ፈልግ

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ ዶክትሪን ጽንሰ-ሐሳብ አራት ደረጃዎች የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ ዶክትሪን ጽንሰ-ሐሳብ አራት ደረጃዎች  

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ ዶክትሪን ጽንሰ-ሐሳብ አራት ደረጃዎች

ክፍል ሰባት

1. ደረጃ አንድ፦ ካቶሊካዊ ጽንሰ-ሐሳብ

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ አጀማመሩ በቀጥታ ከኢንዱስትሪ አብዮት መጀመር ጋር የተያያዘ ሲሆን ይህም ከኢንዱስትሪ አብዮት መጀመር ጋር ተያይዞ በማኅበረሰቡ ላይ ሊቃጥ የሚችሉ አብዮቶችን ለመጋፈጥ በማሰብ የተጀመረ ነው።

በእዚህም መስረት የመጀመሪያው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ በይፋ የተጀመረው  እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1891 ዓ.ም በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩት ሊዮ 13ኛ  በላቲን ቋንቋ “Rerum Novarum” በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም “አዳዲስ ነገሮች” በሚል አርእስት በወቅቱ ለንባብ ባበቁት ሐዋሪያዊ መልዕክት ሲሆን በውቅቱ በአውሮፓ አህጉር በመስፋፋት ላይ በነበረው የኢንዱስትሪ አብዮት ምክንያት በተቋሙ የተለያዩ ፋብሪካዎች እና ማምረቻ ስፍራዎች ውስጥ ተቀጥረው በሚሰሩ የማኅበርሰብ ክፍሎች በእዚህ በተከፈተው አዲስ የስራ እንድል ለመጠቀም ልማዳዊ በሆነ መልኩ ለዘመናት ይኖሩበት የነበረውን የአኗኗር ዘዴ እና ልምድ በመቀየር፣ ከግብርና ወደ አዲስ የአመራረት ዘዴ በመሸጋጋራቸው፣ በገጠር በተበታተነ ሁኔታ ይኖሩ የነበሩ ሕዝቦች በፋብሪካዎች ውስጥ ተቀጥረው መሥራት በጀመሩበት ወቅት ሰብሰብ ብሎ የመኖር ልምድ እየተካኑ በመምጣታቸው ምክንያት አዲስ ማኅበርሰብ መፍጠር ችለው ነበር። በእዚህ አዲስ የማኅበርሰብ ስብስብ ውስጥ በርካታ ማኅበራዊ ችግሮች እየተከሰቱ በመምጣታቸው፣ በስራተኛው እና በአሰሪዎች መካከል በእየጊዜው የሰፋ የመጣ ልዩነት፣ አስሪዎች ለሰራተኞቻቸው የሚከፍሉት ክፍያ ያልተመጣጠን መሆኑ፣ ይህ በእንዱስትሪ አብዮት ምክንያት የተመሰረተው አዲስ ማኅበርሰብ የአኗኗር ባሕሉ እየተቀየረ በመምጣቱ የተነሳ ለተለያዩ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ፣ እንዲሁም የጤና ክብካቤ መስጫ ጣቢያዎች ማነስ እና አለመኖር . . . ወዘተ የመሳሰሉ ተግዳሮቶች በስፊው በመሰታዋላቸው ለእነዚህ አዲስ እየተከሰቱ ላሉ ተግዳሮቶች መልስ ለመስጠት ታስቦ የተጻፈ የመጀመሪያው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮን የተመለከተ ሐዋርያዊ መልእክት ነው።

በወቅቱ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1891-1931 ዓ.ም በአውሮፓ አህጉር በሰፊው ይሰትዋሉ የነበሩ የማርኪስዚም፣ ኮሚኒዚም እና የተለያዩ ዓይነት ፍልስፍናዎች እና ርዕዮተ ዓለማዊ ሐስተሳሰቦች የተነሳ ቤተክርስቲያን ለእነዚህ ወቅታዊ ለሆኑ ጽንሰ-ሐሳቦች እና ርዕዮተ ዓለማዊ አሰታሰቦች የራሷን አቋም ለማስጠበቅ እና የማኅበርሰቡ መንፈሳዊ እሴቶች ተጠብቀው እንዲቀጥሉ ለማስቻል ይረዳት ዘንድ ማኅበራዊ አስተምህሮችን በይፋ ማስተማር ጀመረች።

በወቅቱ በኢንዱስትሪ፣ በሳይንስ፣ በፍልስፍና፣ የተለያዩ ርዕዮተ ዓለማዊ አስተሳሰቦች እና በማኅበራዊ ሳይንስ አስተምህሮ መስፋፋት የተነሳ ማኅበረሰቡ በእነዚህ በውቅቱ በነበሩ አስተሳሰቦች ብቻ እየተነዳ እንዳይሄድ ለማድረግ እና ምንም እንኳን እነዚህ የሳይንስ እና የእንዱስትሪ አብዮት መስፋፋ በማኅበርሰቡ ሕይወት ላይ ከፍተኛ የሆነ አዎንታዊ የሆነ ለውጥ ማምጣቱ የሚካድ ባይሆንም ነገር ግን በእነዚህ አዳዲስ ርዕዮተ ዓለማዊ አስተሳሰቦች የተነሳ ማኅበርሰቡ ግብረ ገባዊ የሆኑ እሴቶቹን አንዳያጣ ለመርዳት በወቅቱ ይህ የማኅበራዊ አስተምህሮ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቱዋል። በተጨማሪም ተፈጥሮኣዊ የሆኑ ሕግጋት ተጠብቀው እንዲቀጥሉ ለማድረግ ታስቦ የሚደርግ ማኅበራዊ አስተምህሮ ሲሆን በይፋ በወቅቱ የነበረውን የሶሻሊዚም እና ኮሚኒዚም ርዕዮተ ዓለማዊ አስተሳሰቦችን ለመቃወም ታስቦ የተለያዩ ዓይነት ማኅበራዊ አስተምህሮች ይሰጡ ነበር።

02 March 2020, 10:36