ፈልግ

የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶች በጸሎት ስነ ስርዓት ላይ፣ የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶች በጸሎት ስነ ስርዓት ላይ፣  

በግብጽ ያለ መንግሥት ፍቃድ የታነጹ ቤተክርስቲያኖች የሕጋዊ ይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ተሰጣቸው።

ከዚህ በፊት ያለ መንግሥት ፍቃድ ለታነጹት በርካታ የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ይዞታ ላላቸው የአምልኮ ስፍራ፣ መንግሥት የባለቤትነት ሕጋዊ እውቅናን እየሰጠ መሆኑ ታውቋል። ባለፉት ጣቂት ቀናት ብቻ 88 ያለ መንግሥት እውቅና እና ፍቃድ ለታነጹት ቤተክርስቲያኖች ሕጋዊ የይዞታነት እውቅናን መስጠቱ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ከሦስት ዓመታት ገደማ በፊት የግብፅ ፓርላማ የአምልኮ ቦታዎችን ግንባታ እና አያያዝ በተመለከተ ሕግ ማውጣቱ ይታወሳል። ይህን ሕግ ተከትሎ፣ ተግባራዊነቱንም ለማስፈጸም በሚል ዓላማ፣ ከዚህ በፊት በአገሪቱ ያለ መንግሥት ፍቃድ የታነጹ 1,100 ለሚሆኑ ቤተክርስቲያኖች እና የአምልኮ ሥፍራዎች እንዲሁም ተያያዥነት ላላቸው የቤተክርስቲያን ሕንጻዎች ሕጋዊ የባለ ቤትነት እውቅናን መንግሥት መስጠቱን ፊዴስ የተሰኘ የዜና ማዕከል አስታውቋል።

በፕሬዚዳንቱ ውሳኔ ተፈቀደ፣

ንብረትነታቸው የቤተ ክርስቲያን የሆኑት በርካታ ሕንጻዎች ከጎርጎሮሳዊው 2016 ዓ. ም. ከወጣው አዲስ ሕግ አስቀድሞ የታነጹት መሆናቸው ታውቋል።  በግብጽ እንደ ጎርጎሮሳዊው 1934 ዓ. ም. የወጣው ሕግ፣ በአገሪቱ የሚታነጹ የአምልኮ ሥፍራዎች፣ ወደ ትምህርት ተቋማት፣ ውሃ ወደ ሚሄዱባቸው ቦዮች ፣ ወደ መንግሥት ሕንፃዎች ፣ ወደ ባቡር ሐዲዶች እና ሌላው ቀርቶ ወደ መኖሪያ አካባቢዎች መቅረብ እንደሌለባቸው የሚያዝ መሆኑ ታውቋል። አሁን የሚታነጹት አዳዲስ ቤተክርስቲያኖች በአገሪቱ ፕሬዚዳንት ውሳኔ እና ፍቃድ ብቻ የሚገነቡ መሆናቸው ታውቋል። በተግባር ይውላል የተባለው አዲሱ ሕግ፣ በቁጥር በርካታ ክርስቲያኖች በሚኖሩበት በላይኛው ግብጽ፣ በዘፈቀድ የሚገነቡትን የአምልኮ ስፍራዎችን ያግዳል ተብሏል።

በተለያዩት አካባቢዎች የሚኖሩ የክርስቲያን ማሕበረሰብ በጎርጎሮሳዊው 1934 ዓ. ም. የወጣው ሕግ ችላ በማለት በሚፈልጉት አካባቢ እና ጊዜ ቤተክርስቲያንን ሲገነቡ መቆየታቸው ታውቋል። ብዙን ጊዜ በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱ እስላማዊ ታጣቂዎች በእነዚህ የአምልኮ ስፍራዎች ጥቃት እንደሚያደርሱ እና በዚህም ምክንያት የብዙዎች ሕይወት መጥፋቱ ታውቋል።  እነዚህን አደጋዎች ለመከላከል እና ሌሎችንም ችግሮች ለማስወገድ በሚል ዓላማ፣ በ1934 ዓ. ም. የወጣውን ሕግ ባማሻሻል፣ የግብጽ ፓርላማ እንደ ጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር በ2014 ዓ. ም. የክርስቲያኖችን የአምልኮ ነጻነት የሚያስከብር ሕግ እንዲወጣ ማድረጉ ታውቋል።

የአምልኮ ስፍራ፣

እንደ ጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር ነሐሴ 30/2016 ዓ. ም. የተቋቋመው ልዩ ኮሚቴ፣ በአገሪቱ የታነጹት ቤተክርስቲያኖች ሕጋዊ እውቅናን አግኝተው ይሁን ሳያገኙ የተገነቡ መሆናቸው እንዲጣራ ትዕዛዝ ማስተላለፉ ታውቋል። ሕጋዊ ፈቃድ ሳይሰጣቸው የታነጹ ቤተክርስቲያኖች ካሉ፣ ሕጋዊ ፈቃድ እና የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ እንዲኖራቸው የሚል ትዕዛዝ ፓርላማው ማስተላለፉ ታውቋል።

ግብጽ ካላት 95 ሚሊዮን ሕዝብ መካከል 10 ከመቶ የሚሆነው የክርስትና እምነት ተከታይ ሲሆን ከእነዚህም አብዛኛው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ መሆኑ ታውቋል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
08 August 2019, 16:30