ፈልግ

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ 

ማሕበራዊ አስተምህሮ የቤተክርስቲያን አገልግሎት መገለጫ ነው

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ ተፈጥሮአዊ ባሕሪይ

ክፍል 21

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማህበራዊ አስተምህሮ የቤተክርስቲያኗ አስተምህሮ መገለጫ ነው፣ ምክንያቱም ቤተክርስቲያኗ የምትቀርፀው ርዕሰ ጉዳይ የምታስተምርበት እና ተልዕኮዏን የምትወጣበት መንገድ ስለሆነ ነው። እሱ የአንድ የቤተ-ክርስቲያን አካል እና ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን የጠቅላላው ማህበረሰብ፣ ቤተክርስቲያኗ ህብረተሰቡን እና ማህበራዊ አወቃቀሮችን እና ለውጥን በተመለከተ የነበራትን አቋም የምትገልፅበት አገላለፅ ነው። የቤተክርስቲያኗ ማኅበረሰብ በሙሉ - ካህናት ፣ ገዳማዊያን እና ምዕመናን - እያንዳንዱ በማህበረሰቡ ውስጥ በሚገኙት የተለያዩ ሥራዎች ፣ ሥርዓቶች እና አገልግሎቶች መሠረት በዚህ ማህበራዊ አስተምህሮ ምስረታ ውስጥ ይሳተፋሉ።

እነዚህ ብዙ እና ልዩ ልዩ አስተዋጾች - እነሱ እራሳቸው “የመላው የሰው ልጅ መላኮታዊ የሆነ የእምነት ግልጸት በመሆን፣ ማሕበረሰቡ የሚተዳደርበት እና የሚነቃቃበት በአጠቃላይ የቤተክርስቲያን አስተምህሮ ከግምት ባስገባ መልኩ ትርጓሜ ተሰጥቶት የሚከናወን ማሕበራዊ አስተምህሮ ነው። የቤተክርስቲያን አስተምህሮን በይፋ ማከናወን የሚችሉት ለዚህ አስተምህሮ እጅግ ተገቢ በሆነ መልኩ የተዘጋጁ ሰዎች አማካይነት ሲሆን በተጨማሪም በእምነት እና ሥነምግባር መስኮች ከክርስቶስ ሥልጣን የተሰጣቸው ሰዎች ሊሆኑ ይገባል። የቤተክርስቲያኗ ማህበራዊ አስተምህሮ ብቃት እና ባለሙያ በሆኑ ሰዎች ብቻ የሚሰጥ አስተምህሮ ወይም ከእዚህ የመነጨ አስተሳሰብ ወይም ሥራ ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን የቤተክርስቲያኗ አስተሳሰብ ነው፣ ምክንያቱም ክርስቶስ በሐዋሪያት እና በተተኪዎቻቸው ላይ ያስተላለፈውን ስልጣን በመጠቀም በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና በጳጳሳት ጭምር ጋር በመተባበር የሚሰጥ አስተምህሮ ነው (የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቁ. 2034)።

በቤተክርስቲያን ማኅበራዊ ትምህርት ውስጥ የቤተክርስቲያን የማስተማር ሥልጣን በተለያዩ አካላትና መስኮች ይገለጻል። ከሁሉም የሚበልጠው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትና የጉባዔው አጠቃላይ የማስተማር ሥልጣን ነው። የዚህን ማኅበራዊ ትምህርት አቅጣጫ የሚወስነውና እድገቱን የሚቆጣጠረው ይኸው የማስተማር ሥልጣን ያለው አካል ነው። ይህም በበኩሉ ከብዙ ልዩ ልዩ የአከባቢ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር በተዛመደ መልኩ ትምህርቱን ከሚተረጉመው እና በሥራ ላይ ከሚያውለው የጳጳሳት ሥልጣን ጋር የተዋሃደ ነው። ጳጳሳት በማኅበራዊ ትምህርት አማካይነት ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሥልጣን ጠቃሚ አስተዋጽ እና ኃይል ይሰጣል። በዚህ ዓይነት በቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ ውስጥ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በአንድነት የሚሰሩ የቤተክርስቲያን እረኞችን ህብረት የሚገልጽ ተዘዋዋሪ ሥራ አለ። ከዚህ የሚነሳው ትምህርት በዚህ መልኩ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትንና የጳጳሳትን አጠቃላይ ትምህርት እና ጳጳሳት በእየአከባቢያቸው የሚሰጡትን ትምህርት በአንድነት ያጠቃልላል (Paul VI, Apostolic Letter Octogesima Adveniens, 3-5: AAS 63 (1971), 402-405)። የቤተክርስቲያን የግብረገብ ትምህርት አካል እስከሆነ ድረስ የቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ እንደ ግብረገብ ትምህርት ሁሉ ተመሳሳይ የሆነ ክብርና ሥልጣን አለው። ይህም መዕመናንን ሁሉ የሚያስገድድ እውነተኛ የማስተማር ሥልጣን ነው፣ የልዩ ልዩ ትምህርቶች የትምህርት ክብደትና የሚፈለገው ስምምነት የሚወሰነው በትምህርቶቹ ልዩ ባህሪ፣ በነፃነት ደረጃና በተዘዋዋሪነታቸው ላይ መሰረቱን ያደረገ ነው።

አዘጋጅ እና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

11 August 2020, 09:12