ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አዳዲስ ቅዱሳን እና ብጹዕንን ሰየሙ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አዳዲስ ቅዱሳን እና ብጹዕንን ሰየሙ 

የቅዱሳን ስም በሰፈረበት መዝገብ ውስጥ ስማቸው የሚካተት ቅዱሳን እና ብጹዕን ስም ይፋ ሆነ።

በሕይወታቸው ዘመን መልካም የሚባል ስነ-ምግባር ያለው ሕይወት በመኖር፣ የክርስትናን ሕይወት ተጨባጭ በሆነ መልኩ በሕይወታቸው ምስክረው ያለፉ ስምንት ሰዎች ስም በቤተክርስቲያን የቅዱሳን፣ የብጹዕን እና ታመኝ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ስም በሰፈረበት መዝገብ ውስጥ መካተቱ ተገለጸ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በቂ የሆነ ቅድመ ጥናት እና ዝግጅት ከተደረገ በኋላ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በተወሰነው ውሳኔ መሰረት በሕይወታቸው ዘመን ያከናወኑት ገድል እና ያሳዩት ተጨባጭ የሆነ የክርስትና ሕይወት ምስክርነት ተገምግሞ፣ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሕግ እና ስረዓት መሰረት በስማቸው ጸሎት ተድርጎ በእነርሱ አማላጅነት ተአምራት መፈጸሙ በመረጋገጡ የተነሳ ከስምንቱ የእግዚኣብሔር አገልጋዮች ውስጥ ሁለቱ ለቅድስና ማዕረግ፣ አንዷ ለብጽዕና ማዕረግ፣ የተቀሩት አምስቱ ደግሞ ታማኝ የእግዚኣብሔር አገልጋይ የሚል የክብር ማዕረግ መታጨታቸውን እና ይህም በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መጽደቁን ከቫቲን ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉኋል።

በግንቦት 05/2011 ዓ.ም ለቅድስና፣ ለብጽዕና እና ታማኝ የእዝጊአብሔር አገልጋይ የተሰኙትን ማዕረግ ከታጩት 8 ሰዎች መካከል አምስቱ ጣሊያናዊያን፣ ሁለቱ ብራዚላዊያን፣ አንድ ከእስፔን መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ መስፈርቱን አሙልተው የተገኙ ሁለቱ ለቅድስና ማዕረግ፣ አንዷ ለብጽዕና ማዕረግ የተቀሩት አምስቱ ደግሞ ታማኝ የእግዚኣቤር አገልጋይ ለተሰኘው የክብር ማዕረግ ታጭተዋል። በቅድስት መንበር ስር የሚተዳደረው እና የቅድስና ማዕረግ አሰጣጥ ሂደትን የሚከታተለው ጳጳሳዊ ማኅበር የበላይ አለቃ የሆኑት ካርዲናል አንጄሎ ቤቹ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ለቅድስና፣ ለብጽዕና እና ታማኝ የእግዚአብሔር አገልጋይ ለተሰኙት ማዕረግ ብቁ የሆኑትን ሰዎች ማዕረጉ እንዲሰጣቸው የሚጠይቀውን ሰነድ ቅዱስነታቸውም ተቀብለው ማጸደቃቸው ተገልጹዋል።

ይህንን መስፈርት አሟልተው ለቅድስና ማዕረግ እጩ ከሆኑት ሁለት እንስቶች መካከል በቀዳሚነት የተጠቀሱት የጣልያን አገር ተወላጅ የሆኑት መነኩሴ የነበሩ ብጽዕት ሲስተር ጁሴፒና ቫኒ በመባል የሚታወቁ መነኩሴ የሚገኙበት ሲሆን እርሳቸው እ.አ.አ በነሐሴ 7/1859 ዓ.ም በጣሊያን በሮም ከተማ ተወልደው እንደ ነበረ ከሕይወታቸው ታሪክ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን እ.አ.አ. በየካቲት 23/1911 ዓ.ም ከእዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። በሕይወት በነበሩበት ወቅት የቅዱስ ካሚሉስ ልጆች በመባል የሚታወቅ ገዳም መመስረታቸው ተገልጹዋል።

በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ለዚህ ቅድስና ማዕረግ የሚያበቃውን መስፈርት በሟሟላት ለቅድስና ማዕረግ ዕጩ የሆኑት ደግሞ በዜግነት ብራዚላዊ የሆኑ እና ያለአዳም ኃጢአት የተጸነሽ የእግዚኣብሔር እናት በመባል የሚታወቀው መንፈሳዊ ማኅበር አባል የነበሩት ብጽዕት ሲስተር ዱልቼ ሎፔዝ እንደ ሆኑ የተገለጸ ሲሆን እርሳቸውም ሳኦ ስላቫዶር ዳ ባሂን በተባለው የብራዚል ግዛት ውስጥ እ.አ.አ በግንቦት 26/1914 ተወልደው እ.አ.አ በግንቦት 22/1992 ዓ.ም ከእዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተገልጹዋል። 

ለብጽዕና ማዕረግ ዕጩ ሆነው የቅረቡት ደግሞ በዜግነት ጣሊያናዊ የሆኑ ታማኝ የእግዚኣብሔር አገልጋይ የነበሩት ሲስተር ሉቺያ የሚባሉ እንስት እንደ ሆኑ የተገለጸ ሲሆን እርሳቸው እ.አ.አ በግንቦት 26/1909 ተወልደው እ.አ.አ በነሐሴ 4/1954 ዓ.ም ከእዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

በሕይወታቸው ዘመን ታላቅ ገድል የፈጸሙ የእግዚኣብሔር አገልጋይ የሚል የክብር ስም የተሰጣቸው ደግሞ በቁጥር አምስት እንደ ሆኑ የተገለጸ ሲሆን በዚህም መሰረት በጣሊያን ውስጥ በሚገኘው የቶሪኖ አገረ ስብከት ረዳት ጳጳስ የነበሩት ጆቫኒ ባቲስታ ፒናርዲ እንደ ሆኑ የተገለጸ ሲሆን እርሳቸው እ.አ.አ በነሐሴ 152/1880 ተወልደው በነሐሴ 2/1962 ከእዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። በሕይወታቸው ዘመን ታላቅ ገድል ፈጸመው ታማኝ የእግዚኣብሔር አገልጋይ የሚል የክብር መጠሪያ ስያሜ ከተሰጣቸው ሰዎች መካከል ጣሊያናዊው አባ ካርሎ ሳለሪዮ፣ እስፔናዊው አባ ዶሜኒኮ ላዛሮ፣ ብራዚሊያዊ ወንድም ሰልቫቶሬ ዳ ካስካ፣ ጣሊያናዊ የሆኑት ሲስተር ማሪያ ሄውፍራኢዛ እንደ ሚገኙባቸው ከደረሰን መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

13 May 2019, 16:04