ፈልግ

የቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ የቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ 

የቤተክርስቲያን መብቶች እና ግዴታዎች

የቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ

ክፍል ዐስራ ስምን

በማኅበራዊ ትምህርቷ አማካይነት ቤተክርስቲያን የምትሰጠው አስተምህሮ ዋና ዓላማው “የሰው ልጅ በደህንነት መንገድ ላይ እንዲጓዝ ለመርዳት ነው” (John Paul II, Encyclical Letter Centesimus Annus, 54: AAS 83 (1991), 860)።  ይህ የእርሷ የቤተክርስቲያኗ ዋና እና ብቸኛው ዓላማ ነው። ይህ ዓላማ የሌሎችን ተልእኮ ለመረበሽ ወይም የሌሎችን ተልዕኮ ለመውረር ያቀደ ሳይሆን የራሷን ዓላም ችላ ሳትል ይህን ዓላማ የሚያደናቅፉ ተግባራትን በማስወገድ ለሰው ልጆች ደህንነት የበኩሏን አስተዋጾ ታደርጋላች ማለት ነው። ይህ ተልእኮ ለቤተክርስቲያኗ መብት አጠቃላይ ቅርፅ ለመስጠት እንዲሁም በተመሳሳይ ጊዜ የራሷን ማህበራዊ አስተምህሮ የማጎልበት እና በእርሱ በሚፈጽሟቸው ሃላፊነቶች እና ተግባራት አማካይነት የራሷን ማህበራዊ ትስስር ለማጎልበት ኃላፊነቷን ለመወጣት ያገለግላል።

ቤተክርስትያን የሰው ልጆች አስተማሪ፣ የእምነት የእውነት መስካሪ ስትሆን ቀኖናዎችን ብቻ የምታስተምር ሳትሆን በሰው ተፈጥሮ እና በቅዱስ ወንጌል ውስጥ የሚገኙትን ስነምግባራትን ጭምር የማስተማር ኃላፊነት ተጥሎባታል። የቅዱስ ወንጌል ቃል ማሰማት ብቻ ሳይሆን መከበር እና ተግባራዊ መሆን እንደ ሚገባው ታስተምራላች ች። “እንግዲህ ይህን ቃሌን ሰምቶ በተግባር የሚያውል፣ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራን ብልኅ ሰው ይመስላል” (ማቴ 7፡24)። የባህሪ ወጥነት አንድ ሰው በእውነት ምን እንደሚያምን እና ከቤተክርስቲያኗ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ወይም በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ብቻ የተወሰነ አለመሆኑን ያሳያል፣ ስለሆነም ወንዶች እና ሴቶች በሙሉ የሕይወት ልምዳቸውን እና የሁሉንም ኃላፊነቶችን ሁኔታ የሚያካትት ነው። ሆኖም እነዚህ ኃላፊነቶች ዓለማዊ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን ርዕሰ ጉዳዩ የሰው ልጅ ነው፣ ይህም ማለት እግዚአብሔር የሚጠራው ሰው ፣ በቤተክርስቲያን በኩል በመዳን ስጦታው ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆን የተጠራው የሰው ልጅ ነው።

ወንዶች እና ሴቶች ለደህንነት ስጦታው በከፊል፣ ረቂቅ በሆነ መልኩ ወይም በቃላት በመግለጽ ብቻ ሳይሆን በሕይወታቸው በሙሉ - ህይወትን በሚገልፅ ማንኛውም ግንኙነት ውስጥ - ማንኛውንም ነገር ችላ ሳይሉ ያልተቀደሱ እና ዓለማዊ የሆኑ ነገሮችን አሽቀንጥሮ በመጣል ለደህንነት ስጦታው ምላሽ እንዲሰጡ ተጠርተዋል። በዚህ ምክንያት የቤተክርስቲያኗ ማህበራዊ አስተምህሮ ለእርሷ ለቤተክርስቲያኗ የተሰጣት ልዩ ስጦታ ወይም ጊዜያዊ የሆነ ወይም ጣልቃ ገብነት ሳይሆን በሕብረተሰቡ አውድ ውስጥ የቅዱስ ወንጌልን ነፃ አውጪ ቃል የማስተጋባት መብቷን ተጠቅማ በማስተጋባት በሰዎች ሥራ ውስጥ፣ በጉልበት ሥራ ፣ በንግድ ፣ በፋይናንስ ፣  በፖለቲካ ፣ በህግ ፣ በባህል ፣ በማህበራዊ ግንኙነቶች ውስጥ ሳይቀር ሥነ ምግባራዊ የሆኑ እሴቶች ተጠብቀው ይኖሩ ዘንድ ቅዱስ ወንጌልን የማስተማር መብት አላት።

ይህ የቤተክርስቲያኗ መብት በተመሳሳይ መልኩ ሥራ ነው፣ ምክንያቱም ለእራሷ እና ለክርስቶስ ያላትን ታማኝነት ሳትከዳ የቅዱስ ወንጌልን እሴቶች የማስረጽ ኃላፊነት ተጥሎባታልና ነው፣ በዚህ ረገድ ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ “ወንጌልን ባልሰብክ ወዮልኝ!” (1 ቆሮ 9፡16) በማለት ይናገራል። ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ራሱ የተናገረው ማስጠንቀቂያ በቤተክርስቲያን ሕሊና ውስጥ የግለሰቦችን ሕሊና የሚመሩትን ብቻ ሳይሆን ወደ ሕዝባዊ ተቋማት የሚወስዱትን ጭምር የሚጠይቅ የወንጌልን መንገድ ሁሉ እንዲራመድ ጥሪ በማድረግ በቤተክርስቲያኗ ህሊና ውስጥ ይገኛል። በሌላ በኩል  የክርስትና መልእክት በምድራዊ ሕልውናችን ላይ ብርሃን እንዲፈነጥቅ ማደረግ ለማይችለው ንጹህ ዓለማዊ ደህንነት ጋር በከፍተኛ ሁኔታ የተለያየ ነው።

ቅዱስ ወንጌል እና የእምነት በይፋ ጠቀሜታ ስላላቸው በዚህ ምክንያት የፍትሕ መጓደል በሚያስከትለው ብልሹ ውጤት ምክንያት ኃጢያት ሲፈጸም እያየች ቤተክርስቲያን ለማህበራዊ ጉዳዮች ግድየለሽ ሆና መቀጠል አትችልም (Paul VI, Apostolic Exhortation Evangelii Nuntiandi, 34: AAS 68 (1976), 28)። መሠረታዊ ሥርዓቶችን ፣ የማህበራዊ ስርዓትን የሚመለከቱትን ጨምሮ በማንኛውም ሰብዓዊ ጉዳዮች ወይም ነፍስን ለማዳን የሚፈለጉ እስከሆኑ ድረስ በማንኛውም ሰብዓዊ ጉዳዮች ላይ የራሷን ብያኔ ትሰጣላች ።

አቅራቢ እና አዘጋጅ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

 

21 July 2020, 09:44