ፈልግ

በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን የሚረዳው የካቶሊክ ቤተክርስትያን የእርዳታ መስጫ ተቋም የሚሰራባቸው አከባቢዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን የሚረዳው የካቶሊክ ቤተክርስትያን የእርዳታ መስጫ ተቋም የሚሰራባቸው አከባቢዎች  

በክርስቲያኖች ላይ እየደረሰ የሚገኘው ስደት እና ወከባ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ።

በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን የሚረዳው የካቶሊክ ቤተክርስትያን የእርዳታ መስጫ ተቋም በቅርቡ ባወጣው አመታዊ ሪፖርት እንደ ገለጸው በያዝነው የጎርጎሮሳዊያኑ 2019 ዓ.ም በዓለማችን ዙሪያ በሚገኙ በ20 አገራት ውስጥ የሚገኙ ክርስቲያኖች ለከፍተኛ ስደት መዳረጋቸውን ድርጅቱ ይፋ ካደረገው ሪፖርት ለመረዳት ተችሉዋል። ድርጅቱ በጥቅምት 13/2012 ዓ.ም ባወጣው አመታዊ ሪፖርት ጨምሮ እንደ ገለጸው በክርስቲያኖች ላይ ስልታዊ የሆኑ ጥቃቶች እየተፈጸሙ መሆናቸውን የገለጸ ሲሆን ይህ ጥቃት በአፍሪካ እና በደቡብ እስያ አገርት ሁኔታው እየተባባሰ መሄዱን ጨምሮ ገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

“አሁን የምንገኝበት ሁኔታ እና የምንኖረው ሕይወት ዘላቂ በሆነ ውጥረት የተሞላ ነው፣ ምክንያቱም ማን ይሁን የት እና መቼ እንደሆነ ማንም ባያውቅውም በሆነ ቦታ እና ሥፍራ ላይ አንድ ቀን ጥቃት እንደ ሚፈጸም ግን አዕምሮዋችን ያውቃል” በማለት የሁኔታውን አሳሳቢነት እና በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸመውን ከፍተኛ ሽብር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያንትን የሚረዳው የካቶሊክ ቤተክርስትያን የእርዳታ መስጫ ተቋም የገለጹት በፓኪስታን የካራቺ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ካርዲናል ጆሴፍ ኩትስ ድርጅቱ ባወጣው አመታዊ ሪፖርት እንደ ገለጸው በአሁኑ ወቅት 300 ሚልዮን የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ለከፍተኛ ስደት እና እንግልት መዳረጋቸውን ጨምሮ ገልጸዋል።

በመስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ-ስረዓት ላይ መሳተፍ፣ የክርስቲያን ማህበረሰብን መንፈሳዊ ሕይወት የሚያነቃቁ ሐዋርያዊ የሆኑ ትምሕርቶችን እና እንቅስቃሴዎችን ማደረግ እና ማስተዋወቅ፣ ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸውን ምልክቶችን መጠቀም ወይም በቀላሉ እምነትን የሚገልጹ ተግባራትን ማከናወን፣ ሐይማኖትን በነጻነት መግለጽ 20 በሚሆኑ የዓለማችን አገራት ውስጥ እነዚህን ተግባራት በነጻነት የመግለጽ መብት እየታገደ እና እየታፈነ መምጣቱን የገለጸው ሪፖርቱ በእዚህ የተነሳ የክርስቲያኖችን ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥሉ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆናቸውን ጨምሮ ገልጹዋል።

 “በሃይማኖታቸው ምክንያት በክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰው ስደት ብዙ ገጽታዎች ሊኖሩት ይችላሉ” በማለት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን ለሚረዳው የካቶሊክ ቤተክርስትያን የእርዳታ መስጫ ተቋም የገለጹት በፓኪስታን የካራቺ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ካርዲናል ጆሴፍ ኩትስ፣ በኢራቅና በሶሪያ በሚገኙ ክርስቲያኖች እና ዛይዲ በመባል በሚታወቁ ማኅበረሰቦች ላይ እስላማዊ መንግስት እመሰርታለሁ የሚለው አይሲስ በመባል የሚታወቀው አሸባሪ ድርጅት በጭካኔ የተሞላ ጥቃት መፈጸሙ የሚታወስ ሲሆን ከእዚህ በቀጥታ ከሚከናወኑት ጥቃቶች ባሻገር በተቀነባበረ መልኩ መድልዎ፣ በቃላት የሚፈጸሙ የሽብር ተግባራት፣ ዝርፊያ፣ ዛቻ፣ ማስፈራሪያ፣ ጠለፋ እና በግዳጅ እምነታቸውን እንዲቀይሩ በሚደረጉ ተግባራት ምክንያት ክርስቲያኖች መብታቸውን እየተገፈፉ ወይም መብታቸው እየተገደበ መምጣቱን ሪፖርቱ ጨምሮ ገልጹዋል።

በፓኪስታን የካራቺ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ካርዲናል ጆሴፍ ኩትስ፣ በችግር ላይ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን የሚረዳው የካቶሊክ ቤተክርስትያን የእርዳታ መስጫ ተቋም ጨምረው እንደ ገለጹት ከ 200 ሚሊዮን በላይ የሚሆን የሕዝብ ብዛት ባላት በፓኪስታን ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ክርስትያኖች እንደ ሚገኙ የገለጹ ሲሆን ክርስቲያኖች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደ ሚገኙ ጨምረው ገልጸዋል። በእየ አመቱ በፓኪስታን በሚገኙ በቁጥር አናሳ በሆኑ ክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸመው ቀጥተኛ ጥቃት እና በተዘዋዋሪ በተቀናጀ መልኩ በእጅ አዙር በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸመው ወከባ እየጨምረ መምጣቱን የገለጹ ሲሆን አሰቸጋሪ በሚባሉ ወቅቶች ውስጥ እንኳን ሳይቀር በችግር ላይ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን የሚረዳው የካቶሊክ ቤተክርስትያን የእርዳታ መስጫ ተቋም የሚያደርገውን ድጋፍ መቀጠሉ በፓኪስታን ለሚገኙ ክርስቲያኖች ከፍተኛ ማበረታቻ ነው ብለዋል።

በቡርኪና ፋሶ እና በሲሪላንካ በክርስቲያኖች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች

በችግር ላይ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን የሚረዳው የካቶሊክ ቤተክርስትያን የእርዳታ መስጫ ተቋም በዓለም ዙሪያ በሚገኙ በመላው ክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰው ስደት እና ጥቀታ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከ2017-2019 ዓ.ም ባሉት ሁለት አመታት ውስጥ ብቻ ከመቼው ጊዜ በላይ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከፍተኛ የሆነ ስደት እና እንግልት በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ክርስቲያኖች ላይ መደረሱን በሪፖርቱ ጨምሮ የገለጸ ሲሆን በመካከለኛው ምስርቅ፣ በኤሽያ አህጉር፣ በአንድ አንድ የአፍሪካ ሀገራት በተለይም በሊቢያ፣ በኒጀር፣ በናይጄሪያ፣ በመካከለኛው የኮንጎ ሪፖብሊክ፣ በግብጽ፣ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ደግሞ በቡርኪና ፋሶ በሚገኙ ክርስቲያኖች ላይ ቀጥተኛ እና ስልታዊ በሆነ መልኩ አክላዊ እና አእምሮኣዊ ጥቃቶች በተከታታይ እይተፈጸሙ እንደ ሚገኙ ዘግቡዋል።

እነዚህ ጥቃቶች በቀጣይነት በግለሰብ፣ በቤተሰብ፣ በማኅበረሰብ፣ በሀገረሰብ እና በቤተክርስቲያን ደረጃ በተከታታይ እይተፈጸሙ የሚገኙ የተቀነባበሩ ጥቃቶች እንደ ሆነ ከሚወጡት መረጃዎች ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በእዚህም ምክንያት በክርስቲያኖች ላይ ከፍተኛ የሆነ ስደት እያስከተለ መሆኑ ይታወቃል።

እንደ ጎርግሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከ2017-2019 ዓ.ም. ባሉ ሁለት አመታት ውስጥ ብቻ 215 ሚልዮን በሚሆኑ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ክርስቲያኖች ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከፍተኛ ስደት እና መከራ እንደ ተቃጣባቸው ሪፖርቱ ጨምሮ የገለጸ ሲሆን እነዚህ ጥቃቶች በዓለማችን ዙሪያ በሚገኙ 50 ሀገራት ውስጥ እንደ ተፈጸሙም ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ከእነዚህ አምሳ አገራት ውስጥ ደግሞ በ20 አገራት ውስጥ በክርስቲያኖች ላይ የተፈጸመው የተቀናጀ እና ስልታዊ ጥቃት ከፍተኛውን ድርሻ እንደ ሚይዝ ጨምሮ ተገልጹዋል።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ2017 ዓ.ም. በክርስቲያኖች ላይ ከፍተኛ ስደት ከደረሰባቸው 50 ሀገራት ውስጥ በ20 ሀገራት በሚገኙ ክርስቲያኖች ላይ የደረሰው ከፍተኛ ስደት የተፈጸመው ISS ወይ ዳይሽ በሚባለው ጽንፈኛ የሙስሊም አሸባሪ ቡድን አማካይነት የተፈጸመው ስደት እንደ ሆነ ለመረዳት የታቸለ ሲሆን በሰሜናዊ የናይጄሪያ ግዛት በክርስቲያኖች ላይ እይተፈጸመ የሚገኘው ጥቃት አሁን ጋብ ያለ ቢመስልም ባለፉት አመታት ያስከተለው ጥፋት እና ስደት ከፍተኛ እንደ ነበረ ይታወሳል።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በክርስቲያኖች ላይ ስደት በከፍተኛ ሁኔታ የተከሰተባቸው ሀገሮች ውስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀሱት አገራት የመን፣ ሊቢያ፣ አፊጋንስታን፣ ፓኪስታን፣ ሱዳን፣ ኢራን፣ ሶሪያ እና ኢራቅ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ አገራት ሲሆኑ በዚህ ስደት ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ክርስቲያኖች ለስደት እና ለሞት፣አብያተ ክርስቲያኖቻቸው እና ስርዓተ-አምልኮ የሚፈጽሙባቸው ሥፍራዎች ለወድመት መዳረጉን በችግር ላይ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን የሚረዳው የካቶሊክ ቤተክርስትያን የእርዳታ መስጫ ተቋም በዓለም ዙሪያ በሚገኙ በመላው ክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰው ስደት እና ጥቀታ በተመለከተ በጥቅምት 13/2012 ዓ.ም በሮም ከተማ ከሰጠው መግለጫ ለመረዳት ተችሉዋል።

በዓለም ዙሪያ በተለያዩ ምክንያቶች ስደት እና መከራ የሚደርስባቸውን ክርስቲያኖች በመርዳት የሚታወቀው የካቶሊክ የእርዳታ መስጫ ተቋም በመላው ዓለም በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ስደት እና መከራ በሚፈጸምባቸው 140 ሀገራት ውስጥ በመንቀሳቀስ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደርገ የሚገኝ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እርዳታ ሰጪ ድርጅት እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን ይህንን እርዳታ የሚያደርገው ለካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ብቻ ሳይሆን ለመላው የክርስቲያን ማኅበረሰብ እንደ ሆነም ተያይዞ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
25 October 2019, 15:46