ፈልግ

የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ተአምራት አደረገች የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ተአምራት አደረገች 

የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ተአምራት አደረገች

የሐምሌ 15/2012 ዓ.ም አስተንትኖ

ዳዊት በእግዚአብሔር እጅ ተደግፎ ከብዙ ድንገታዊ ነገሮች እንደዳነ እና ለክብር እንደ ደረሰና የልዑልንም ሐሳብ እንደፈጸመ ስላየ «የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ተአምራትን አደረገች፣ የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ከፍ አደረገችኝ፣ የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ኃይልን አደረገች አልሞትም በሕይወት እኖራለሁ የእግዚአብሔርንም ሥራ እናገራለሁ” (መዝ. 117፣6) እያለ ዘመረ፡፡

ያለፈውንና ያለውን ሕይወታችንን ስንመለከት ይህን ዳዊት የሚለውን ቃል መድገም አለብን፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ በእኛ ላይም ትልቅ ተአምር እንዳደረገች ያስረዳናል፡፡ የእግዚአብሔርን እጅ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከኃጢአት ወደ ጽድቅ አሻገረችን፤ አባላቷ እንድንሆን ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን አስገባችን፣ ከብዙ ስህተትና ከጨለማ መውጣታችንና ሃይማኖተኛ መሆናችንም በራሳችን ሳይሆን በአምላክ እጅ እርዳታ ነው፡፡ እኛም እንደማንኛቸውም ደካሞች ነበር፡፡ ስለዚህ እኛም ከአረማውያን የበለጠ ልንሳሳትና ልንወድቅም በቻልን ነበር፡፡ ነገር ግን ከውደቅ የዳንነውን የጸጋን አምላክ ኃይል ይዘን ነው፡፡ አንዳንድ ጓደኞቻችን በፈተና ጊዜ ሲሸነፉ በትልቅ ኃጢአት ሲወድቁ እኛ ግን ከብዙ ውድቀቶች የዳንነው ብርቱ ፈተናዎችን ልናሸንፍ የቻልነው፣ በኃጢአት ያልተበከልነው ከእኛ ጥረት ሳይሆን ከእግዚአብሔር እጅ ነው።

መነኮሳትና ካህናት … በመሆን በእግዚአብሔር ቤት በመገኘት ለእርሱ አገልግሎት መሰጠታችን ሁሉ የእግዚአብሔር ጸጋ ነው፡፡ ገና በጥሪያችን ጸንተን መገኘታችን በመንፈሳዊነት በእግዚአብሔር ቤት መኖራችን ሁሉን ሥራ በሚገባ መፈጸማችን በእግዚአብሔር እጅ ስለታዘዝን ነው፡፡ መንፈሳዊ አረማመዳችን መልካም ቢሆን በመንፈሳዊ ጉዳይ ጠንቃቆች ብንሆን በእኛ ኃይል ሳይሆን በእግዚአብሔር ኃይልና ጸጋ ነው፡፡ የእግዚአብሔር እጅ ነች በጥሩ መንገድ የምትመራን፡፡ ይህችን የተከበረች እጅ በአድናቆት እናመስግናት ሕይወታችን ኃይላችን ተስፋችን እርስዋ በመሆንዋ ከእርስዋም ምን ጊዜም ቢሆን አንራቅ በምንም አንለይ፡፡

ቅዱስ ፊሊጶስ ሔነሪ የተባው ጻድቅ «ጌታ ሆይ ፊሊጶስ ላይ እጅህን ካላደረክ ሊክድህ ነው´ ይል ነበር። የእግዚአብሔር እጅ ካልደገፈችን እንዳንወድቅ መፍራት አለብን፡፡ ያለ እርስዋ መልካም ሥራ መሥራት አንችልም፡፡ ስንፍናችንንና ድከማችንን አውቀን ወደዚህች እጅ እንጠጋ፣ በአርስዋ እንመራ ፈጽመን አንሳሳትም አንወድቅምም፡፡

22 July 2020, 10:36