ፈልግ

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ ምንጩ ምንድነው? የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ ምንጩ ምንድነው? 

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ ምንጩ ምንድነው?

ክፍል ስድስት

የካቶሊክ ቤተክርስትያን ማኅበራዊ አስተምህሮ በመረጃነት ወይም በምንጭነት ከእዚህ በታች የተጠቀሱትን ትጠቀማላች

1.     መጽሐፍ ቅዱስ

2.    የቤተክርስቲያን አባቶች በተለያዩ ውቅቶች ያስተማሩዋቸው አስተምህሮዎች እና የጻፉዋቸው ቃለ ምዕዳኖች፣ ሐዋርያዊ መልእክቶች. . . ወዘተ።

3.    የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ እና አስተምህሮ

4.    የነገረ መለኮት እና የፍልስፍና አስተምህሮዎችን ከግምት ባስገባ መልኩ

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ በዋነኝነት መሰረቱን የሚያደርገው የሰው ልጅን ክብር እና የማይገረሰሱ መብቶቹን በቀዳሚነት ከግምት በማስገባት እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን 4 ምንጮች በመረጃነት በመጠቀም የሚሰጥ አስተምህሮ ነው።

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ አራት ዋና ዋና መርሆችን መሰረት በማድረግ የቤተክርስቲያኗን አስተምህሮ ማሕበራዊ ይዘት እንዲኖረው በማድረግ ይጀምራል። የካቶሊክ ቤተክርስትያም ማኅበራዊ አስተምህሮ መሰረታዊ መርሆዎች የሚባሉት ውስጥ በቀዳሚነት የሚጥቀሰው የሰው ልጅ ሰብዐዊ ክብር የሚለው ሲሆን፣ የጋራ ተጠቃሚነት፣ ኅበረት እና መተጋገዝ (ድጎማ) የሚሉት ናቸው።

1.     የሰው ልጅ የስብዕና ክብር፡ የሰው ልጅ ሰብዕና ክብር እንዲጎናጸፍ ካደረጋቸው ነገሮች መካከል አንዱ እና ዋነኛው የሰው ልጆች ሁሉ መለኮታዊ ባሕሪይ አላቸው ከሚለው ጽንሰ ሐስብ የመነጨ ነው። የሰው ልጅ ሁሉ እግዚአብሄር ለእያንዳንዳችን የተሰጠውን ያንን ክብር የመጠበቅ፣ የማስተዋወቅ፣ የማራመድ ሞራላዊ ግዴታ አለበት። በእዚህም የተነሳ በእየለቱ በሥራ ቦታዎቻችን ውስጥ ይሁን በማንኛውም ማሕበራዊ ስፍራዎች ውስጥ የሰው ልጆችን ሰብዕዊ ክብር የሚነኩ ነገሮችን በማስወገድ፣ በምትኩም የሰው ልጆች ሰብዕዊ መብት ተከብሮ እንዲቀጥል የበኩላችንን አስተዋጾ ማድረግ ይገባናል። ከላይ ለመጥቀስ እንደ ተሞከረው የሰው ልጆች ሁሉ መለኮታዊ የሆነ ባሕሪይ አለቸው። (COMPENDIUM OF THE SOCIAL DOCTRINE OF THE CHURCH) በተሰኘው እና በእዚሁ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ ላይ አጭር እና የተሟላ ማብራሪይ በሚሰጠው  መጽሐፍ ላይ በምዕራፍ 3 ከቁጥር 105 ጀምሮ የተጠቀሰው ይህንኑ የሰው ልጆች መለኮታዊ በሕሪይ በማንሳት እንዲህ ይላል. . .

1.     ቤተክርስቲያን እያንዳንዱን ወንድ እና ሴት የእግዚአብሔር ራሱ ሕያው ምስል አድርጋ ትመለከታለች። ይህ ሕያው ምስል ሁል ጊዜም አዲስ በሆነ፣ ጥልቅ እና ሙሉ በሆነ መልኩ በክርስቶስ ምስጢራዊ እይታ፣ በእግዚኣብሔር ፍጽም በሆነ ምስል እግዚኣብሔርን ራሱ በሚገልጽ በአንድ ወንድ እና በአንድ ሴት ሰብዓዊ ክብር ላይ ሊገለጽ ይገባዋል። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በማኅበራዊ አስተምሮዋ አማካይነት ለድርድር ሊቀርብ የማይችል እና በፍጹም ሊገረሰስ የማይገባው የአንድ ወንድ እና የአንድ ሴት ሰብዓዊ ክብር ይከበር ዘንድ የምትሞግተው እና እነዚህም የሰብዓዊ ክብሮች ገቢራዊ እንዲሆኑ ልዩ ትኩረት ሰጥታ የምትንቀሳቀሰው የሰው ልጆች ሁሉ የእግዚኣብሔር መልኮታዊ ባሕሪይ መገለጫ በመሆናቸው የተነሳ ነው። የእግዚኣብሔር ልጅ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ስጋ በመልበስ ወደ ምድር መምጣቱ ሰዎች የእግዚኣብሔርን መለኮታዊ ባህሪይ በክርስቶስ አማካይነት ለገራት ችለዋል።  በእዚህም የሰውን ሰብዓዊ ባሕሪ ተላብሱዋል፣ በዚህ ምክንያት ቤተክርስቲያን ይህ መሰረታዊ ኃላፊነት ቀጣይነት ባለው መልኩ እየተከበረ መሆኑን በማየት ቀጣይነት ባለው መልኩ የሰው ልጆች ሰብዓዊ ክብር የእግዚኣብሔር ክብር መገለጫ በመሆኑ የተነሳ ተጠብቆ እንዲቀጥል ያራሱዋን ከፍተኛ የሆነ አስተዋጾ በማድረግ ላይ ትገኛለች። በክርስቶስ አማካይነት ቤተክርስቲያን የሰው ልጆችን መንገድ ታመላክታለች፣ በእዚህም ተግባሩዋ ቤተክርስቲያን ሁሉንም የሰው ልጆች ቅርብ ይሁኑ ሩቅ፣ ብናውቃቸውም ባናውቃቸውም፣ በተለይም ደግሞ ድኾችን እና በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ እየተጎሳቆሉ የሚገኙ ሰዎችን፣ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችንም ሳይቀር ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ እንደ ሞተ ቤተክርስቲያን ለሁሉም ለማስገዘብ ትወዳለች። (1 Cor 8:11; Rom 14:15)

2.    በማንኛውም ዓይነት ማኅበራዊ ኑሮ ውስጥ ዋነኛው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው የሰው ልጅ ብቻ ሊሆን ይገባዋል። ቤተክርስቲያን ባገኘችሁ አጋጣሚ ሁሉ በማንኛውም ማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ዋነኛውን ገጸ ባሕሪይ ሊጫወት የሚገባው የሰው ልጅ እንደ ሆነ ታስተምራልች፣ ግንዛቤ እንዲፈጠር የበኩሉዋን ጥረት ታደርጋለች። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮን ለማስተማር ካነሳሱዋት ዋነኛ ነገሮች መካከል አንድን ማኅበረሰብ ማኅበረሰብ እንዲሆን የሚያደርገው የሰዎች ስብስብ በመሆኑ የተነሳ ቤተክርስቲያን ደግሞ የሰው ልጆች በእግዚኣብሔር መልክ እና አማሳል መፈጠራቸውን የምታምን እና የምታስተምር በመሆኑዋ፣ የሰው ልጆች ባሉበት ቦታ ሁሉ ቤተክርስቲያን ሊገረሰስ የማይችሉ የሰው ልጆች መሰረታዊ ሰብዓዊ መብቶች እና አብሮ የመኖ ሕልውናቸው ተጠብቆ ይሄድ ዘንድ የምታስተምረውም በእዚሁ ምክንያት ነው። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ መሰረቱን እና ግቡን የሚያደርገው በሰው ልጆች ላይ ብቻ ነው። ማንኛውም ዓይነት ማኅበራዊ ኑሮ መሰረቱን ያደርገው በሰው ልጆች መስተጋብር ላይ ነው። በእዚህም ምክንያት የሰው ልጆችን ከማኅበረሰብ ጽንሰ-ሐሳብ ለይተን ማየት በፍጹም አንችልም። በእዚህም ምክንያት ማኅበረሰብ የሚለው ቃል የምያመልክተው ወደ ሰው ልጆች ነው።

3.    የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በታሪክ ሂደት ውስጥ ያደረገችው የማኅበራዎ አስተምህሮ የሰው ልጆችን ማዕከል ባደረገ መልኩ እንደ ነበር የሚታወቅ ሲሆን የሰው ልጆች በእግዚኣብሔር መልክ እና አምሳል የተፈጠሩ በመሆናቸው የተነስ፣ ይህንን የእግዚኣብሔር ገጽታ በሚያጎድፍ መልኩ በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ማንኛውንም ዓይነት ኢሰባዊ የመብት ጥሰት ታወግዛለች፣ ይህም የጭቆና ቀንበር ይወገድ ዘንድ ድምጹዋን ለዓለም ታሰማለች።

4.    የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ መሰረታዊ መርሆች አጠቃላይ በሆነ ማኅበረሰባዊ እውነታ ላይ የተመሠረተ ነው። በእዚህም መስረት እያንዳንዱ ሰው ሕሊና በእውነት ላይ በተመስረተ መልኩ ሁሉም ሕዝቦች ወይም ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል ከሕሊን እውነት በሚመነጭ መልኩ እርስ በእርስ እንዲገናኙ በማድረግ ላይ ትኩረቱን ያደርገ ነው። እነዚህ መሰረታዊ መርሆች ግብረገባዊ የስብዕና ትርጉም አላቸው፣ ምክንያቱም በማህበረሰቡ ውስጥ የህይወት መሠረት እና ማደራጃ መሠረት ናቸው።

02 March 2020, 10:33