ፈልግ

ኢየሱስ የወይን ኝድ ነው ኢየሱስ የወይን ኝድ ነው 

ክፉዎች የወይን አትክልት ጠባቂዎች

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሙሴ ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን የሚከተለውን ምሳሌ አሰማቸው፡፡ «ልብ አድርጉ አስተውሉ አንደ የቤተሰብ አስተዳዳሪ አባት በእርሻው የወይን አትክልት ተከለ፡፡ አጥሮ መጠበቂያ ጐጆ ከላይ ሠርቶ እንዲጠብቁ ለጠባቂዎች ሰጣቸው ይህን የአደራ ጥበቃ ካመቻቸ በኋላ ወደ ሩቅ አገር ሄደ፡፡ የአዝመራው ጊዜው ሲደርስ የወይን ፍሬ እንዲያመጡለት አገልጋዮችን ላከ፡፡ ጠባቂዎች ግን ሲጡ ባዩዋቸው ጊዜ ይዘው አንዱን በዱላ ደበደቡት፣ ሌላውን ወግረው ገደሉት፣ ሶስተኛውን አቁስለው ተውት፡፡ ጌትየው ተስፋ ሳይቆርጥ እንደገና ከፊተኞቹ ጠንከር ያሉ ሌሎች አገልጋዮች ላከ፣ አሁንም የላኩትን አገልጋዮች ተቀብለው ፊተኞቹን እንዳደረጉ ሁሉ አደረጉአቸው፡፡ በመጨረሻም የእርሻው ባለቤት «ልጄንስ አይነኩትም ይፈሩት ይሆናል´ ብሎ አንዲያ ልጁን ላከባቸው እነርሱ ግን ከሩቅ ሲመጣ ባዩት ጊዜ «እነሆ የወይን አትክልት እርሻ ወራሽ ልጁ መጣ ኑ እንግደለው ርስቱም ለእኛ ይሆናል´ አሉ፡፡ ይዘውም ከአትክልት ቦታ ውጭ አውጠተው ወግረው ገደሉት፡፡ «የወይን አትክልቱ እርሻ ጌታ ሲመለስ የአትክልቱን ጠባቂዎች ምን ያደርጋቸዋል;´ በማለት ኢየሱስ ጠየቃቸው፡፡

እነርሱም «ክፉዎችን በክፋታቸው አጥፍቶ የወይን አትክልቱን የአዝመራ ፍሬ በወቅቱ ለሚሰጡት ለሌሎች ሊያከራይ ይገባል´ ብለው መለሱለት፡፡ ኢየሱስለ ከዚህ ጋር አያይዞ «እንግዲህ ለእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ወስዶ ለሌሎች በጊዜው ፍሬ ለሚሰጡ ሕዝቦች ሊሰጥ ይገባል´ (ማቴ. 21፣43 ) አላቸው፡፡ ይህ ምሳሌ የአይሁዳውያን ተቃራኒ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ የአይሁዳውያን መሪዎች (ፊሪሳውያን የሙሴ ሕግ መምህራን ጻፎች) የነበረ ነው፡፡ እነርሱም ታወቅቸውና ኢየሱስን ሊይዙት ሞክረው ሕዝቡን ፈሩና ተውት፡፡ የወይን አትክልት ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ የወይኑ አትክልት ቦታ ደግሞ የእግዜአብሔር መንግሥት ነው፣ እነዚያ ክፉ ጠባቂዎች አይሁዳውያን ናቸው፣ መልአክተኞች ነቢያት ናቸው፡፡

06 May 2020, 14:04