ፈልግ

በሊቢያ የሚገኙ አፍሪካዊ ስደተኞች በሊቢያ የሚገኙ አፍሪካዊ ስደተኞች  

ለወጣት ስደተኞች ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የሚረዳ ሐዋርያዊ እንክብካቤ

በዚህ ጹሁፍ ውስጥ የተጠቀሰው ሐዋርያዊ እንክብካቤ  የማድረግ ዓላማ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ወጣት ስደተኞች ስደታቸውን ከመጀመራቸው በፊት ቅድመ መከላካል ማድረግ እንደ ሚገባ እና ለወጣቶች የሚደረገው ሐዋርያዊ እንክብካቤ በመንፈሳዊ መንገድ ብቻ የሚደረግ ሳይሆን በተቀናጀ እና በተደራጀ መልኩ የተለያዩ የወጣት ሰበዓዊ አገልግሎቶች አቅጣጫ  መመልከት ተገቢ ስለሆነ በዚህ አግባብ ወጣቶች መንፈሳዊ እና ሰብዓዊ የሆኑ አስተምህሮዎችን እንዲያገኙ ቤተክርስቲያን የበኩሏን ጥረት ታደርጋለች። 

በዚህ መሠረት የአመለካከት ለውጥ ይመጣ ዘንድ የቤተክርስቲያኗን መዋቅሮች በመከተል እና ተኩረት በመስጠት፣ ተቀባይነት ያለውን እሴቶችን ዘወትር ወደ ተፈላጊነት ለመቀየር ትጥራለች። በዚሁ ሁኔታ የጥናቱ ዓላማ ቤተክርስቲያን በምጸጠው ሐዋርያዊ እንክብካቤ  በመታገዝ ምላሽ እንዲሰጥ፣ በአገልግሎቱ የወጣትን ፍላጎት ባማከል መልኩ እንዲከናወን በዓለም አቀፍ ደረጃ በምትገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሰረታዊ አመለካከት ሁሉን አቀፍ ቤተክርስቲያን እንደ መሆኗ እና በክርስቶስ የተላከች እንደመሆኗ መጣን ተነሳሽነቷን እና ኃላፊነቷን መወጣት ያለባት በተለይም  በአሁኗዊ ሁኔታ በሀገራችን በወጣቶች ላይ የተጋረጠውን ፈተና፣ ወጣቶች በተለያዩ ምክንያቶች ከቦታቸው ለተፈናቅለው ለብዙ ችግሮች   ተዳርገው ከአገር ለሚሰደዱ ወጣቶች የተሻለ ሐዋርያዊ እንክብካቤ መስጠት የሚያስችሉ እቅዶችን በመንደፍ መርሃ-ግብሮችን በመዘርጋት እንዲተገበሩ ማደረግ ይኖርባታል። ሕገወጥ የሆነ የወጣት ስደተኞች እንቅስቃሰ ለመግታት በአገር ደረጃ በተቻለ መጠን ከተለያዩ አካላት ጋር በመተባበር የስራ እድል  በመፍጠር ፣ ለወጣት ስደተኞች ያለን አመለካከት ለመቀየር፣ በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ልማት አጀንዳን በመቅርጽ፣ ግንዛቤን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ በቤተክርስቲያን ይበልጥ መሰራት እንዳለበት ለመደገፍ ጭምር ይረዳል።

ር.ሊ.ጳ  ፍራንቸስኮስ እ.አ.አ በ2019 በድህረ-ሲኖዶስ ምልከታ ላይ እንዳብራሩት “ስደት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታየው መዋቅራዊ ክስተት እንጂ ድንገተኛ አደጋ አይደለም፡፡ የቤተክርስቲያኗ ትኩረት በተለይ ከጦርነት፣ ከዓመፅ፣ ከፖለቲካ ወይም በሃይማኖት ምክኛት የሚከሰት ስደት ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በከባድ ድህነት ምክንያት አደጋዎችን ሸሽትወ በሚሰደዱ ሰዎች የሚከሰት ስደት ላይ ያተኮረ ነው “ (Christus Vivit ቁ.91) ማለታቸው ይታወሳል

 ይህንን ሀሳብ እንደ መግቢያነት በመጠቀም ወደ ዋናው ዓላማ ለመመለስ እፈልጋለሁ። የዚህ  ጽሑፍ ዓላማ ከላይ እንዳሳሰባኩት ለችግሮች ዘላቂ መፍተሄ ለማምጣት፣ ቤተክርስቲያን ከመንፈሳዊ አገልግሎት ጎን ለጎን ለሰው ልጅ አስፈላጊ የሆኑ እገዛዎችን መስጠት እንደ ሚኖርባት ለመግልጽ ነው። ስለሆነም ቤተክርስቲያን በአገልግሎት ዘርፍ በሁለት አቅጣጫዎች  ትኩረት መስጠት ይኖርባታል ማለት ነው። ይህ ማለት አገልግሎቱ መንፈሳዊ እና ቁሳዊ የሆኑ አግልግሎቶችን ለመስጠት ያስችላት ዘንድ ለልማታዊ መዋቅር እንደ አስፈላግነቱና እንደቦታው ትኩረት መስጠት ይኖርባታል ማለት ነው።

በቅዱስ ዶንቦስኮ የወጣቶች አገልግሎት አስተምሮ መሰረት እንደምለው በልማት ዙርያ የወንጌላዊነቱ ሥራ የቤተክርስቲያን አካል በመሆን ለተለያዩ ወጣቶች ሁለንተናዊ የልማት ፍላጎት፣ በትምህርታ ፕሮግራም እንዲበረቱ ከፍተኛ አስተዋጾ በማደረግ ላይ ይገኛል። ስለዚህ የሰዎች እሴት እና መሠረታዊ የሐዋርያዊ አገልግሎት ፕሮግራም (ፕሮጄክት) በምክንያታዊነት፣ በሃይማኖታዊ ግንዛቤ እና በመልካም ስራ ላይ የተመሠረተ ስርዓት ባለው መልክ መታየት እንደ ሚኖርበት እቅዱ አበክሮ ይገልጻል።

የቅዱስ ዶኒ-ቦስኮ ዓላማ ስለ ወጣቶችና ስለ ወጣቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በመጠቆም፣ የወጣትነት ዕድሜ ከልጅነት ወደ አዋቂነት፣ እንድሁም በሃይማኖት ጠንክሮ ወደ ክርስቲያንዊ ማንነት የሚሸጋገሩበት ወቅት እንደሆነ ያሰመርበታል። ስለዚህ በዚህ ጹሑፍ የግባችን ዓቅጣጫ ለወጣት ስደተኞች የሐዋርያዊ እንክብካቤ መስጠት የሚቻልበትን ሁኔታ ይበልጥ በማደራጀት፣ እቅድ በማውጣትና የቤተክርስቲያኗን የህብረተሰብ ተሳትፎ በማጣመር የሚሰራ ሥራ ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት ለወጣቶች ጠንካራ የሐዋርያዊ እንክብካቤ አገልግሎት ስለሚያስፈልግ፣ በተለይም በዋናነት፣ ተቀዳሚ አማራጭ የሚሆነው ወጣቱ ከመሰደዱ በፊት በአገራቸው ሆኖ ዕድላቸውን በብልሃት ለመወሰን ይችሉ ዘንድ ግንዛቤ የሚፈጥር ስራ በማከናወን በተቻለ መጠን ችግሩን የሚጋፈጡበት መንገድ ለማመቻቸት ዕድል መስጠት አስፈላጊ ሲሆን፣ በተጨማሪ ከተሰደዱበት አገር ሲመለሱ የአዕምሮአዊ ምክርና እገዛ ለማድረግ፣ እድሁም ከአገር ወጥተው ለሚኖሩት ሁሉ ባሉበት እንግዳ አገር የሐዋርያዊ  እንክብካቤን አገልግሎት ዕድል እንድያገኙ  በማድረግ፣ የተሻለ አቅጣጫ በማሳየት፣ ግንዛቤ ማስጨበጥ ያስፈልጋል። ምክንያቱም ካቶሊካዊነት ማለት አንድነት፣ አብሮነት እና ዓለምአቀፋዊነት ማለት ነውና ፡፡

የወጣት ስደተኞች እንቅስቃሰ በሐዋርያዊ አግልግሎት ለመደገፍ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የሚያስችል አቅም ለማግኘት ብዙ ወጣቶች ለቤተክርስቲያናቸው ያላቸውን ቀና አመለካከት እንዲያሳድጉ ማድረግ የሚገባ ሲሆን የተሻለ አቅጣጫ መዘርጋት ያስፈልጋል።  ወጣቶች በቤተክርስቲያን ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ በሐዋርያዊ አገልግሎት እንቅስቃሴ ሊነቃቃ በማስቻል ረገድ አስፈላጊ መስዋዕነት መክፈል ይገባል። በዚህ ሁኔታ የእምነት አመለካከቶች ወደ ቀጣዩ ትውልድ እንዲሸጋገሩና እንዲቀጥል በማድረግ፣ ጠንካራ የወጣት ሐዋርያዊ   እንቅስቃሴ  አገልግሎት በቤተክርስቲያኗ ውስጥ አዲስ አመለካከት እንዲመጣ ያግዛል።

አዘጋጅ እና አቅራቢ አባ ኤርሚያስ ኩታፎ

06 August 2020, 08:54