ፈልግ

የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ  

የቅዱሳን ጰጥሮስ እና ጳውሎስ ዓመታዊ በዓል

እምነትን መመስከር፣ ስደት እና ጸሎት  

የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በመላው ዓለም በሚገኙ የካቶሊክ ምዕመናን ዘንድ የቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ አመታዊ ክብረ በዓል በሰኔ 22/2011 ዓ.ም. በደማቅ ሁኔታ ይከበራል። ይህንን አመታዊ ክብረ በዓል አስመክተን ያዘጋጀነውን አስተንትኖ እንደ ሚከተለው እናቀርብላችኋለን፣ ተከታተሉን።

የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለቤተክርስቲያን ግንባታ ተጨባጭ የሆነ መሰረት በመጣል የቤተ ክርስቲያን አምድ የሆኑትን ቅዱሳን ጴጥሮስን እና ጳውሎስን ማነጻጸር ይወዳሉ።

 

ሁለቱም በስብከታቸው ክርስቶስን በመመስከር ደማቸውን በማፍሰስ የክርስትና ማኅበረሰብ እንዲፈጠር መሰረት ጥለዋል።  ይህም ምስክርነታቸው ዛሬ በመስዋዕተ ቅዳሴያችን ላይ የተነበቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት እንደ ሚያመለክቱት እምነታቸውን በመመስከራቸው እና በማወጃቸው ከፍተኛ የሆነ ፈተና ገጥሞዋቸው ሰማዕት እንዲሆኑ አድርጎዋቸዋል።

የሐዋሪያት ሥራ ምዕራፍ 12:1-11 ላይ ጴጥሮስ እስር ቤት መግባቱን እና ከእስር እንዴት እንደ ተፈታ ይተርክልናል። እርሱም ንጉሥ ሂሮደስ “በሕዝብ ፊት አውጥቶ ሊያስፈርድበት አስቦ” እስር ቤት ውስጥ አስከርችሞበት ስለነበረ ገና በኢየስሩሳሌም እያለ በወንጌል ምክንያት ገጥሞት የነበረውን ጥላቻ ተለማምዶት ነበር። ነገር ግን ተዐምራዊ በሆነ መልኩ ከእስር ቤት ወጥቶ፣ ተልዕኮውን በመቀጠል በቅድሚያ ከቅድስቲቷ ሀገር በመጀመር፣ ቀጥሎ እስከ ሮም ድረስ ጉልበቱን ለክርስቲያን ማኅበረሰብ አገልግሎት በማዋል እስከ ሕይወቱ ፍጻሜ አገልግልዋል።

ጳውሎስም ቢሆን ከደረሰበት ከፍተኛ ጥላቻ በጌታ እርድታ ነጻ ወጥቶዋል። ከሙታን የተነሳው ጌታ በሚያደርግለት ጥሪ በተለያዩ የአረማዊያን ከተሞች በተመላለሰባቸው ወቅቶች ከአሳዳጆቹ እና ከባለስልጣናትም ሳይቀር ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ደርሶበት ነበር። የእርሱ ተከታይ ለነበረው ለጦሞትዮስ በጻፈው መልእክቱ ላይ የተጠቀሰው የሚያጠነጥነው በሕይወቱ ዙሪያ እና በትልእኮ ወቅት ስልገጠመው እንዲሁም ወንጌልን በማብሰር ሂደት ውስጥ ገጥመውት የነበሩትን ተግዳሮቶች ያመለክታል።

የቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ ነጻ መውጣት እነዚህ ሁለት ሐዋሪያት በጣም አስቸጋሪ በሆነ ቦታ እና አንድአንዴም በጥላቻ በተሞሉ ስፍራዎች ወንጌልን እንዲያበስሩ መልካቸውን ያሳያል።  ሁለቱም በግል እና ከቤተ ክርስቲያናቸው በኩል በገጠማቸው ተግዳሮቶች በመነሳት ዛሬ ለእኛ የሚያሳዩን እና የሚነግሩን ጌታ ሁል ጊዜም ቢሆን ከጎናችን እንደ ሚሆን፣ አብሮን እንደ ሚጓዝ፣ መቼም ቢሆን ብቻችንን እንደ ማይተውን  ያስተምሩናል። በተለይም ደግሞ በፈተናዎች ውስጥ በምንገባባቸው ወቅቶች፣ እግዚኣብሔር እጆቹን እንደ ሚዘረጋ፣ እንደ ሚረዳን፣ ከገጠሙን ተግዳሮቶች እና ስጋቶች እንደ ሚታደገን ያስተምሩናል።  ነገር ግን እኛን ወደ ኃዋላ የሚሰበን ትልቁ ጠላታችን ኃጢአያችን እንደ ሆነ ማስታወስ ይገባል። ለየት ባለ ሁኔታ በምስጢረ ንስሐ አማካይነት፣ የይቅርታን ጸጋ ተቀብለን ከእግዚኣብሔር ጋር በምንታረቅባቸው ወቅቶች ሁሉ የስህተቶቻችን ሸክም ተቃሎልን ከመጥፎ መንገዶቻችን ሁሉ እንርቃለን።  በዚህም መልኩ እኛ በቀዳሚነት ምህረትን ተቀብለን በደስታ ተሞልተን ቅዱስ ወንጌልን ለማወጅ እና ለመመስከር እንችላለን።

የሮም ከተማ ጠባቂ የሆኑት ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስ በከተማዋ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በወንድማማችነትና በመግባባት በመኖር የክርስትና እምነታቸውን ቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ በነበራቸው ወኔ እና ብርታት ተሞልተው መመስከፍር እንዲችሉ የቅዱስኑን አማላጅነት እንማጸናለን።

28 June 2019, 12:56