ፈልግ

በቻይና ሕዝባዊት ሪፓብሊክ የተሰየሙት ካቶሊካዊ ጳጳስ፣ ብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ ሹ ኋንጉዌ፣ በቻይና ሕዝባዊት ሪፓብሊክ የተሰየሙት ካቶሊካዊ ጳጳስ፣ ብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ ሹ ኋንጉዌ፣ 

በቻይና ሕዝባዊት ሪፓብሊክ ተጨማሪ ካቶሊካዊ ጳጳስ መሰየማቸው ተገለጸ።

በቻይና ሕዝባዊት ሪፓብሊክ አዲስ ካቶሊካዊ ጳጳስ መሰየማቸውን፣ ትናንት ነሐሴ 22/2011 ዓ. ም. ቫቲካን አስታወቀ። በቻይና ሕዝባዊት ሪፓብሊክ የተሰየሙት አዲሱ ጳጳስ፣ ቅድስት መንበር ከቻይና ሕዝባዊት ሪፓብሊክ መንግሥት ጋር፣ ያለፈው ዓመት በመስከረም 12/2011 ዓ. ም. ከደረሰችበት ጊዜያዊ ስምምነት ወዲህ ሁለተኛው መሆናቸው ታውቋል። ለብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ ሹ ኋንጉዌ የጵጵስና ማዕረግ የተሰጣቸው በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ወሳኔ መሠረት መሆኑ ታውቋል። ብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ ጹ ሆንጅዊ፣ በቻይና የሃንዞንግ (ሻንክሲ) ተባባሪ ጳጳስ ሆነው የሚያገለግሉ መሆናቸው ታውቋል። በቻይና ሕዝባዊት ሪፓብሊክ ውስጥ ከሁለቱ ወገኖች ስምምነት ወዲህ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የተሰጠው የጵጵስና ማዕረግ በቻይና ሕዝባዊት ሪፓብሊክ መንግሥትና በቅድስት መንበር መካከል በማደግ ላይ ያለው የጋራ ውይይት መልካም ፍሬ መሆኑን ቫቲካን አስታውቋል። 

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በመስከረም 12 ቀን 2011 ዓ. ም. በቻይና ሕዝባዊት ሪፓብሊክ መንግሥትና በቅድስት መንበር መካከል የተደረሰው ጊዜያዊ ስምምነት፣ በቻይና የቅድስት መንበር ዕውቅና ያልነበራቸው ጳጳሳት እውቅናን እንዲያገኙና በቅድስት መንበር ትዕዛዝና የበላይነት በመመራት ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን እንዲያበረክቱ የሚጠይቅ ሲሆን በተጨማሪም ወደ ፊት በየጊዜው የሚሰጥ ስመተ ጵጵስና በሁለቱ አገሮች ስምምነት እንዲከናወን የሚጠይቅ እንደሆነ ታውቋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቻይና ሕዝባዊት ሪፓብሊክ መንግሥትና በቅድስት መንበር መካከል የተፈረመውን ጊዜያዊ ስምምነት በማስመልከት ለቻይና ካቶሊካዊ ምዕመናን በላኩት መልዕክታቸው፣ ጊዜያዊ ስምምነቱ በቻይና ሕዝባዊት ሪፓብሊክና በቅድስት መንበር መካከል የተሻለ ግንኙነትን ለመፍጠር ያግዛል ብለው በመካከላቸው የነበረውን መራራቅ ለማጥበብ ይረዳል ብለው፣ ስለዚህም መላው የቻይና ካቶሊካዊ ምእመናን በጋራ ሆነው የወንጌልን መልካም ዜና ለማብሰር እንዲነሳሱ አደራ ማለታቸው ይታወሳል።

የቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል ዳይሬክተር የሆኑት ክቡር አቶ ማቴዎ ብሩኒ፣ በቫቲካን ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ በሰጡበት ወቅት እንዳስረዱት፣ የጵጵስና ማዕረግ የተቀበሉት ብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ ሹ ኋንጉዌ፣ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንችስኮስን ትዕዛዝ እና አደራ የተቀበሉ መሆናቸውን ገልጸው፣ ስመተ ጵጵስናቸውም፣ ያለፈው ዓመት በመስከረም ወር 2011 ዓ. ም. በቻይና ሕዝባዊት ሪፓብሊክ መንግሥትና በቅድስት መንበር መካከል በተደረሰው ጊዜያዊ ስምምነት መሠረት መሆኑን አስረድተዋል።

የብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ ሹ ኋንጉዌ የጵጵስና ስያሜ፣ ጊዜያዊ ስምምነቱ በቻይና ሕዝባዊት ሪፓብሊክ እና በቅድስት መንበር መካከል ከተደረሰ ጊዜያዊ ስምምነት ወዲህ ሁለተኛው መሆኑ ታውቋል። በቻይና ሕዝባዊት ሪፓብሊክ ውስጥ የማንጎሊያ ጳጳስ ሆነው የተመረጡት ብጹዕ አቡነ አንጦኒዮስ ያዎ ሹን፣ በሁለቱ አገሮች መካከል ከተደረገው ስምምነት በኋላ የተሰየሙት የመጀመሪያው ጳጳስ መሆናቸው ታውቋል።

የብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ ስመተ ጵጵስና መስዋዕተ ቅዳሴን ስነ ስርዓት የመሩት፣ የኩንሚንግ (ዩናን) ሀገረ ስብከት ጳጳስ እና የቻይና ሕዝባዊት ሪፓብሊክ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ፕሬዚደንት የሆኑት ብጹዕ አቡነ አንጦኒዮስ ማ ይንግሊን መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ስነ ስርዓቱም የተፈጸመው በቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል መሆኑን ኤዢያ ንውስ አስታውቋል። በመስዋዕተ ቅዳሴው ስነ ስርዓት ላይ ሌሎች 5 ብጹዓን ጳጳሳት፣ 80 ካሕናት እና በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን የተገኙ መሆናቸውን የዜና ማዕከሉ አክሎ አስታውቋል።

በቻይና ሕዝባዊት ሪፓብሊክ ውስጥ የሃንዞንግ (ሻንክሲ) ሀገረ ስብከት ተባባሪ ጳጳስ ሆነው የተሰየሙት ብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ ሹ ኋንጉዌ የተወለዱት ጥር 8 ቀን 1967 ዓ. ም. ሲሆን ዕድሜያቸው 44 ዓመት መሆኑን ኤዢያ ኒውስ ገልጿል። በ1985 ዓ. ም. ወደ ዘርዓ ክህነት ትምህርት ቤት የገቡት ብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ ሹ ኋንጉዌ የክህነት ማዕረጋቸውን በሐምሌ ወር 1994 ዓ. ም. ከተቀበሉ በኋላ የክህነት አገልግሎታቸውንም በአንዞንግ ሀገረ ስብከት ማበርከታቸው ሲታወቅ በተመሳሳይ ዓመት በአንዘንግ ወረዳ በሚገኝ የአንዞንግ ካቴድራል የሐዋርያዊ አገልግሎት አስተባባሪ ሆነው ማገልገላቸው ታውቋል። አቡነ እስጢፋኖስ ሹ ኋንጉዌ፣ ከ1996 – 2000 ዓ. ም. ድረስ ሮም በሚገኝ በኡርባኒያን ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ ገብተው ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርቶችን የተከታተሉ መሆናቸው ታውቋል። ቀጥሎም ከታህሳስ ወር 2002 ዓ. ም. ጀምሮ በካናዳ ቫንኩቨር ሀገረ ስብከት ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸው ታውቋል። ቀጥሎም በሃንታይ ሀገረ ስብከት የዊስት ስትሪት ካቴድራል አገልጋይ ሆነው መሥራታቸው ታውቋል።                                 

ብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ ሹ ኋንጉዌ፣ ከእነዚህ የከፍተኛ ትምህርት እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዓመታት በኋላ ወደ አገራቸው ተመልሰው ከ2004 ዓ. ም. እስከ 2009 ዓ. ም. ድረስ በቻይና የሃንታይ ክፍለ ሀገር፣ የህዝባዊ ፖለቲካ ምክር ቤት የኮሚቴ አባል ሆነው መሥራታቸውን የኤዢያ ኒውስ ዘገባ አስታውቋል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
29 August 2019, 15:13