ፈልግ

የአባ ራጊድ ጋኒ መካነ መቃብር በእስላማዊ ጽንፈኞች ከተደመሰሰ በኋላ፤ የአባ ራጊድ ጋኒ መካነ መቃብር በእስላማዊ ጽንፈኞች ከተደመሰሰ በኋላ፤ 

ኢራቅ በአሸባሪዎች እጅ የተገደሉትን ካህን፣ አባ ራጊድ ጋኒን አስታወሰች።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ሰኔ 3/2007 ዓ. ም. በእስላማዊ መንግሥት ታጣቂዎች እጅ የተገደሉት አባ ራጊድ ጋኒ ፣ በሞሱል ከተማ የመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያስን ቁምስና መሪ ካህን የነበሩ መሆናቸው ታውቋል። አባ ራጊድ ጋኒ በአሸናሪዎች እጅ የተገደሉት በቁምስናቸው የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎትን አሳርገው ሲወጡ እንደነበር ይታወሳል። አባ ራጊድ ጋኒ በኢራቅ ውስጥ በክርስቲያኖች ላይ ስቃይ እና ስደት ይደርስ በነበረበት ጊዜ መደበኛውን የቤተክርስቲያን አገልግሎታቸውን ሳያቋርጡ በመቆየታቸው በአሸባሪዎች እጅ በሰማዕትነት መገደላቸው ይታወሳል። ከአባ ራጊድ ጋኒ ጋር ሦስት ወጣት ዲያቆናት መገደላቸው ይታወሳል።

የቫቲካን ዜና፤

“የእግዚአብሔርን ቤት መዝጋት አልችልም”፣

አባ ራጊድ ጋኒ ከመገደላቸው በፊት በቤተክርስቲያናቸው የሚሰጡትን መንፈሳዊ አገልግሎቶች እንዲያቆሙ እና ቤተክርስቲያኑንም እንዲዘጉ መጠየቃቸው ይታወሳል። አባ ራጊድ ጋኒ ግን አሻፈረኝ ብለው “የእግዚአብሔርን ቤት መዝጋት አልችልም” ብለው መመለሳቸው ይታወሳል። በኢራቅ ውስጥ አሸባሪዎች የሚፈጽሙትን አሰቃቂ ግድያ እና ስቃይን አምልጠው የሸሹ ክርስቲያን ወጣቶች እና ቤተሰቦች ቁጥር ብዙ መሆኑ ይታወቃል። አባ ራጊድ ጋኒ በአሸባሪዎች ከመገደላቸው አስቀድመው በነበሩ ጊዜያት እንደተናገሩት፣ ሁሉ ነገር ሰላም እና ጸጥታ በሆነበት ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ የሰጠንን ውድ ስጦታን እንዘነጋለን ብለው፣ በአመጽ፣ በጦርነት እና በሽብር ወቅት ለኛ ሲል ተሰቃይቶ በሞተው እና ከሞት በተነሳው ኢየሱስ ክርስቶስ ስጋ እና ደም የዘለዓለም ሕይወት እንደምናገኝ፣ የሚደርስብንን መከራ እና ስቃይ ችለን ተስፋን እናደርጋለን ማለታቸው ይታወሳል።

ለብጽዕና የሚያበቃ ጥናት በ2019 ዓ. ም. ተጠናቋል፤

አባ ራጊድ ጋኒ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ጥር 20/1972 ዓ. ም. በኢራቅ ውስጥ ካርምሌሽ በሚባል ሥፍራ ተወልደው የከፍተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በባግዳድ ውስጥ በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ከተከታተሉ በኋላ በምንድስና ሞያ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ1993 ዓ. ም. የተመረቁ መሆናቸው ታውቋል። ከ1996-2003 ዓ. ም. ሮም በሚገኝ ቅዱስ ቶማስ አኲናስ ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ፣ የስነ መለኮት ትምህርታቸውን ተከታትለው በአብያተ ክርስቲያናት አንድነት የትምህርት ዘርፍ ድግሪ መቀበላቸው ታውቋል። ከአረብኛ ቋንቋ በተጨማሪ ጣሊያንኛን፣ ፈረንሳይኛን እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎችን በሚገባ የሚናግሩ መሆኑ ታውቋል። አባ ራጊድ ጋኒ ከክህነት አገልግሎት በተጨማሪ ኤዢያ ኒውስ ለተባለ የውጭ አገር ተልዕኮ ጳጳሳዊ የመገናኛ ተቋም ዘጋቢ ሆነው ማገልገላቸው ታውቋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ሚያዝያ 22/2017 ዓ. ም. አዳዲስ ሰማዕታትን ለማስታወስ፣ ሮም በሚገኘው በቅዱስ ቤርቶለመዎስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ባሳረጉት የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ላይ የአባ ራጊድ ጋኒ የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት አልባሳት መልበሳቸው ይታወሳል። እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ2018 ዓ. ም. የቅድስና ማስረጃ ምክንያቶች አጥኚ ጳጳስዊ ምክር ቤት የአባ ራጊድ ጋኒ የሕይወት ታሪክ መጠናት እንዲጀመር ትዕዛዝ መቀረቡ ይታወሳል።

የግድያ ሙከራ ቢደረግባቸውም የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎትን ቀጥለውበታል፤

አባ ራጊድ በእርግጥ የቅዱስ ቁርባን ሰማዕት ናቸው ያሉት የአባ ራጊድ ጋኒ የአብያት ክርስቲያናት ኅብረት ሰነ መለኮት ተማሪ የሆኑት ክቡር አባ ረቧር ባሳ፣ የአባ ራጊድ ጋኒ እረፍት አሥረኛ ዓመት መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ ባሳተሙት መጽሐፋቸው “አባ ራጊድ ጋኒ፣ በእስላማዊ መንግሥት ከሚተዳደር አገር የተገኙ ካቶሊካዊ ካህን” በማለት መግለጻቸው ይታወሳል። የአባ ራጊድ ጋኒ መካነ መቃብር በእስላማዊ ጽንፈኞች ከተደመሰሰ በኋላ እንደገና መገንባቱ ታውቋል። አባ ራጊድ ጋኒን “የቅዱስ ቁርባን ሰማዕት” ብለን ልንጠራቸው እንችላለን ያሉት አባ ረቧር፣ ቅዱስ ቁርባን የክርስቲያን ሕይወት ማዕከል ነው ብለው፣ በተለይም በካህን ህይወት ውስጥ ማዕከላዊ ሥፍራ የሚሰጠው ነው ብለዋል። “አባ ራጊድ ይህን በተግባር ያስመሰከሩ፣ ሕይወታቸው በአደጋ ውስጥ በነበረበት ጊዜ በድፍረት የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ሲያሳርጉ የነበሩ፣ ቆራጥ ካህን ናቸው” በማለት አስረድተዋል። ብዙን ጊዜ አደጋ የተጣለበት ቤተክርስቲያናቸው ወይም ቁምስናቸው፣ የሚወዷቸውን የቤተሰብ አባላት እና የቁምስናው ምዕመናን በአሸባሪዎች እጅ የተገደለበት ነው ብለው፣ አባ ራጊድ በአስቸጋሪ ጊዜም ቢሆን ሳያቋርጡ የመስዋዕተ ቅዳሴን ጸሎት ሲያቀርቡ የነበሩ፣ ያለ ቅዱስ ቁርባን ሕይወት እንደሌለ፣ ለአንድ ክርስቲያን ያለ ቅዱስ ቁርባን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እና ከመላዋ ቤተክርስቲያ ጋር ኅብረት እንደሌለው ያስገነዘቡ ካህን ነበሩ በማለት ገልጸዋል።  

ክቡር አባ ረቧር ባሳ ማብራሪያቸውን በመቀጠል እንዳስረዱት፣ አባ ራጊድ ጋኒን የምናውቃቸው፣ የባግዳድ ቤተክርስቲያን እና የኢራቅ ሕዝብ በሙሉ መሆኑን ገልጸው ለአባ ራጊድ ጋኒ ካሳ መክፈል ይኖርብናል ብለዋል። አባ ራጊድ ጋኒ ሕይወታቸውን ለሞት አሳልፈው እስከ መስጠት ድረስ ኢራቅን ከልብ የወደዱ አባት ነበሩ በማለት ገልጿቸዋል። ለአባ ራጊድ ጋኒ ምስጋናችንን እያቀረብን፣ ምሳሌነታቸውን ለመከተል የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን ብለው፣ አባ ራጊድ የእውነተኛ ክርስቲያን እና የቤተክርስቲያን አገልጋይ ነበሩ ብለው፣ “ሕይወትን እንዴት አሳልፎ መስጠት እንደሚገባ፣ ጠላትንም እንዴት መውደድ እንደሚገባ፣ ለሰው ልጅ መብት እንዴት መታገል እንደሚገባ፣ ለድሆች እና ለተጨቆኑት እንዴት መቆም እንደሚገባ እና እርዳታን የሚፈልጉትን እንዴት መርዳት እንደሚገባ ያስተማሩን የቤተክርስቲያን አገልጋይ ነበሩ” በማለት አስረድተዋል።  

09 June 2020, 17:14