ፈልግ

ብፁዕ አቡነ አንጄሎ ሞሬስኪ ከእዚህ ዓለም በሞት ተለዩ! ብፁዕ አቡነ አንጄሎ ሞሬስኪ ከእዚህ ዓለም በሞት ተለዩ! 

ብፁዕ አቡነ አንጄሎ ሞሬስኪ ከእዚህ ዓለም በሞት ተለዩ!

በኢትዮጵያ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጋምቤላ ሀገረ ስብከት ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ አንጄሎ ሞሬስኪ ትላንት መጋቢት 15/2012 ዓ.ም. ከእዚህ ቀደም በደረሰባቸው የጤና እክል ምክንያት ለብዙ ጊዜ ያህል በጣልያን ሀገር በሕክምና ሲረዱ ከቆዩ በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ መሆናቸው ተገልጹዋል።

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ የሆኑት ክቡር  አባ ተሾመ ፍቅሬ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን፣ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባሄ ፕሬዚዳንትን በመወከል ባስተላለፉት መልእክት ለወንድሞቻቸው ብጹዕን ጳጳሳት፣ በጋምቤላ ሀገረ ስብከት ለሚገኙ ካህናት፣ ገዳማውያን፣ ምእመናን እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸው በሙሉ በብፁዕነታቸው ህልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልጸዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ አባላት እና መላዋ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በጸሎት ከናንተ ጋር መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።

እግዚአብሔር የብፁዕ አንጀሎን ነፍስ በገነት ያሳርፍ! አሜን!!

የቫቲካን ዜና

25 March 2020, 16:05