ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በጥር 10/2011 ዓ. ም. ለክርስቲያኖች አንድነት ጸሎት በሮም በቅ. ጳውሎስ ባዚሊካ በተካሄደበት ወቅት (ፋይል) ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በጥር 10/2011 ዓ. ም. ለክርስቲያኖች አንድነት ጸሎት በሮም በቅ. ጳውሎስ ባዚሊካ በተካሄደበት ወቅት (ፋይል) 

ለአንድ ሳምንት ያህል ለክርስቲያኖች አንድነት ለሳምንት የሚደረገው የጸሎት በጥር 09/2012 ዓ.ም ተጀመረ!

በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በየአመቱ ከጥር 09-16/2012 ዓ.ም ድረስ ለክርስቲያኖች አንድነት ጸሎት የሚደረግበት ሳምንት እንደሆነ ይታወቃል። ይህ የጸሎት ሳምንት መሰረቱን ያደረገው “አባት ሆይ፤ አንተ በእኔ፣ እኔም በአንተ እንዳለሁ ሁሉም አንድ እንዲሆኑ፣ እንዲሁም አንተ እኔን እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፣ እነርሱም በእኛ እንዲሆኑ ነው” (ዮሐንስ 17፡21) በማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአባቱ ባቀርበው ጸሎት ላይ መሰረቱን ያደርገ ነው።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በስነ-ቋንቋ የቃላት የሀረግ አመጣጥና እድገት ጥናት መሰረት በአጠቃላይ ክርስቲያን ማለት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አስተምህሮን የተቀበለ፣ ይህንን አስተምህሮ ተቀብሎ ምስጢረ ጥምቀትን የተቀበለ፣ ክርስቶስ ባስተማረው መሰረት በስነ-ምግባር የታጀበ ሕይወት የሚኖር ሰው ማለት ነው። እንደ ሚታወቀው በአሁኑ ወቅት እጅግ በጣም በርካታ የሚባሉ በክርስቶስ ስም የሚጠሩ ክርስቲያኖች በዓለም ውስጥ እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ የተነሳ በክርስቶስ ስም የሚጠሩ ክርስቲያኖች በሙሉ መሰረታቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመሆኑ የተነሳ አንድ የሚያደርጋቸው የክርስትና እምነት እሴቶች ይኖራቸዋል ማለት ነው።

በአሁኑ ወቅት በክርስቶስ ስም ላይ መሰረታቸውን ያደረጉ በርካታ የተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን እነዚህ የክርስቶስን ስም ያነገቡ አብያተ ክርስቲያናት አንድ የሚያደርጋቸው እና መሰረታቸውን የገነቡት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በመሆኑ የተነሳ በአንድነት የክርስትና እምነት እሴቶችን ለዓለም ይመሰክሩ ዘንድ በማሰብ የሚደርገ የጸሎት ሳምንት ነው። ለክርስቲያኖች አንድነት ጸሎት የሚደረግበት ሳምንት ማለት ሁሉም ክርስቲያኖች የእመነት ተቋሞቻቸውን ትተው በአንድ የእምነት ተቋም ሥር እንዲተዳደሩ በማሰብ የሚደረግ የጸሎት ስማንት ሳይሆን ነገር ግን በተቃራኒው የክርስቶስን ስም የሚጠሩ ክርስቲያኖች ሁሉ በእያሉበት ቦታ ሆነው የክርስትና እምነት መሰረታዊ እሴቶችን ለዓለም በተቀናጀ መልኩ እንዲያቀርቡ መንፈስ ቅዱስ ይረዳቸው ዘንድ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለአንድ ሳምንት ለየት ባለ ሁኔታ የምታደርገው ጸሎት ነው።

በእዚህም መሰረት በዓለም ዙሪያ የሚገኙ 1.3 ቢልዮን የሚሆን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በያሉበት አብያተ ክርስቲያናት እና ቁምሳናዎች ውስጥ ከጥር 09-16/2012 ዓ.ም ድረስ ለአንድ ሳምንት ያህል “የሚያስገርም ደግነት አሳዩን” (የሐዋ. 28፡2) በሚል መሪ ቃል በሚደረገው የጸሎት ሳምንት ላይ የሚሳተፉ ሲሆን ለእዚህ ለዘንድሮ 2012 ዓ.ም ለአንድ ሳምንት ያህል ለክርስቲያኖች አንድነት ለሚደርገው ጸሎት የሚሆን መሪ ቃል እንዲመርጡ እንድል የተሰጣቸው በማልታ ደሴት ላይ የሚኖሩ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቄሳውስት እና ምዕመናን መሆናቸውም ተገልጹዋል።

በሐዋርያት ሥራ በምዕራፍ 28 ላይ ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ እና ሌሎች ጓደኞቹ ቅዱስ ወንጌልን ለመስብከ በመርከብ ወደ ጣሊያን ጎዞ ያደርጉ በነበረበት ወቅት በባሕር ላይ ከፍተኛ አውሎ ነፋስ ተነስቶ መርከባቸው ከቋጥኝ ጋር ተላትማ አደጋ ከደርሰባት በኋላ በተአምር ተርፈው ማልታ በምትባል ደሴት ላይ በደረሱበት ወቅት “የደሴቲቱ ነዋሪዎችም የሚያስገርም ደግነት አሳዩን፤ ዝናብና ብርድ ነበርና እሳት አንድደው ሁላችንን ተቀበሉን” በሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተንተርሰው ይፋ ያደረጉት መሪ ቃል ሲሆን በእዚህም መሰረት ይህንን የማልታ ደሴት ነዋሪዎች መልካም አብነት በመከተል በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ክርስቲያኖች በሙሉ በተለያዩ አሰቸጋሪ በሚባሉ ሁኔታዎች የተነሳ ከአገር / ወገኖቻቸውን ጥለው የሚሰደዱ ሰዎችን ክርስቲያኖች ከማግለል እና ድንበሮቻቸውን ከመዝጋት ይልቅ ተቀብለው ያስተናግዱ ዘንድ እግዚኣብሔር ልባቸውን እንዲያራራ በማሰብ የሚደረግ የጸሎት ሳምንት ነው።

18 January 2020, 13:41