ፈልግ

በዓለ ሆሳዕና በኢራቅ፣ በዓለ ሆሳዕና በኢራቅ፣ 

የኢራቅ ቤተክርስቲያን ብዙ ሰማዕታት የሚገኙባት መሆኗ ተገለጸ።

ፓትሪያር ሉዊስ ራፋኤል ሳኮ፣ ቅዱስነታቸው በዚህ አስቸጋሪ ወቅት በመካከላቸው መገኘታቸው ለአገሩ ሕዝብ በሙሉ ትልቅ ድጋፍ እና ብርታት እንደሚሆናቸው አስረድተው፣ በከፍተኛ ናፍቆትም የሚጠብቁት መሆኑን ገልጸዋል።

በኢራቅ ለምትገኝ እና የምስራቅ ቤተክርስቲያን ስርዓተ አምልኮን የምትከተል ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ሉዊስ ራፋኤል ሳኮ፣ ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በላኩት መልዕክታቸው፣ ወደ ኢራቅ የሚያደርጉት ሐዋርያው ጉብኝት እጅግ ደስ እንዳሰኛቸው እና በከፍተኛ ናፍቆትም የሚጠብቁት መሆኑን ገልጸዋል። 

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ፓትሪያርክ ሉዊስ ራፋኤል ከዚህ በፊት ቫቲካንን በጎበኙበት ወቅት፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ኢራቅን ለአንድ ቀን እንኳን ጎብኝተው መስዋዕተ ቅዳሴን ቢያሳርጉ፣ ከሌሎች አብያተ ክርስትያናት ጋር የሕብረት ጸሎት ቢያደርጉ፣ ከሌሎች የሃይማኖት መሪዎች እና ከመንግሥት ባለስልጣናት ጋር ሰላምታን ቢለዋወጡ በማለት የግብዣ ጥሪ ቢያቀርቡላቸውም በሃገራቸው የፖለቲካ አለመረጋጋትና የጸጥታ ችግር ምክንያት ሳይሳካ መቆየቱን የሚታወስ ነው።

ብጹዕ ፓትሪያርክ ሉዊስ ራፋኤል፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እስካሁን ለኢራቅ ክርስቲያኖች ያደረጉትን የጸሎት ድጋፍ፣ ለመላው የኢራቅ እና የአካባቢው አገሮች ሕዝቦች ያላቸውን ፍቅር በማስታወስ በኢራቅ በምትገኝ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ስም ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል። ብጹዕ ፓትሪያርክ ሉዊስ ራፋኤል ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መልዕክታቸውን የላኩት እስከ ነሐሴ 7/2011 ዓ. ም. ድረስ በኢራቅ ግዛት በሆነው የኩርዲስታን ክፍለ ሃገር በመካሄድ ላይ ባለው ዓመታዊ የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ወቅት መሆኑ ታውቋል።

ምዕመናንም የሚካፈሉበት የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ፣

ብጹዕ ፓትሪያር ሉዊስ ራፋኤል ሳኮ በመልዕክታቸው በመካሄድ ላይ ያለውን የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በአገሪቱ ከሚገኙ ሀገረስብከቶች የተላኩ የምዕመናን ወገኖችም የሚካፈሉ መሆናቸን አስታውቀዋል። የብጹዓን ጳጳሳቱ ጉባኤ የተጀመረው፣ በቆጵሮስ የማሮናይት ስርዓት አምልኮን የምትከተል ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት የሆኑት ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ ሱዌፍ በመሩት የሱባኤ ስነ ስርዓት መሆኑ ታውቋል። ጉባኤውን ከነሐሴ 2/2011 ዓ. ም. ጀምሮ ብጹዓን ጳጳሳት ብቻ የሚካፈሉት መሆኑ ታውቋል።

የወንጌል መልዕክተኛ እና ሰማዕት ቤተክርስቲያን፣

አነስተኛ የምዕመናን ቁጥር እንዳላቸው የገለጹት ብጹዕ ፓትሪያር ሉዊስ ራፋኤል ሳኮ፣ ለመላው ቤተክርስቲያን እና ለሌሎች አብያተክርስቲያናት ትልቅ ምሳሌ እና ምልክት መሆናቸውን አስረድተዋል። የኢራቅ ቤተክርስቲያን ከመጀመሪያዎቹ ክፍለ ዘመናት ጀምራ እስከ ቻይና ድረስ የወንጌል ተልእኮዋን የተወጣች፣ ብዙ ሰማዕታት ያሉባት፣ ወደፊትም ቢሆን የሚገኙባት ቤተክርስቲያን መሆኗን ገልጸዋል።

ከእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር ስቃይን በጋራት፣

ብጹዕ ፓትሪያር ሉዊስ ራፋኤል ሳኮ በመልዕክታቸው በአገራቸው የሚደርስባቸውን የስቃይ እና የችግር ሕይወት ከእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር የሚጋሩ መሆናቸውን አስረድተው፣ ይህ የጋራ ስቃይ ወደፊት ለሚመጣው የመልካም ሕይወት ጥሩ ምሳሌ እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

የቅዱስነታቸው የኢራቅ ጉብኝት ትልቅ ድጋፍ ይሆናል፣

ቅዱስነታቸው ወደ ኢራቅ የሚያደርጉትን ሐዋርያው ጉብኝት በደስታ የተቀበሉ መሆናቸውን የገለጹት ብጹዕ ፓትሪያር ሉዊስ ራፋኤል ሳኮ፣ ቅዱስነታቸው በዚህ አስቸጋሪ ወቅት በመካከላቸው መገኘታቸው ለአገሩ ሕዝብ በሙሉ ትልቅ ድጋፍ እና ብርታት እንደሚሆናቸው አስረድተው፣ በከፍተኛ ናፍቆትም የሚጠብቁት መሆኑን ገልጸዋል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
07 August 2019, 15:19