ፈልግ

የየካቲ 15/2012 ዓ.ም ዘዘወረደ እለተ ስንበት ቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ የየካቲ 15/2012 ዓ.ም ዘዘወረደ እለተ ስንበት ቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ 

የየካቲ 15/2012 ዓ.ም ዘዘወረደ እለተ ስንበት ቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ

ሰዎች እንዲያዩላችሁ፣ መልካም ሥራችሁን በፊታቸው ከማድረግ ተጠንቀቁ፤ እንዲህ ካደረጋችሁ ከሰማዩ አባታችሁ ዋጋ አታገኙም። “ግብዞች በሰዎች ዘንድ ለመከበር ብለው በየጎዳናውና በየምኵራቡ እንደሚያደርጉት፣ አንተም ለድኾች ምጽዋት በምትሰጥበት ጊዜ ይታይልኝ ብለህ ጥሩምባ አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ እንዲህ የሚያደርጉ ዋጋቸውን በሙሉ ተቀብለዋል። እናንተ ግን ለድኾች ስትሰጡ ቀኝ እጃችሁ የሚያደርገውን ግራ እጃችሁ አይወቅ፤ ምጽዋታችሁ በስውር ይሁን፤ በስውር የተደረገውን የሚያይ አባታችሁም ዋጋችሁን ይከፍላችኋል። “ስትጸልዩ እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ እነርሱ ለሰዎች ለመታየት ሲሉ በየምኵራቡና በየመንገዱ ማእዘን ላይ ቆመው መጸለይ ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ሙሉ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ስትጸልይ ወደ ክፍልህ ግባ፤ በሩንም ዘግተህ በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የተደረገውን የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል። 

“ስትጾሙ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ እነርሱ መጾማቸው እንዲታወቅላቸው ሆን ብለው በፊታቸው ላይ የሐዘን ምልክት ያሳያሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ እንዲህ የሚያደርጉ ዋጋቸውን በሙሉ ተቀብለዋል። አንተ ግን በምትጾምበት ጊዜ ፊትህን ታጠብ፤ ራስህንም ተቀባ፤ በዚህም መጾምህ በስውር ያለው አባትህ ብቻ የሚያውቀው፣ ከሰዎች ግን የተሰወረ ይሆናል፤ በስውር የተደረገውን የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል (ማርቆስ 6=1)።

 “በጽዮን መለከትን ንፉ፥ ጾምንም ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ” (ኢዩኤል 2፡15) ይለናል። ይህ ዐብይ ጾም ወቅት የሚጀመረው ለጆሮ በሚሰቀጥጥ መለከት በሚነፋበት ወቅት በሚያወጣው ድምጽ ሲሆን ነገር ግን ከዚያን በኋላ ወደ ደስታ በዓል ይለወጣል። ይህ የሕይወታችን ጉዞ እንዲዘገይ ማድረግ የሚችል በጣም ፈጣን የሆነ ድምጽ ሲሆን ነገር ግን አቅጣጫ አልባ የሆነ ድምጽ ነው። በሚያስፈልጉን ነገሮች ላይ ብቻ ማተኮር እንችል ዘንድ የቀረቡ የመጥሪያ ድምጾች ናቸው፣ እኛን የሚረቡሹን የማያስፈልጉንን ነገሮች መጾም እንድንችልኛ የቀረበልን የማቂያ ድምጽ ነው።

ይህ የማንቂያ ጥሪ ጌታ በነቢዩ ከንፈር አማካይነት በተናገረው አጭር እና ከልብ የመነጨ “ወደ እኔ ተመለሱ” (ኢዩኤል 2፡12) ከሚለው መልእክት ጋር ተያይዞ የቀረበ ነው። ወደ እኔ ተመለሱ። መመለስ ካለብን እኛ ቀድመን ጠፍተናል ማለት ነው። የዐብይ ጾም ወቅት የህይወት አቅጣጫን ዳግም ለማግኘት እድል የሚሰጠን ወቅት ነው። ምክንያቱም በእያንዳንዱ ጉዞ ውስጥ፣ በኣያንዳንዱ የጉዞ ሂደት ውስጥ  ዋናው ጉዳይ ግባችን ምን መሆኑን አለመዘንጋታችን ነው። ለመጓዝ የምንፈልገን ነገር ቢኖር በጉዞ ወቅት አከባቢያችንን በመቃኘት ምግብ መብላት ስላለብን በእዚያ አከባቢ ምግብ ቤት መኖሩን ወይም አለሞኖሩን ካላረጋገጥን በስተቀር ርቀን ለመጓዝ አንችልም። ራሳችንን እንዲህ እንዲህ ብለን እንጠይቅ፣ በሕይወት ጉዞዬ ውስጥ መንገዱ ቢርቅም እንኳን ወደ ፊት ለመጓዝ እፈልጋለሁ ወይ? ወይም የዛሬውን ጊዜ ቢቻ በመኖር ጥሩ ስሜት እንዲሰማኝ በማድረግ አንዳንድ ችግሮችን በመፍታት እና በመዝናናት ደስተኛ ሆኜ ለመኖር እፈልጋለሁ ወይ? ታዲያ ይህ መንገድ የተኛው ነው? በዛሬው ዘመን የሚገኙ  ብዙዎች እንደሚናገሩት በቅድሚያ የሚያስፈልገኝ አላፊ የሆነው የጤና ጉዳይ ነው? ወይስ ደግሞ ሐብት መሰብሰብ እና ጥሩ የሆነ ኑሮ መኖር ነው? እኛ ክርስቲያኖች ግን በዚህ ዓይነት ዓለም ውስጥ መኖር አይገባንም። “ወደ እኔ ተመለሱ ይለናል” አምላክችን። ወደ እኔ ኑ ይለናል። በዚህ ዓለም ውስጥ የእኛ የክርስቲያኖች ግብ ጌታ አምላካችን ብቻ ነው። ሁሉም አቅጣጫ ወደ እርሱ ሊመራን ይገባል።

የዐብይ ጾም ወቅት ከክርስትና ሕይወታችን ጋር የማይጣጣሙ ነገሮችን በማስወገድ እና ከመቼው ጊዜ በተሻለ ለመታደስ፣ በደስታ እና በተስፋ ተሞልተን የጌታን ትንሳሄ ለማወጅ አመቺ የመዘጋጃ ወቅት ነው። ቤተክርስቲያን በእናትነት ጥበብ ተሞልታ እምነታችንን ልያዳክሙ ወይንም ልያጥለቀልቁ የሚችሉ ማነኛቸውንም ነገሮች ልዩ ትኩረት እንድንሰጥ ትጋብዘናለች።

ለብዙ ፈተናዎች ተግላጮች ነን። እያንዳንዳችን ልያጋጥሙን የሚችሉትን ችግሮች እናውቃለን። የእለት ተእለት ሕይወታችንን ሁሌም የሚለያይ ሁኔታዎች ሲገጥመን ይህንን ህመምና እና ያለመተማመን ስሜት የሚጠቀሙ ድምፆች አሉ፡ እነዚህ ድምጾች በእዚህ አጋጣሚ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር የእነርሱን ተአማኝነት የሌለውን ድምጽ እንድንሰማ ማድረግ ነው። የእመንት ፍሬ ፍቅር ከሆነ ቅድስት እማሆይ ትሬዛ አዘውትረው ይሉ እንደ ነበረው በእዚህ መሰረት የአለመተማመን ፍሬ ደግሞ ግዴለሽነት ወይም የያዝነውን ሕይወት መተው ነው። አለመተማመን፣ ግድዬለሽነት እና ከሕይወት ጉዞ መሸሽ~ እነዚህ ነገሮች አማኝ የሆኑ ሰዎችን ነብስ የሚገሉ እና ሽባ የሚያደርጉ ነገሮች ናቸው።

የዐብይ ጾም ወቅት እነዚህን እና እነዚን የመሳሰሉ ፈተናዎችን ነቅሰን የምናወጣበት ወቅት ነው፣ የልብ ምትአችን ትርታ በኢየሱስ ቅኝት እንዲመታ ማድረግ ይገባል። ይህንን የአብይ ጾም ወቅት በእዚህ ዕእይነቱ እምነት ተሞልተን መፈጸም ይኖርብናል፣ ይህንንም ስናደርግ የክርስቲያኖችን ልብ ብርሃን እንደ ገና እንዲበራ የሚያደርጉትን ለፍታ ያህል ቆም ማለት፣ መመልከት እና መመለስ የሚሉትን ነገሮች በሕይወታችን መለማመድ ይኖርብናል።

 ለአፍታ ቆም ማለት ያለእኛ ፈቃድ በሕይወታችን ውስጥ ገብተው ነብሳችንን ሚያስጨንቁ ስሜቶችን የሚሞሉ አለመረጋጋትና ጭንቀቶች መተወ ማለት ነው። ከዚህ ነገሮች መታቀብ ደግሞ አስደንጋጭ በሆነ ፍትነት ሕይወታችንን በመበታተን እና በመከፋፈል በመጨረሻም ከቤተሰቦቻችን፣ ከጓደኞቻችን፣ ከልጆቻችን ከአያቶቻችን በመጨረሻም ለእግዚኣብሔር እንሰጠው የነበረው ነገር ግን በአስገዳጅ ሁኔታ ከእኛ የተወሰደብንን ጊዜ መልሰን እንድናገኝ ያስችለናል።

ለአፍታ ያህል ቆም ማለት እዩኝ እዩኝ ከሚያሰኘን መንፈስ እና በሁሉም ዘንድ እንደ ማስታወቁያ ሰሌዳ ከመታየት እንድንቆጠበ ያደርገናል።

ሕይወታችንን አንድ ጊዜ ቆም ብሎ መመልከት የሚጠቅመው፣ ኩራትን በማስወገድ፣ የርህራሄ ልብ እንዳይኖረን ከሚያደርጉ ነገሮች በመራቅ፣ በኃጢአትና በስህተት የተጠቁት እና ለተጎዱ፣ ለመጥፋት የተጋለጡትን ጋር በመተባበር ልባዊ ርህራሄ እና አክብሮት እንዲኖረን ያደርገናል።

ሕይወታችንን አንድ ጊዜ ቆም ብለን መመልከት የሚጠቅመው፣ ሁሉን ነገር በቁጥጥራችን ሥር እናድርግ ከሚል ስሜት፣ ሁሉን ነገር እናውቃለን ከሚል ስሜት፣ ሁሉን ነገር ወደ ጥፋት መንገድ ከመምራት እንድንቆጠብ ያግዘናል። ይህን ማድረግ የምንችለው ሕይወትንና መልካም የሆኑ ስጦታዎችን በሙሉ ለሰጠን እግዚአብሔር ምስጋናችንን ማቅረብ ስንችል ነው።

ሕይወታችንን አንድ ጊዜ ቆም ብለን መመልከት የሚጠቅመው፣ የማዳመጥ ችሎታችንን በመቀነስ፣ ፍሬያማ እንዳንሆን በማድረግ እያታችንን ከሚጋርዱን ነገሮች ነጻ እንሆናለን።

ሕይወታችንን ለአንድ አፍታ ቆም ብለን መመልከት መካን እንድንሆን ከሚያደርጉን እና በብቸኝነታችን የተነሳ ከሚፈጠሩት ገንቢ ካልሆኑ ሐሳቦች እና ከራስ ወዳድነት መንፈስ፣ ወንድሞቻችንን መገናኘት እንዳለብን ከሚያስረሳን ጫናዎቻቸውን እና መከራዎቻቸውን ችላ እንድንል ከሚያደርጉን ነገሮች ነጻ እንድነዋጥ ኣያደርገናል።

ሕይወታችንን ለጥቂት ጊዜ ቆም ብለን መመልከት በውስጣችን ያለውን ባዶነት እንድንመለከት፣ ጊዜያዊ እና በነው የሚጠፉ ነገሮችን፣ ከሥር ምሰረታችን ከሚለኣዩን ነገሮች፣ ነባር ከሆአን ግንኙነቶች የሚለያየንን፣ እሴቶቻችን ጠብቀን እንዳንሄድ ከሚያደርጉ ነገሮች እና ጉዞዋችንን በማስተዋል እንዳንጓዝ የሚያደርጉ ነገሮችን ነቅሰን ለማውጣት ይረዳናል።

ስለእዚህም ለአፍታ ያህል ቆም ብላችሁ ሕይወታችንሁን ተመልክቱ ሕይወታችሁን መርምሩ።

የበጎ አድራጎት ተግባራትን እንዳንፈጽም የሚከለክሉ ነገሮችን በመምልከት የእምነትን እና የተስፋን ነበልባል ተቀጣጥሎ እንዲቀጥል አድርጉ። ሕያው በሆኑት ሰዎች ፍት ላይ የእግዚአብሔር ርኅራኄን እና በጎ ሥራ በመካከላችን ውስጥ እየሠራ መሆኑን ተመልከት።

እለት በኣለት በሕይወታችን ውስጥ ወደፊት ለመጓዝ እና ብዙ አሳሳቢ ጉዳዮች እና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢያጋጥማቸውም  ቤታቸውን የፍቅር ትምህርት ቤት ለማድረግ የሚጥሩ ቤተሰቦቻችንን ፊት ተመልከት።

22 February 2020, 12:51