ፈልግ

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ 

የቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ ተፍጥሮአዊ ሁኔታ

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ

ክፍል ዐስራ ዘጠኝ

 በእምነት ብርሃን የበራ እውቀት

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማህበራዊ አስተምህሮ መጀመሪያ ላይ የቤተክርስቲያኗ አስተምህሮ አንድ አካል ተድርጎ አልታሰበም ወይም አልተቆጠረም ነበር፣ ነገር ግን ከጊዜ በኋላ በማህበራዊ ጉዳዮች ውስጥ በርካታ የቤተክርስቲያኗ አስተምህሮዎች እና ጣልቃ-ገብነቶች መፈጠር ጀመሩ። በዚህ መንገድ መገኘቱ ተፈጥሮው፣ ዘዴው እና የስነ-አዕምሮ አወቃቀር አንፃር አንዳንድ ለውጦች የተከናወኑ መሆናቸውን ለመረዳት የሚያስቸግረን አይሆንም። የቤተክርስቲያኗ ማኅበራዊ አስተምህሮ  “ርዕዮተ-ዓለም ሳይሆን የነገረ መለኮት አስተምህሮ እና በተለይም የሞራል ሥነ-መለኮት (መስክ) ነው” (John Paul II, Encyclical Letter Sollicitudo Rei Socialis, 41: AAS 80 (1988), 571)። የቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ በማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ መለኪያዎች መሠረት ቢቻ ሊገለፅ አይችልም። የቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ግንኙነቶችን ለመግለጽ እና ለማመንጨት እና ለማፍራት የታቀደ ርዕዮተ-ዓለም ወይም ስልታዊ ስርዓት አይደለም፣ ነገር ግን ለእራሱ አንድ ምድብ ነው፣ የቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ በሰው ልጅ ሕብረተሰብ ውስጥ ባሉ ውስብስብ እውነታዎች ላይ ፣ በማኅበረሰቡ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በእምነት እና በቤተክርስቲያኗ ባህል መሠረት በጥንቃቄ በማሰላሰል ውጤቱ ትክክለኛ እንዲሆን የሚያደርግ አስተምህሮ ነው። ዋናው ዓላማው በሰው እና በጥሪው ላይ፣ የሰው ልጅ ምድራዊ ተግባሩን እና ከእዚያም በኋላ ሰለሚከተለው ሰማያዊ ሕይወቱ ከግምት ባስገባ መልኩ ሕይወቱ ከወንጌል ትምህርት መስመሮቻቸው ጋር ተመሳሳይ መሆን ወይም ተመጣጣኝ መሆኑን መወሰን ወይም ለማሻሻል እነዚህን እውነታዎች መተርጎም ነው። ዓላማውም የክርስቲያናዊ ባህሪን ለመምራት ነው ”።

በመሆኑም የቤተክርስቲያኗ ማህበራዊ አስተምህሮ “የሰዎችን ባህርይ ለመምራት የሚያገለግል ትምህርት ስለሆነ” ሥነ-መለኮታዊ ተፈጥሮ አለው። “ይህ ትምህርት የሚገኘው ክርስቲያናዊ ሕይወትና ህሊና ከእውነተኛው ዓለም ጋር በሚገናኝባቸው መሸጋግሮች ላይ ነው። የቤተክርስቲያኗ ማህበራዊ አስተምህሮ “በግለሰቦች ፣ በቤተሰቦች ፣ በባህላዊ እና በማህበራዊ ሕይወት ውስጥ የተሳተፉ ግለሰቦች እንዲሁም በፖለቲካ ውስጥ ያሉ እና የታሪክ ሂደት በታሪክ ውስጥ ተጨባጭ ቅርፅ እና አተገባበር ለመስጠት ጥረት ሲያደርግ ታይቷል ” (John Paul II, Encyclical Letter Centesimus Annus, 59: AAS 83 (1991), 864-865)። በእርግጥ ይህ ማህበራዊ አስተምህሮ ሦስት ደረጃዎች ያሉት ሥነ-መለኮታዊ እና ሥነ-ምግባራዊ ትምህርትን ያንፀባርቃል፣ እነዚህም የመሰረታዊ ተነሳሽነት ደረጃ፣ በኅብረተሰቡ ውስጥ ያሉ የሕይወት መመሪያዎች መመሪያ ደረጃ፣ ተጨባጭ እና ልዩ ማህበራዊ ሁኔታዎች ውስጥ ዓላማና አጠቃላይ ደንቦችን ለማስታረቅ የሚጥር የሕሊና ደረጃ የተሰኙት ናቸው። እነዚህ ሶስት እርከኖች በትክክል የቤተክርስቲያኗን ማህበራዊ አስተምህሮዎች ትክክለኛ ዘዴ እና ልዩ አወቃቀር በግልጽ ያብራራሉ።የቤተክርስቲያኗ ማህበራዊ አስተምህሮ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ መገለጥ እና በቤተክርስቲያኗ ባህል ውስጥ ይገኛል። ከላይ ከሚመጣው ከዚህ ምንጭ የሰውን ተሞክሮ እና ታሪክ ለመረዳት ፣ ለመፍረድ እና ለመምራት የሚረዳ መነሳሳትን እና ብርሃንን ይስባል። ከምንም ነገር በላይ እና ከምንም ነገር በፊት እግዚአብሔር ለፈጠረው ዓለም እና በተለይም በቅድስት ሥላሴ ህብረት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆን ለተጠራው የሰው ልጅ ሕይወት እና ዕጣ ፈንታ ከእግዚአብሔር የተሰጠ የማዳን እቅድ ነው።

መለኮታዊውን ቃል የሚቀበል እና በተግባር ላይ የሚያውል እምነት ከአስተሳሰቡ ጋር በትክክል እንዲሰራ ለማደረግ ይችላል ማለት ነው። የእምነት መረዳትን በተለይም ተግባራዊ እርምጃን የሚወስድ እምነት በምክንያታዊነት የተዋቀረ ሲሆን ምክንያቱም ሊሰጥ የሚችለውን እያንዳንዱን አስተዋፅኦ ይጠቀማል። ማህበራዊ አስተምህሮ እንዲሁ ለታሪካዊ ገጽታዎች ጥቅም ላይ የሚውል እውቀት ስለሆነ የዚያ የበለጸገ ግንኙነት መገለጫ ነው።

እምነት እና ምክንያት የቤተክርስቲያን ማህበራዊ አስተምህሮን ሁለት የእውቀት ጎዳናዎችን ይወክላሉ እነዚህም የክርስቲያን ራዕይና የሰዎች ተፈጥሮ የተሰኙት ናቸው። በእምነት የበለጸገ “እውቀት” የሰው ልጆችን ህይወትን ይገነዘባል እንዲሁም ወደ ታሪካዊ የማዳን ምስጢር፣ እግዚአብሔር መገለጥ እና በክርስቶስ ለእኛ ወደ ተሰጠን ስጦታ ይመራል። ይህ የእምነት መረዳት ምክንያቱን ያጠቃልላል ፣ በዚህ መንገድም - በተቻለ መጠን - ይገለጣል፣ ይረዳል፣ በፍጥረት ውስጥ ከተገለጠው መለኮታዊ ዕቅድ ከተገኘው ከሰው ተፈጥሮ እውነት ጋር ያዋህዳል። ይህ የሰው ልጅ መንፈሳዊና ሥጋዊ አካል በመሆን ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ፣ ከሌሎች ሰዎች እና ከሌሎች ፍጥረታት ጋር የሚጣመርበት መሠረታዊ እውነት ነው” (John Paul II, Encyclical Letter Veritatis Splendor, 13, 50, 79: AAS 85 (1993), 1143-1144, 1173-1174, 1197)።

በተጨማሪም በክርስቶስ ምስጢር ላይ ማተኮር የማመዛዘን ሚና አይዳከምም ወይም አያጠፋም፣ ስለሆነም የቤተክርስቲያኗን ማህበራዊ አስተምህሮ መሠረታዊ ትምህርት አይገታም፣ ስለሆነም ሁለንተናዊ ጠቀሜታ አለው ማለት ነው። የክርስቶስ ምስጢር የሰውን ምስጢር ያበራልና ፣ ለሰው ልጅ ክብር እና ለሚጠብቁት የሥነ ምግባር መስፈርቶች ሙሉ ትርጉም ይሰጣል። የቤተክርስቲያኗ ማህበራዊ አስተምህሮ በእምነት የእውቀት ብርሃን የበራ ነው፣ እናም እንደዚያው በተመሳሳይ መልኩም ለእውቀት ታላቅ አቅም መግለጫ ነው። እሱ የሚያረጋግጠውን እውነት እና የሚፈልገውን ግዴታዎች ለሁሉም ሰዎች ያብራራል ፣ ሊቀበል እና ለሁሉም ሊጋራ ይችላል።

አዘጋጅ እና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን 

27 July 2020, 11:47