ፈልግ

በጣሊያን ውስጥ ቤተክርስቲያኖች ለመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ክፍት ተደርገዋል፣ በጣሊያን ውስጥ ቤተክርስቲያኖች ለመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ክፍት ተደርገዋል፣ 

በጣሊያን ቤተክርስቲያኖች ለመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ክፍት መደረጋቸው ተገለጸ።

የጣሊያን ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳ ጉባኤ፣ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አስቸኳይ ጊዜ ሁለተኛ ዙር እቅድን አስመልክቶ ከመንግሥት ጋር ባደረገው ስምምነት መሠረት ከሰኞች ግንቦት 10/2012 ዓ. ም. ጀምሮ ቤተክርስቲያኖች ለመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ክፍት የተደረጉ መሆናቸው ታውቋል። በመስዋዕተ ቅዳሴው ጸሎት ሥነ ሥርዓት ላይ የሚገኙ ምዕመናን ከመንግሥት የወጣውን ደንብ እንዲያከብሩ ትዕዛዝ መተላለፉ ታውቋል።

የቫቲካን ዜና፤

በቫቲካን የሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ጨምሮ በአገሪቱ የሚገኙ ቤተክርስቲያናት በሙሉ ከሰኞ ግንቦት 10/2012 ዓ. ም. ጀምሮ ዕለታዊውን የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ሥነ ሥርዓት መጀመራቸው ታውቋል። ማኅበራዊ ርቀት መጠበቅ፣ ጭንብልን ማጥለቅ እና ንጽሕናን መጠበቅ በሁለተኛውም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጥንቃቄ ወቅት እንዲከበሩ በማለት በመንግሥት እና በጣሊያን ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳ ጉባኤ መካከል ስምምነት የተደረገ መሆኑ ታውቋል።

ቁምሳናዎች የሚገኙባቸው ሁኔታ፣

በጣሊያን መዲና ሮም በሚገኙት ቁምስናዎች ምዕመናን ጠዋት በሚደረጉ የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ላይ መካፈል መጀመራቸው ሲታወቅ፣ በቁጥር በርካታ ምዕመናን የሚገኙበት ከሰዓት በኋላ የሚቀርብ የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ላይ መሆኑ ታውቋል። ምዕመናን በቤታቸው እንዲቆዩ በታዘዙባቸው ሳምንታት የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ሥነ ሥርዓት በማኅበራዊ ሚዲያዎች በኩል እንዲሳተፉ የተደረገ ቢሆንም በርካታ ምዕመናን ቅዱስ ቁርባንን መቀበል ሳይችሉ መቅረታቸው ቅር እንዳሰኛው ገልጸዋል። በሰሜን ጣሊያን፣ ሚላኖ ከተማ በሚገኝ የልደተ ማርያም ካቴድራል ለምዕመናን ክፍት የተደረገ ሲሆን፣ የካቴድራሉ ሊቀ ካህን የሆኑት ብጹዕ አቡነ ጃናንቶኒዮ ቦርጎኖቮ፣ በመስዋዕተ ቅዳሴው ጸሎት ላይ ለተገኙት ምዕመናን ባደረጉት ንግግር፣ ካቴድራሉ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከተዘጋ ከሳምንታት በኋላ በመከፈቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ለምዕመናኑም መልካም አቀባበል አድርገውላቸዋል። በደቡብ ጣልያን ናፖሊ ከተማ በሚገኝ በቅዱስ ኒኮላ ቤተክርስቲያንም ምዕመናን ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት ጸሎታቸውን ያቀረቡ መሆኑ ታውቋል።

ተግባራዊ የሚሆኑ ስምምነቶች፣

የሁለተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አስቸኳይ ጊዜ ደንብ አስመልክቶ በጣሊያን መንግሥት እና በሀገሪቱ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳ ጉባኤ መካከል በተደረገው ስምምነት መሠረት፣ ምዕመናን በርከት ብለው በሚሰበሰቡባቸው ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ማኅበራዊ ርቀትን እንዲጠብቁ፣ ጭንብልን ማጥለቅ እና የእጅ ንጽሕናን እንዲጠብቁ የተደረገ መሆኑ ታውቋል። ስምምነቱ በተጨማሪ ምዕመናን ከሥነ ሥርዓት አስከባሪዎች የሚነገራቸውን ትዕዛዝ ተቀብለው ተግባራዊ እንዲያደርጉ፣ የጉንፋን ስሜት ወይም የትኩሳት መጠን ጨምሮ የተገኘ ከሆነ ከቤት መውጣት እንደ ሌለባቸው፣ የመስዋዕተ ቅዳሴን ጸሎት የሚካፈሉ ምዕመናን ብዛት መቀነስ፣ ቅዱስ ቁርባንን ምዕመናን በተቀመጡበት ሥፍራ ወስዶ ማደል እንደሚያስፈልግ፣ ካህን ጭንብል በማጥለቅ፣ የእጅ ንጽሕና በመጠበቅ ቅዱስ ቁርባንን በምዕመና እጅ ላይ በማስቀመጥ ለማደል ስምምነት ላይ መደረሱ ታውቋል።    

20 May 2020, 17:07