ፈልግ

ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን  

ለሰላም የቆመ ሕዝብ ለብልጽግና ቅርብ ነው

በመላው ዓለም ሆነ በሀገራችን በየጊዜው የወንድማማችነትንና አብሮ የመኖርን በጐ መንፈስ የሚፈታተኑ ሁኔታዎች በግልም ሆነ በሕብረት ለመኖር ተግዳሮቶች እየሆኑ ነው፡፡ ይህንንም ችግር ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በጥቅምት 27 ቀን 2012 ዓ.ም. የመድኃኔዓለም ክብረ በዓል ቀን በመላው አገሪቱ የሰላም ጸሎት ተደርጓል፡፡

ይህን መሠረት በማድረግ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን ዘኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በሰጠቻቸው ኃላፊነት እንዲሁም የአገራችን  መንግሥት  በጣለባቸው ኃላፊነት ሁሉም ወገን ለሰላም እንዲቆም  ዳግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ብፁዕ ካርዲናል ይህን የተናገሩት በአዲስ አነባ ሃገረስብከት መድኃኔዓለም ቁምስና የክብረ በዓሉን ስርዓተ ቅዳሴ የሰላም ጸሎቱን በሚመሩበት ወቅት ነው፡፡ ከጥቅም 11 ቀን 2012 ዓ. ም. ጀምሮ በሀገራችን በሰላም መደፍረስ ምክንያት ሕይወታቸው ላጡ ወገኖች ሁሉ እግዝአብሔር ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት እንዲያኖርና ለቤተሰባቸው መጽናናትን እንዲሰጥ እና በዚህ አሳዛኝ  ድርጊት ጉዳት የደሰባቸው ወገኖች ሁሉ እግዚአብሔር ፊውስ እንዲሰጣቸውበጸሎት አስበዋቸዋል፡፡ "በማወቅ ሆነ ባለማወቅ ይህን ግጭት የፈጠሩና የተባበሩ ሁሉ የተነሱበት ሃሳብ በሰላም መነጋገር እየተቻለ በደረሰው ጥፋት አዝነናል" ብለዋል፡፡  በተጨማሪ እንዚህ ወገኖች የሰው ልጅ ክቡርነትን ተገንዝበው ዳግም ወደዚህ ድርጊት እንዳይመለሱ በመጠየቅ እና  የጐዱትን ሕብረተሰብ እንዲክሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአገራችን  ሰላም ሰፍኖ ሁሉም የሰላሙ ተጠቃሚ እንዲሆን  የተጀመረው የሰላም ጥረት ውጤታማ እንዲሆን   ካቶሊካዊያን እና በጎ ፈቃድ ያላቸው ወገኖች ሁሉ  ተስፋ ባለመቁረት ጸሎት እንዲቀጥሉ   አሳስበዋል፡፡ በማያያዝም  በመላው ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የቅዱስ ፍራንቼስኮስ የሰላም ጸሎት ምዕመናን ሁሉ በየዕለቱ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት ጥሪውን በመቀበል ጥቅምት 27 ቀን 2012 ዓ.ም. መላውን ሠራተኛ በመሰባሰብ ለሀገራችን ሰላም ጸሎት ተደርጓል፡፡  በቀጣይነት ሁሉም ሠራተኛ ለሀገራችን ሰላም መስፈን በግልም ሆነ በጋራ ጥረቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ክቡር አባ ተሾመ ፍቅሬ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጸ/ቤት ዋና ጸሐፊ  አሳሳበዋል፡፡

08 November 2019, 12:34