ፈልግ

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ ክፍል 5 የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ ክፍል 5 

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምሕሮ የሚጠቀማቸው ሳይንሳዊ ዘዴዎች

ክፍል  አምስት 

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ በዋነኛነት ሁለት ዓይነት የማኅበራዊ ሳይንስ ምክንያት አሰጣጥ ዘዴዎችን ይጠቀማል። ከንዑስ ነገሮች በመነሳት ወደ ዓብይ ወይም አጠቃላይ ሁኔታዎችን ከግምት ያስገባ የምክንያት አሰጣጥ ዘዴ (inductive) ከዓብይ ወይም ከአጠቃላይ ጉዳዮች በመነሳት ወደ ንዑስ ጉዳዮች በመወረድ የሚሰጠ የምክንያት አሰጣጥ ዘዴ (deductive) የሚባሉትን የማኅበራዊ ሳይንስ የጥናት እና ምክንያት አሰጣጥ ሳይናሳዊ ዘዴዎችን ይከተላል።

1. ከንዑስ ነገሮች በመነሳት ወደ ዓብይ ወይም አጠቃላይ ሁኔታዎችን ከግምት ያስገባ የምክንያት አሰጣጥ ዘዴ (Inductive Method)፦ ማኅበረሰቡ እየተጋፈጣቸው የሚገኙትን ጭግሮች እና ተግዳሮቶችን ሥር መሰረታቸውን በማጥናት፣ የችግሮችን መንስሄ በመለየት፣ እነዚህ ማኅበራዊ የሆኑ ችግሮች እና ተግዳሮቶች እንዲፈጠሩ ምክንያት የሆኑ ንዑስ ጉዳዮችን ነቅሶ በማውጣት፣ ችግሮችን በጥልቀት በመመረመር፣ በእውነት ላይ የተመሰረት ምክንያታዊ የሆነ ምላሽ ትሰጣላች። በእዚህም አግባብ በማኅበረሰቡ ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮችን መሰረታዊ የሆኑ ንዑስ ምክንያቶችን በሚገባ በመመርመር ችግሮች በሰላማዊ ሁኔታ ይፈቱ ዘንድ በማኅበራዊ አስተምህሮዋ አማካይነት የበኩሉዋን አዎንታዊ አስተዋጾ ታደርጋለች። በአጠቃላይ የችግሮችን መነሻ ባሕሪ በመመርመር፣ በየደረጃው ተገቢ የሆነ መፍትሄ እንዲገኝ ባማድረግ፣ የማኅበረሰቡን ማኅበራዊ መስተጋብር፣ ህልሙን፣ አብሮነቱን እነዚህን እና እነዚህን የመሳሰሉ ማኅበረሰቡን በሰላም እና በመከባበር እንዲኖር የሚያደርጉ ክስተቶች ተጠብቀው እንዲሄዱ ባማስተማር፣ በተቃራኒው ደግሞ የማኅበረሰቡን ሰላም የሚያናጉ ማነኛቸውንም ነገሮች ምክንያትዊ እና ሰላማዊ በሆነ መልኩ በመቃወም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትሰጣለች።

2. ከዓብይ ወይም ከአጠቃላይ ጉዳዮች በመነሳት ወደ ንዑስ ጉዳዮች በመወረድ የሚሰጠ የምክንያት አሰጣጥ ዘዴ (deductive method)፦ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ይህንን ከአጠቃላይ ሁኔታ በመነሳት ወደ ንዑስ ጉዳዮች በመወረድ (deductive method) የተባለውን የማኅበራዊ ሳይንስ ምክንያት አሰጣጥ ዘዴ በመጠቀም በማኅበረሰቡ ውስጥ የሚከሰቱ የማኅበረሰቡን ሁለንተናዊ ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ ነገሮችን ከአጠቃላይ ሁኔት በመነሳት በመገምገም፣ ለእዚህ ማኅበራዊ ችግር አስተዋጾ ያደርጉትን ጥቃቅን የሚባሉ ተግባራትን ከአጠቃላይ ሁኔታ በመነሳት በየፈርጁ ያሉትን ነገሮች በመመርመር የመፍትሄ ሐሳብ በማስቀመጥ የማኅበረሰቡ ሰላም እና አንድነት ተጠብቆ እንዲቀጥል የበኩሉዋን አስተዋጾ ታደርጋለች። ይህ የማኅበራዊ አስተምህሮ አሰጣጥ ሳይንሳዊ ዘዴ ይበልጡኑ ግልጽ ይሆን ዘንድ የሚከተለውን ምሳሌ ለመጠቀም እፈልጋለሁ።

እንደ ሚታወቀው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣው የዓለማችን የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በዓለም ዙሪያ የሚገኙ አገራት በተለይም ለዓለማችን የአየር ንብረት ለውጥ እዚህ ግባ የሚባል አስተዋጾ ያላደርጉ፣ ነገር ግን ይህ የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው ሰበብ ምክንያት በጎርፍ፣ በርሃብ፣ በቸነፈር፣ በሙቀት፣ በውሃ ሙላት... .ወዘተ መቋቋም አቅቱዋቸው እየተሰቃዩ ለሚገኙ ድሃ የሆኑ ሀገሮችን በምሳሌ ማንሳት ይቻላል። የእዚህ ችግር አጠቃላይ መንስሄ ስንመለከት የአየር ንብረት ለውጥ ያስከተለው ችግር መሆኑን እንገነዘባለን። ከእዚህ ጠቅላላ ሁኔታ በመነሳት ለዓለማችን የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሆኑ መንስዎችን ማለትም (በእንዱስትሪ ቴክኖሎጂ ምክንያት ከሚፈጠረው በካይ ጪስ፣ የተፈጥሮ ሐብቶችን ያለአግባቡ ወይም ከመጠን በላይ ከመጠቀም፣ በካይ የሆኑ ጋዞችን ወደ ከባቢያዊ አየር መልቀቅ. . . ወዘተ) እነዚህን እና እነዚህን የመሳሰሉ የችግሩ መነሻዎችን በመመልከት ከጠቅላላ ሁኔታ በመነሳት ይህ ችግር እንዲከሰት መንስሄ የሆኑትን ንዑስ ጉዳዮችን በጥልቀት በመመርመር የመፍትሄ ሐሳብ ታቀርባለች፣ ምክንያቱም በአይረ ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚጎዳው ያው የሰው ልጅ በመሆኑ የተነሳ ነው። ለእዚህም በአብነት መጠቀስ የሚቻለው በላቲን ቋንቋ “Laudato si” በአማሪኛው ሲተረጎም ውዳሴ ላንተ ይሁን በሚል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለንባብ ያበቁት ቃለ ምዕዳን ላይ የጋራ የሆነችውን የመኖሪያ ቤታችንን እንከባከብ በማለት ያሰፈሩትን መልእክት በዋቢነት መጥቀስ ወይም መመልከት ይቻላል።

03 February 2020, 15:19