ፈልግ

በሊቢያ የሚገኙ አፍሪካዊያን ስደተኞች በሊቢያ የሚገኙ አፍሪካዊያን ስደተኞች  

የወጣቶች ስደት እና በስደት ላይ የሚያጋጥማቸው ተግዳሮቶች

ክፍል ሦስት

የወጣቶች ስደት በአዎንታዊ ጎኑ ስንመለከት ቤተሰቦች ከድህነት አርንቋ ለማውጣት ወጣቶች የሚወስዱ እርምጃ ቢሆንም፣ በአሉታዊ ጎኖች ያመዝናሉ፥ ተሰደው በሚኖሩበት አገር ከሚደርስባቸው አሉታዊ ገጽታዎች መካከል ጥቅቶቹ የሚከተሉት ናቸው።

Ø በግለሰብ ደረጃ፣ ወጣት ስደተኞች ከሚያጋጥማቸው ተግዳሮቶች መካከል  ለስነ-ልቦናዊና፣ ለአካላዊ፣ ስሜታዊና ለአእምሮአዊ ችግሮች ያዳረጋሉ፣ በኢኮኖሚያዊ ዘርፊ እንድሁም፡  የሞራል ውድቀት ፣ የዕዳ ቀውስ ፣ የሥራ ጫናና፡ በተለይም  በቋንቋ ችግር ምክኛት የበለጠ ለችግር ይዳረጋሉ፣ በግለሰብ ደረጃ።

Ø የቤተሰብ ቀውስ፥ በቤተሰብ ውስጥ መከፋፈልን ያመጣል፡ ምክንያቱም ወጣቶች ትዳር ከመሰረቱ በኋላ ለስደት በሚዳረጉበት ወቅት ቤተሰብ ላይ መከፋፈል ይፈጥራል፣ በተለይም በትዳር ውስጥ ውዝግብ ይፈጥራል፣ እስከ መለያየት ሊያደርስ ይችላል፣ አልፎ ተርፎም ሕጻናትን ለአደጋ ያጋልጣል፣ ይህ በብዙ ቤተሰብ ውስጥ ትልቅ ፈተና ሆኖ የምታይ ሀቂ ነው፣ ምክንያቱም የቤተሰብ ኑሮ ለማሻሻል ሲባል የተወሰደ እርምጃ ቢሆንም በቤተሰብ መካከል ክፍተት ይፈጥራል። 

Ø ማህበራዊ ውህደት፥ ሰላማዊ ማህበራዊ ግንኙነቶችን ለማዳበር እና ለመጠበቅ ሁሉም አባላት በውይይት የሚሳተፉበት ተለዋዋጭ መዋቅራዊ ሂደት ነው። ማህበራዊ ውህደት ቁሳዊ የሆኑ ነገሮች በሚፈጥሩት ልዩነት፣ በራስ ወዳድነት፣ አግባብ ባልሆነ የደሞዝ ክፍያ ምክንያት ተገድቦ በኅብረተሰቡ አኗኗሪ ዘይቤ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል።

Ø በሐይማኖት ልዩነት፣ የሃይማኖትን ብዙሐነት በተመለከተ ትልቁ ፈታኝ ሁኔታ በክርስቲያኖች እና በሙስሊሞች መካከል ተጓዳኝ ጉዳይ ያሳድራል። ስደት ቀጣይነት ያለው ክስተት መሆኑ መርሳት የለብንም። ይህ ደግሞ በቤተክርስቲያንና በማህበረሰቡ ላይ ፈታኝ የሆኑ ሁኔታዎችን ያስከትላል። ስለዚህ የሃይማኖታዊ መለያዎች እንደ የሰዎች እምነትና አረዳድ ይለያል፣ ሐይማኖት የአንድ ሕዝብ መለያ እና ርዕዮተ ዓለም እየሆነ መጥተዋል። ስለሆነም በተለያዩ ምክኛቶች የተነሳ የገዛ አገራቸውን ጥለው የሚሰደዱ ሰዎች በየደረሱበት አገር ከእነርሱ የግል ሐይማኖት ጋር የሚመሳሰል እምነት ካላገኙ ለተለያዩ ጭንቀቶች ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ። በግለሰብ ደርጃ በእመነታቸው ላይ ጫና ይፈጥራል።

Ø ኢኮኖሚያዊ ፍላጎት፣ የሚያገኙት ኢኮኖሚያዊ የሆነ ገቢ የሰዎችን መሠረታዊ ፍላጎቶች የማያሟላ ከሆን መሰረታዊ የሚባሉ ነገሮች ለምሳሌም ምግብ እና ውሃ፣ መጠሊያ ያሉ ቁሳቁሶችን ሟሟላት ካልቻሉ ለሕሊና ድብርት ይዳረጋሉ።  ወጣቶች እንደ መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸው ሁሉ ለኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው ፡፡ ኢኮኖሚ ለሰው ልጆች እድገት መሰረታዊ ፍላጎቶች ፈር ቀዳጅ ነው። ይህንን ለማሳካት ደግሞ ያለምርጫቸው በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ በመግባት ራሳቸውን እና ሕይወታቸውን ለአደጋ ያጋልጣሉ።

Ø የባህል ልዩነት፣ የባህል ልዩነት በኅብረተሰቡ ውስጥ በአጠቃላይ ሲታይ እና ከተለያዩ ባህላዊ ባህሪዎች አንጻር ሲገመገም እንዲህ ዓይነቱ ልዩነት በተለምዶ በዘር፥ በብሔር ፣ በእድሜ ፣በጾታ፣ የሃይማኖት እና የባህል  ልዩነቶችን በስፋት ያገናዘበ ሊሆን ይችላል። “ስደት በባህል ልዩነት ውስጥ ትልቅ ሚና አለው”።

በአጠቃላይ የሀገራችን ገጽታ ስንመለከት፥ በሀገራችን ኢትዮጵያ ያሉ ከተሞች በጣም ጥቂቶች በመሆናቸው እንደምናውቀው በዓለም ውስጥ ካሉት ከተሞች ጋር ስናነጻጽር በቁጥር ትንሽ ናቸው፣ በመሆኑም 84 በመቶ የሚሆነው ሕዝቧቹዋ በገጠራማ አካባቢዎች የሚኖሩ ናቸው፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ የወጣቶች  እንቅስቃሴ ፍላጎት ወደ ከተማ ያመዝናል። ከእነዚህ ችግሮች ጋር በተያያዘ መልኩ ከፍተኛ የፖለቲካ፣ የማህበራዊና፣ የኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች በየጊዜው መልካቸውን እየቀያየሩ ተለዋዋጭ እየሆኑ በመከሰት ላይ የገኛሉ። ከዚህ የተነሳ የአገሪቷ ውስብስብ ድርጊቶች ውጤት ከአዎንታዊ ይልቅ አሉታዊ ጉዳይ ያመዝናል። በነዚህ ሁኔታዎች የተነሳ ወጣቶች የተለያዩ የስደት ስልቶችን እና ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን እንዲፈጥሩ አስችሏል።  በተለይም ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶች ይበልጥ ለወጣቶች ስደት የጎላ አስተዋጾ ያበረክታሉ።

19 June 2020, 12:53