ፈልግ

የስሪላንካ ምዕመናን አሁንም በፍርሃት ውስጥ፣ የስሪላንካ ምዕመናን አሁንም በፍርሃት ውስጥ፣ 

ብጹዕ ካርዲናል ራንጂት የስሪላንካ ምዕመናን አሁንም በፍርሃት ውስጥ መሆናቸውን አስታወቁ።

ብጹዕ ካርዲናል ራንጂት ይህን ያስታወቁት ከቫቲካን የዜና አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ መሆኑን የዜና አገልግሎቱ ባልደረባ አመዴዎ ሎሞናከው የላከልን ዘገባ አመልክቷል። ከሦስት ወራት በፊት በስሪላንካ የተፈጸመው የአጥፍቶ ጠፊዎች ጥቃት ለ258 ሰዎች ሕይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑ ይታወሳል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በስሪላንካ ውስጥ በተለያዩት አካባቢዎች አጥፍቶ ጠፊዎች ጥቃት ያካሄዱት የክርስትና እምነት ተከታዮች የብርሃነ ትንሳኤውን በዓል ባከበሩበት እሁድ ሚያዚያ 13 ቀን 2011 ዓ. ም. እንደነበር ይታወሳል። ጥቃቱ ከተፈጸባቸው ሥፍራዎች አንዱ በዋና ከተማዉ ኮሎምቦ በሚገኝ የቅዱስ አንጦንዮስ ካቴድራል ውስጥ መሆኑን ካርዲናል ማልኮም ራንጂት ከቫቲካን የዜና አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል። ካርዲናል እንደገለጹት የቤተክርስቲያኑ ውስጣዊ ክፍል ሙሉ በሙሉ መውደሙን እና በርካታ ሰዎች የሞቱበት፣ አደጋው የደረሰባቸው በቁጥር በርካታ ሰዎች ጩሄት በማስተጋባት የሕክምና እርዳታን ሲለምኑ መደመጣቸውን በማስታወስ ገልጸዋል።

ካርዲናል ማልኮም ራንጂት ከቫቲካን የዜና አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት የሽብር ጥቃትን የፈጸመው ክፍል ማን መሆኑን ለይቶ ለማወቅ የተደረገ ጥረት አልነበረም ብለዋል። ምንም እንኳን መንግሥት አስቀድሞ በማንኛውም ሰዓት ጥቃቱ ሊፈጸም እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም ጥቃቱን ለማስቀረት በቂ ዝግጅት አላደረገም ብለዋል። ጉዳቱ እንዲደርስባቸው ዋና ምክንያት የሆነውም ይህ ነው ብለዋል።

የስሪላንካ መንግሥት በሀገሪቱ ከሚንቀሳቀስ የታሚል አማጺ ቡድን ጋር ጦርነት ባካሄደበት ወቅት ጠንካራ የደህንነት ተቋም መሥርቶ ይሰራ እንደነበር ያስታወሱት ብጹዕ ካርዲናል ማልኮም ራንጂት፣ ጦርነቱ ካበቃበት ጊዜ ጀምሮ ከዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በኩል የሚሰማ ተቃውሞ እየበረታ በመምጣቱ ምክንያት መንግሥት ያቋቋማቸውን ወታደራዊ የደህንነት ተቋሞችን ለማፍረስ መገደዱን ገልጸዋል። ይህ በሆነበት ሁኔታ ሊከሰት የሚችል አደጋ መኖሩ ግልጽ ነው ያሉት ካርዲናል ማልኮም ራንጂት መንግሥት የአደጋ ማስጠንቀቂያ መልዕክት ባሰራጨበት ወቅት የደህንነት ተቃማቱ አለመኖራቸውን ገልጸዋል።

በደረሳባቸው ጥቃት የተሰማቸው ሃዘን ከፍተኛ እንደነበር የገለጹት ብጹዕ ካርዲናል ማልኮም ራንጂት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስም በአደጋው ከፍተኛ ሃዘን የተሰማቸው መሆኑን ገልጸዋል። ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ ከባድ አደጋ ያልደረሳቸው ቢሆንም ፍርሃት አልተለየንም ብለው የሕዝባቸው የደህንነት ሁኔታ አስተማማኝ ካለመሆኑ የተነሳ በየዕለቱ በስጋት ውስጥ ይገኛል ብለዋል። ። 

22 July 2019, 17:02