ፈልግ

ለምድራችን የምናደርገውን እንክብካቤ ከሌሎች የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ጋር በጋራ እናከናውን! ለምድራችን የምናደርገውን እንክብካቤ ከሌሎች የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ጋር በጋራ እናከናውን! 

ለምድራችን የምናደርገውን እንክብካቤ ከሌሎች የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ጋር በጋራ እናከናውን!

 “laudato si” በአማረኛው ውዳሴ ለአንተ ይሁን በሚል አርዕስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እ.አ.አ በግንቦት 24/2012 ዓ.ም ለንባብ ያበቁ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ይፋ የሆነበት 5ኛው ዓመት ባለፈው ግንቦት 16/2011 ዓ.ም ተዘከሮ አልፉዋል። በዚህ ሐዋርያዊ መልእክታቸው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “የጋራ መኖሪያ ቤታችን የሆነችውን ምድራችንን እንከባከብ” በሚል ጭብጥ ዙሪያ ላይ የዛሬ 5 አመት ገደማ ያፋ ያደርጉት ሐዋርያዊ መልእክት ሲሆን በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ በዓለማችን ላይ የሚታየው የአየር ንብረት ለውጥ መንስሄ ምድራችንን ያለ አጋቡ በመበዝበብዛችን፣ ከባቢ አየርን ሊበክሉ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችን፣ ጋዞችን ወደ አከባቢ በመልቀቃችን በመሳሰሉ ጉዳዮች የተከሰተ እና የጋራ የመኖርያ ቤታችንን አደጋ ላይ የጣለ ክስተት በመሆኑ ክስተቱን ለመግታት ባለድርሻ አካላት የራስቸውን ሚና መጫወት ይገባቸዋል የሚል ጭብጥ ያለው ሐዋርያዊ መልእክት እንደ ሆነ ይታወሳል።

የቫቲካን ዜና

ለጋራ የመኖሪያ ቤታችን እንራራላት

ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጋር በጋር በመሆን፣ እንዲሁም ከሌሎች የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት እና የክርስቲያን ማሕበረሰቦች አጋርነት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን “ለተፈጥሮ እንክብካቤ ይደረግ ዘንድ ዓለማቀፍ የጸሎት ቀን ታከብራለች”። በዚህ ወቅት “አማኝ ግለሰቦች እና የማኅበረሰብ ክፍሎች እያንዳንዳቸው ተፈጥሮን የመንከባከብ ጥሪያቸውን በድጋሚ የሚያድሱበትን አጋጣሚ በመጠቀም፣ የዚህን ድንቅ የሆነ ተፈጥሮ፣ እንድንከባከበው በአደራ ያስረከበንን እግዚኣብሔርን እንድናመሰግነው እና በቀጣይነትም ይህንን ተፈጥሮ ለመንከባከብ እንድንችል ይረዳን ዘንድ፣ በተጨማሪም በምንኖርባት ዓለም ላይ ላደረስነው ውድመት ይቅርታን እንድንለምነው” ይህ ወቅት አጋጣሚውን ፈጥሮልናል።

አብያት ክርስቲያናት እና የክርስቲያን ማኅበረሰብ እንዲሁም የሌላ እምነት ተከታዮች ለገጸ-ምድራችን የወደ ፊት እጣ ፋንታ መጠበብ መጀመራቸው አበረታች ነገር ነው። በእርግ ባለፉት አስርተ-ዓመታት የሐይማኖት መሪዎች እና ልዩ ልዩ ተቋማት በምድራችን ላይ እየተከሰት የሚገኘውን ኋላፊነት የጎደለው ብዝበዛ ለብዙኋኑ አጋልጠው እንደ ነበረ ይታወሳል። በእዚህም ረገድ የቁስጥንጥንያው ፓትሪያርክ በርተሌሜዎስ ከእርሳቸው ቀደም ብለው የነበሩትን የፓትሪያርክ ዲሚትሪን ፈለግ በመከተል በተፈጥሮ ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ሐሳሳቢ ውድመት ኋጥያት መሆኑን እና ይህም በአከባቢ ላይ እየደረሰ የሚገኘው ውድመት ሞራላዊ እና መንፈሳዊ ሥር መሰረቶችን እንደ ምያቃውስ መገለጻቸው ይታወቃል። ከተፈጥሮ ጋር ያለን ውህደት እዲጨምር እንዲሁም የአደጋው አሳሳቢነትን ለማጉላት በማሰብ በሮማኒያ በሲቢው ከተማ 2007 ዓ.ም የተካሄደው ሦስተኛው የአውሮፓ አብያተ-ክራስቲያንት የውይይት ጉባሄ ከመስከረም 1 ጀምሮ ባሉ አምስት ሳምንታት ውስጥ እንዲከበረ በመወሰኑ በተለይም ደግሞ በመስከረም 1 የኦርቶዶክስ አብያተ-ክርስቲያናት አምላክ የፈጠራቸውን ፍጥረታትን የሚያስቡበት ቀን በመሆኑ እና በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቅጣጠር በጥቅምት 4 የሚከበረው የቅዱስ ፍራንቸስኮ በዓልን ምክንያት በምድረግ የመስከረም ወር ለየት ባለ ሁኔታ ለተፈጥሮ እንክብካቤ በማደረግ ይከበራል።  ሦስተኛው የአውሮፓ አብያተ-ክራስቲያንት የውይይት ጉባሄ በቀጥይነትም በተፈጥሮ እንክብካቤ ዙሪያ ብዙ ሐሳቦች እንዲነሱ ምክንያት ሆኖኋል። በእዚህም ሳቢያ በዓለማችን በእዚሁ ጉዳይ ዙሪያ የተለያዩ ሥራዎች እንዲከናወኑ መንስሄ ከመሆኑም ባሻገር ፍታዊ የሆነ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም እዲኖር፣ ለድሆች ትኩረት እንዲሰጥ፣ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል ኃላፊነት ተሰምቶት በተለይም ደግሞ የተለያዩ ሐይማኖት ተከታይ የሆነው የወጣቱ ትወልድ በአንድነት በእዚህ ጉዳይ ላይ እንዲረባረብ ያነሳሳ ነው። ክርስቲያኖች ይሁኑ ክርስቲያን ያልሆኑ በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎችም ጭምር የጋራ መጠልያ ቤታችን ለሆነችው ምድራችን ርኅራኄን እንዲያሳዩ እና የጋራ መኖሪ ቤታችን የሆነችውን ምድራችንን መንከባከብ ይኖርብናል።

1.     ምድራችን በልቅሶ ላይ ናት

በዚህ መልዕክቴ ቀደም ሲል ያደረኩትን ንግግር በድጋሜ በማስታወስ “በዚህ ምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በመከራ ውስጥ የሚገኙ ድሆችን እና በአከባቢ ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ውድመት በድጋሜ ማስታወስ እፈልጋለሁኝ”። እግዚኣብሔር የተትረፈረፈ የአትክልት ሥፍራን ሰጠን ነገር ግን እኛ ወደ በረሃማነት እና የትርኪሚርኪ መጣያ፣ ወደ ተበከለ የቆሻሻ መጣያ ሥፍራነት ቀየርናት”። በምድራችን ስነ-ምዕዳር እና የተመጋጋቢነት ሂደት ላይ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ እና በእራስ ወዳድነት መንፈስ እየደረሰ የሚገኘውን ውድመት በግድየለሽነት ስሜት ወይም በዝምታ መመልከት አይኖርብንም። “ምክንያቱም በሺዎች የሚቆጠሩ ዝርያዎች እየጠፉ በሚመጡበት ወቅት በመኖራቸው ምክንያት እነርሱን በማየት ለፈጣሪ የምንሰጠው ምስጋና እየቀነሰ ስለ ሚመጣ እና ይህንን የማድረግ መብትም ስለሌለን ጭምር ነው።

የሰው ልጆች በምያደርጉ እንቅስቃሴ ምክንያት የአለም ሙቀት መጨመሩ ይቀጥላል፣ ባሳለፍነው 2015 ዓ.ም የነበረው የዓለማችን ሙቀት እስካሁን ከተመዘገቡት ሁሉ በጣም የላቀ ሲሆን በ2016 ዓ.ም ይህ ነገር በቀጣይነት እንደ ሚከሰት እሙን ነው። ይህም ጉዳይ በዓለማችን ድርቅ፣ ጎርፍ፣ እሳት እና ያልተለመደ የአየር ንብረት ለውጥ እዲኖር እያደረገ ይገኛል። የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ለስደተኞች ፍሰት ቀውስ ከፍተኛ የሆነ ድርሻ አበርክቱኋል። በዓለም ውስጥ የሚኖሩ ድሆች ኃላፊነት በማይሰማቸው ሰዎች አማካይነት ድህነት ከደቀንባቸው መከራ ባሻገር በአለም የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ከድጥ ወደ ማጡ እየወረዱ ይገኛሉ።

 የተመጣጠን የስነ-ምዕዳር ሂደት እንደ ምያሳየው የሰው ልጆ ከተፈጥሮ ጋር ጥብቅ የሆነ ግንኙነት እንዳላቸው ነው። ስለዚህም ተፈጥሮን መበደል ማለት የሰው ልጆችን መበደል ማለት ነው። በተመሳሳይ መልኩ እያንዳንዱ ፍጥረት የራሱ የሆነ ተፈጥሯዊ እሴቶች አሉት ይህም ሊከበር ይገባዋል። “ምድራችን እና ድሆች እያሰሙ የሚገኙትን ለቅሶ ችላ አንበል” ተገቢ እና ወቅታዊ ምላሽ እንዲገኝ የተቻለንን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል።

2.     . . .እኛ ኃጥያትን ስለ ሠራን

እግዚአብሔር ለእኛ ምድርን የሰጠን ተመጣጣኝ በሆነ መልኩ “እንድናለማት እና እንድንከባከባት ነው” (ዘፍጥረት 2፡1)። ከመጠን በላይ መጠቀም እና በጣም አንሰተኛ በሚባል መልኩ መንከባከብ ኃጥአት ነው።

ወንድሜ ፓትሪያርክ በርቴሌመዎስ ብርታት በተሞላው መልኩ በተፈጥሮ ላይ እየፈጸምነው የምንገኘውን ኃጥያት ተንብየው ነበር።  አሁን በጋራ የመኖሪያ ቤታችን ላይ እየተከሰተ ካለው እውነታ በመነሳት በተለይም ደግሞ በምስጢረ ንስሐ አማካይነት “ውስጣዊ የሆነ ለውጥ ማምጣት ይኖርባናል።  በተፈጥሮ ላይ ያደረስነውን ጥፋት ተገንዝበን ይቅርታን የምንጠይቅበት ወቅት ሊሆን ይገባል። እንዲሁም ይህንን ሁኔታ ለመለወጥ ተጨባጭ እርምጃዎችን መውሰድ እንድያስችለን እስቲ ራሳችንን እንመልከት፣ ምክንያቱም ለስነ-ምዕዳር የምናደርገው አስተዋጾን በግልጽ በማወቅ  ለራሳችን፣ ለጎረቤቶቻችን፣ ለተፈጥሮ እና ለፈጣሪ ማሳየት የሚገባንን ኃላፊነት ማወቅ ያስፈልጋል።

3.     ሕሊናችንን መመርመር እና መጸጸት

ለዚህ ችግር ቀዳሚ የሆነ መፍትሄን ለማምጣት እንዲያስችለን በቅድሚያ “ማመስገን እንድንችል፣ ዓለማችን የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑዋን መረዳት እንድንችል እንዲሁም በጽሞና የእርሱን መልካምነትን በመላበስ በመልካም ሥራችን ራሳችንን መስዋዕት ማድረግ እንድንችል፣ በቅድሚያ እራስን መመርመር ያስፈልጋል። ጠንከር ያለ የሕሊና ምርመራ ካደረግን ቡኋላ በፈጣሪ፣ በፍጥረት፣ እንዲሁም በወንድም እና ሕህቶቻችን ላይ ባደረስነው ጥፋት ተጸጽተን ንስኋ መግባት ያስፈልጋል። “ንስኋን አስመልክቶ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ  እንዳስቀመጠው እውነት ነጻ ያወጣችኋል” “እግዚአብሔር ከኋጥያታችን በላይ ነው” ይለናል፣ስለሆነም በተፈጥሮ ላይ ላደረስነው በደል ይቅር ይለናል”።

4.     አካሄዳችንን ማስተካከል

ሕሊናን መመርመር፣መጸጸት እንዲሁም ኃጥያታችን በምሕረት ለተሞላው እግዚአብሔር መናዘዝ ወደ አንድ መሻሻልን ማምጣት ወደ ምያስችለን አንድ ዓላም ይመራናል። ይህም ዓላማ ተፈጥሮን ማክበር ወደ ምያስችለን ተጨባጭ ሐሳብ እና ተግባር ሊተረጎም ይገባል። ለምሳሌም “ፕላሲቲክ ነክ የሆኑ ነገሮችን መጠቀም አቁመን በምትኩም ወረቀት ነክ ነገሮችን መጠቀም፣ የውሃ አጠቃቀማችንን በቁጠባ ማድረግ፣ ህይወት ያላቸው ፍጥረቶች ሁሉ እንክብካቤ ማሳየት፣ በካይነት የሌላቸውን የመጓጓዣ አገልግሎቶችን መጠቀም፣ ዛፎችን መትከል. . . ወዘተ የመሳሰሉትን ተግባራት መፈጸም ያስፈጋል።

5.     አዲስ የምሕረት ተግባር

“የምሕረትን ተግባር ከማከናወን ከዚህ በተሻለ ሁኔታ ከእግዚአብሔር ጋር የምያዋህደን የተሻለ ነገር የለም፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ኃጥያታችንን ይቅር የሚለን እና ፀጋውን የሚሰጠን እኛም ይህንን የምሕረት ተግባር በስሙ ማከናወን እንድንችል ነው”።

የክርስቲያን ሕይወት ባህል ሰባት አካላዊ እና መንፈሳዊ የምሕረት ተግባራትን መፈጸም እንዳለብን ያስተምረናል። “ብዙን ጊዜ የምሕረት ተግባራት ከግለሰቦች ጋር በተያያዘ ሁኔታ የሚፈጸሙ ሲሆኑ ለምሳሌ ለታመሙት ሆስፒታል፣ ለተራቡት ምግብ ቤት፣ ቤት ለሌላቸው መኖሪያ ቤት፣ ለተማሪዎች ትምህርት ቤት. . . ወዘተ ብቻ መስሎን ሊታይን ይችላል። ነገር ግን የምሕረት ተግባራትን በጥቅሉ ብንመለከት የምሕረት ተግባራት ዋናው ትኩረት የሰው ነፍስ እና ሰውን ያማከሉ ነገሮች ብቻ እንደ ሆኑ ያመለክታል።

ያለምንም ጥርጥር “የሰው ልጅ ሕይወት እና ይህንንም ያማከሉ ነገሮች ሁሉ” የጋራ መኖሪያችን የሆነውን ቤታችን እንድንከባከብ አደራ ይሉናል ማለት ነው። ስለ የጋራ መኖሪያ ቤታችን መንከባከብ የዚህ የምሕረት ተግባራ አንደኛው አካል ነው።

6.     በመጨረሻም እንጸልይ

ምንም እንኳን ኃጥያተኞች ብንሆንም እና በብዙ መከራዎች ውስጥ እያለፍን ቢሆንም ቅሉ ተስፋ መቁረጥ አይገባንም ምክንያቱም ፈጣሪያችን መቼም ቢሆን ብቻችንን አይተወንምና ነው። መቼም ቢሆን ፈጣሪያችን መሆኑን አያቆምም፣ ምክንያቱም እርሱ ከምድራችን ጋር የተዋሃደ እና የእርሱ ፍቅር ሁል ጊዜም ቢሆን ወደ ፊት እንድንጓዝ የሚደግፈን በመሆኑ ጭምር ነው።

እንዲህ ብለን ልንጸልይ ይገባናል. . . “የድሆች አምላክ የሆንክ እግዚአብሔር ሆይ የተረሳችሁን እና የተጣለችሁን በአንተ ፊት ግን በጣም ውድ የሆነችውን ምድራችንን መታደግ እንድንችል እርዳን። የፍቅር አምላክ ሆይ በእዚህ ምድር ላይ ለሚገኙ ፍጥረታት ሁሉ ያንተን ፍቅር ማሳየት የምንችልበትን ቦታ እና ምንገዱን አሳየን። የምሕረት አምላክ ሆይ የተጎናጸፍነውን የአንተ ምሕረት የጋራ የመኖሪያ ቤታችን በሆነችው ምድራችን ውስጥ መተግበር እንድንችል እርዳን። የእግዚአብሔር ሥም የተመሰገን ይሆን።

25 May 2020, 18:39