ መልእክት እንዳደመጥነው በሁለት ምላስ የሚጠቀም ሃሰተኛ ሰው ነው ስለዚህ ከዚህ ዓይነቱ ተቀያያሪ ባሕሪ እግዚብሐር እያንዳዳችንን ይሰውረን ይልቁኑም በእምነታችን የበረታን በክርስትና እምነታችን ደግሞ ጠንካሮች ሆነን ለመጓዝ ዘወትር የሁላችን እናትና አጋዥችን የሆነች እመቤታችን ቅደስት ድንግል ማርያም ጸጋንና በረከትን ከልጇ ከጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ታስጠን የሰማነውንም ቃል በተግባር ለመተርጐም እንድንችል ከጐናችን ትቁምልን፡፡

28 November 2020, 11:32