ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በባሪ የሚያደርጉ ጉብኝት በስደተኞች እና በመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ ላይ ማዕከሉን ያደረገ ነው። ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በባሪ የሚያደርጉ ጉብኝት በስደተኞች እና በመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ ላይ ማዕከሉን ያደረገ ነው።  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በባሪ የሚያደርጉ ጉብኝት በስደተኞች እና በመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ ላይ ማዕከሉን ያደረገ ነው።

የደቡባዊ ጣልያን ግዛት የሆነችው የፑሊያ ክፍለ አገር ዋና ከተማ በሆነችው ባሪ በመባል በምትታወቀው ከተማ ውስጥ “ሰላም የሰፈነበት ሜድትራንያን” በሚል መሪ ቃል መንፈሳዊ አስተንትኖን ያካተት አንድ ጉባሄ በመካሄድ ላይ እንደ ሚገኝ ተገልጹዋል። በእዚህ ጉባሄ ላይ ለመገኘት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመጪው እሁድ የካቲት 15/2012 ዓ.ም ወደ ባሪ እንደ ሚያቀኑ የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በባሪ በሚያደርጉት የግማሽ ቀን ውሎ በስደተኞች እና በመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ ላይ ማዕከሉን ያደረገ እንደ ሚሆን ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ- ቫቲካን

በእዚህ ጉባሄ ላይ የሜድትራኒያን ባሕር ከሚያዋስናቸው አጋራት የተውጣጡ ከ19 በላይ የሚሆኑ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጽዕን ጳጳሳት ተካፋይ እንደ ሆኑ የተገለጸ ሲሆን በእዚህ ጉባኤ ላይ “የዓለማችን የስልጣኔ ምንጭ ነው” ተብሎ በሚታሰብበት በእዚሁ የሜድትራኒያን ቀጣን አከባቢ በአሁኑ ወቅት የሚታዩትን የተለያዩ ችግሮች በተለይም በአስገዳጅ ሁኔታ አገሮቻችውን ጥለው የሚሰደዱ ስደተኞችን ተቀብሎ ማስተናገድ የሚችላበትን መንገድ፣ ወጣቱ የማሕበርሰብ ክፍል በክርስትና እምነቱ ታንጾ ማደግ የሚችልበት ሁኔታ ላይ እየተነጋገረ የሚገኝ ጉባሄ ሲሆን በተጨማሪም ሥራ አጥነትን በተመለከተ፣ የባህል ሽግግር እና የሰላም ግንባታን የተመለከቱ ወቅታዊ የሆኑ ጉዳዮችን በማንሳት ውይይት እየተደረገ እንደ ሚገኝ ተገልጹዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የደቡባዊ ጣልያን ግዛት የሆነችው የፑሊያ ክፍለ አገር ዋና ከተማ በሆነችው ባሪ በመባል የምትታወቀውን ከተማ ሲጎበኙ ይህ በመጪው እሁድ የካቲት 15/2012 ዓ.ም የሚያደርጉትን ጉብኝት ጨምሮ ሁለኛው ጉብኝት እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን እ.አ.አ በ2018 ዓ.ም በእዚያው በባሪ ከተማ ተገኝተው በመካከለኛው ምስርቅ ሰላም ይሰፍን ዘንድ ጸሎት ማደራጋቸው ይታወሳል።

“ሰላም የሰፈነበት ሜድትራንያን” በሚል መሪ ቃል መንፈሳዊ አስተንትኖን ባካተተ መልኩ በባሪ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው ጉባሄ የተዘጋጀው በጣሊያን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ አስተባባሪነት እንደ ሆነ የጉባሄው ዋና ፕሬዚዳንት የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ጓልቲዬሮ ባሴቲ ከቫቲካን ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ የገለጹ ሲሆን ይህ የቀደምት ስልጣኔ ምንጭ አከባቢ የሆነው የሜድትራኒያን አከባቢ የሰላም ቀጣና ይሆን ዘንድ የሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሚወያይ ጉባሄ እንደ ሆነ ጨምረው ገለጸዋል።

በእዚህ ጉባሄ ላይ ከሰሜን አፍሪካ፣ ከአውሮፓ እና ከመካከለኛው ምስራቅ የተውጣጡ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት እና እንዲሁም በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ምሁራን ተሳተፊ እንደ ሆኑ የተገለጸ ሲሆን በእዚህ ጉባሄ ላይ ከስደት ጋር የተገናኙ ጉዳዮችን፣ ስብከተ ወንጌልን ለወጣቶች ተገቢ በሆነ መልኩ ተደራሽ ለማደረግ የሚረዱ ጥናቶች፣ የሥራ አጥነት፣ የባህል ሽግግር እና የሰላም አተገባበርን በተመለከተ ውይይቶች እየተካሄዱ እንደ ሆነ ተገልጹዋል።

ጉባሄው በይፋ የተጀመረው ረቡዕ የካቲት 11/2012 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ሐሙስ እለት “እምነትን ለመጪው ትውልድ ማሸጋገር” በሚል አርዕስት ውይይት የተካሄደ ሲሆን ዐርብ የካቲት 13/2012 ዓ.ም ደግሞ “በቤተክርስቲያን እና በማኅበረሰብ መካከል ያለው ግንኙነት- እንቅስቃሴ ፣ ዜግነት ፣ የሃይማኖት ነፃነት ፣ እኩልነት” በሚሉ አርእስቶች ላይ ውይይት ተደርጉዋል።

ቅዳሜ የካቲት 14/2012 ዓ.ም በመጨረሻው ሰነድ ላይ የሚካተቱን አጠቃላይ ድምዳሜዎችን በተመለከተ ሰፊ ውይይቶች ከተደረጉ በኋላ እሁድ የካቲት 15/2012 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በተገኙበት የጉባሄው አጠቃላይ ይዘት ላይ ማብራርያ ከተሰጠ በኋላ የመጨረሻው ሰነድ ላይ ፊርማቸውን እንደ ሚያኖሩ ይጠበቃል።

የክርስቲያኖች ፍልሰት እና ስደት

ከቱርክ ሆነ ከሰሜን አፍሪካ ወደ አውሮፓ ለመግባት የሚሞክሩ ሰዎች በቀጠናው በብዛት እንደ ሚስተዋሉ የሚታወቅ ሲሆን አብዛኛዎቹ ስደተኞች በሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች አማካይነት የሚዘዋወሩ ሲሆን በእዚህም የተነሳ ብዙዎቹ ስደተኞች ሕገወጥ በሆነ የመጠሊያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ሲሆን በእነዚህ ጣቢያዎች ውስጥ ለጉልበት ብዝበዛ እና ለጥቃት እንደ ሚጋለጡ ከሚወጡት ሪፖርቶች ለመረዳት ይቻላል።

የስደተኞችን ጉዳይ በተማከለ መልኩ እልባት መስጠት የሚያስችሉ ፖሊሲዎችን ለመቀረጽ ይቻል ዘንድ ስደትኞችን በሕገወጥ መንገድ የሚያዘዋውሩ ሕገወጥ ሰዎችን መጋፈጥ እንደ ሚገባ እና ይህንን ሕገ ወጥ  ድርጊት ለመግታት ይችላ ዘንድ የተማከለ አሰራር መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ የተነሳ ለእዚህ አንገብጋቢ ጉዳይ ትኩረት ለመስጠት ታስቦ የሚካሄድ ጉባሄ ሲሆን የስደተኞችን ጉዳይ ሰብዓዊ እና ሕጋዊ በሆነ መልኩ ዘላቂ በሆነ መልኩ ለመፍታት የሚያስችሉ ሐሳቦች ከእዚህ ጉባሄ እንደ ሚጠብቀ ከወዲሁ ግምት ተሰጥቱዋል።

21 February 2020, 15:57