ፈልግ

ብፁዕ ሊቀጳጳስ አቡነ አንቷን ካሚሌሪ ቅድሰት መንበር እንደራሴ በኢትዮጵያ  በመሆን ተሾሙ ብፁዕ ሊቀጳጳስ አቡነ አንቷን ካሚሌሪ ቅድሰት መንበር እንደራሴ በኢትዮጵያ በመሆን ተሾሙ 

ብፁዕ ሊቀጳጳስ አቡነ አንቷን ካሚሌሪ ቅድሰት መንበር እንደራሴ በኢትዮጵያ በመሆን መሾማቸው ተገለጸ።

ቅድሰት መንበር እንደራሴ በኢትዮጵያ ብፁዕ ሊቀጳጳስ አቡነ አንቷን ካሚሌሪ አዲስ አበባ ገቡ
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ታህሳስ 8 ቀን 2012 ዓ.ም በቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለብፁዕ ሊቀጳጳስ አቡነ አንቷን ካሚሌሪ የቅድሰት መንበር እንደራሴ በኢትዮጵያ ደማቅ አቀባበል አደረጉላቸው፡፡ በመቀጠልም በቅድስት መንበር (ቫቲካን) ኤምባሲ ሲደርሱ ካህናት፣ ገዳማዊያን/ያት፣ የምእመናን ተወካዮች እና የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተቋማት ሃላፊዎች በዝማሬና በእልልታ የቅዱስ አባታችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ፍራንቼስኮስ ተወካይ ወደ ኢትዮጵያ በሰላም በመምጣታቸው ተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡ በተለይም ከብፁዕ ሊቀጳጳስ አቡነ አንቷን ካሚሌሪ ጋር በትብብር ለመስራት ያለቸውን ዝግጁነት ገልፀውላቸዋል፡፡

እርሳቸውም በበኩላቸው ስለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል አመስግነው በተልይም አቀባበሉ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ለቅዱስ አባታችን ያላት ፍቅርና አክብሮት ይመሰክራል በማለት ደስታቸውን አካፍለዋል፡፡ የቅዱስ አባታችን ሰላምታ እና አባታዊ ቡራኬ ለመላው ኢትዮጵያውያን ካቶሊካዊያን አስተላልፈዋል፡፡
ብፁዕ ሊቀጳጳስ አቡነ አንቷን ካሚሌሪ በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የቅድሰት መንበር እንደራሴ እና የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተወካይ እንዲሁም በሶማሊያ የቅድስት መንበር ልዩ ተወካይ በመሆን ቤተክርስያንን ያገለግላሉ፡፡

20 December 2019, 13:38