ፈልግ

ቅዱስ አጎስጢኖስ ቅዱስ አጎስጢኖስ  

ጌታ ሆይ ልባችን አንተን ካላገኘ ዕረፍት የለውም

የሰው ልብ አምላኩን ካገኘ ሁሉን ነገር ያገኘ መስሎ ይሰማዋል፤ ያን ጊዜ ሙሉ ደስታ ያገኛል፡፡ እግዚአብሔርን ካላገኘ ግን ምንም እንኳን ሁሉን ቢያገኝ ዘወትር ጐደሎ ሆኖ አካባቢው ባዶ መሰሎ ይሰማዋል፣ ብዙ ይመኘው የነበረ ውስጣዊ ሰላም ያጣል፡፡ ቅዱስ አውጉስጢኖስ ከአምላኩ ርቆ በነበረ ጊዜ ምንም እንኳን የሚያበቃው ገንዘብና ዕውቀት ቢኖረውም በውስጡ እየታወከ ባልተረጋጋ መንፈሰ ይኖር ነበር፡፡ ይኸውም ከፈጣሪው ርቆና ተለይቶ ስለነበረ ነው፡፡ ይህን ሁከት፣ ግርግር፣ መከራ ለማሸነፍ ብዙ ጊዜ ጥረት ያደርግ ነበር፡፡ በፍጥረቶች የሕሊና ሰላምና እርካት የማያገኝ መስሎት ይጠጋ ይቀርብ ነበር፡፡

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በዚህ ሁኔታ ከባሕሮች ከወንዞች፣ ከሐይቆች፣ ከተራራዎች፣ ከከዋክብት፣ ከፀሐይና ከጨረቃ ወዘተ … ውስጣዊ ሰላምን ተመኝቶ ይለምን ነበር፡፡ ግን እነርሱ «ከእኛ በላይ ፈልግ´ እያሉ ይመለሱለት ነበር፡፡ እንዳሉትም ከእነርሱ አልፎ ወደ ላይ ከፍ ብሎ ሲፈልግ እግዚብሔርን አገኘ፤ በልቡ አረፈ፣ እውነተኛና ውስጣዊ ሰላምን አገኘ፡፡ በዚህ በፍጹም ተደሰተ «ጌታ ሆይ ስለ ፈጠርኸን ልባችን አንተን ካላገኘ ዕረፍት እያገኝም፤ ፈጽሞ እርካተ አግኝቶ አያርፍም´ አለ፡፡ እውነቱን ነው ከፈጣሪያችን ርቀን ስቃይና መከራ እንጂ ደስታ፣ ሰላምን ዕረፍት ማግኘት የማይታሰብ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ትተን ከሕሊና መራራ ወቀሳ በስተቀር ሌላ የምናገኘው የለንም፡፡ ኢየሱስ «በእኔ ሰላምን ታገኛላችሁ በዓለም ግን ሐዘን መከራና ስቃይ ታገኛለላችሁ´ (1) ይለናል፡፡

ልባችን አንተን ካላገኘ ዕረፍት አይኖረውም ዓለምን ከነሀብቱና ደስታው ጨብጠን ብንይዝና እንደምንፈለገውና አንደምንመኘው ደስ ከሚለን የልባችን ምኞት ከሚፈጸምልን ከምንረካ ይልቅ የምንጠላውን ሁከት የመንፈስ መረበሽና ሐዘን ይጥብናል፡፡ በዓለም ነገሮች ብፅዕና ያለ መስሎን ተንሰፍስፈን በጉጉት ፈልገን ካገኘናቸው በኋላ እንደ ጉም የማይጨበጡ የማያጠግቡና የማያረኩ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ የዓለም ሀብት ክብርና ሹመት እንደ እሾክ ይወጋናል፤ ክፉኛ ያሰቃየናል፡፡ ዓለም ጥሩ ጣፋጭ ይመስለናል፤ እስከምን ጨብጠው ድረስ በሩቅ ምኞታችን የሚያሟላልን መስሎ ይታየናል፤ ጨብጠን ከሞከርነው ግን እናስበው ከነበረው ጋር ተቃራኒ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

ዓለምን ትተን እግዚአብሔርን ከያዝን በእውነት በመንፈስ የምንረካና የዓለምን ነገሮች ንቀን አምላክን ካገኘን ብቻ ያን ጊዜ የልብ ሙሉ ደስታ ይሰማናል፡፡ ምኞታችንና ሕይወታችን የሆነውን እግዚአብሔርን ስናገኘው ደስ ይለናል፣ ከእርሱ ሌላ አለ ብለን አናስብም፣ ተስፋችን እርሱ በመሆኑ የኑሮአችን ዋና ዓላማ ሆኖ ይሰማናል፡፡ «ጌታ ሆይ ለራስህ ብለህ ፈጠርኸን ልባችንም አንተን ካላገኘ ፈጽሞ ዕረፍት አያገኝም´ እንግዲህ ይህን አስታውሰን በሕይወታችን ዘመን በማሰታወስ ሁል ጊዜ ፈጣሪያችንን በጥሞና እናሰላስል፡፡ እርሱን ብቻ ለማግኘት ጥረት እናድረግ፣ ባለን ኃይልና አቅምና ምን ጊዜም ሳናቋርጥ እንታገል፡፡ ከእርሱ ጋር ለመኖር እንፈልግ፣ ሁሉን ፍጥረቶች ንቀን ፈጣሪያችንና አባታችን የሆነውን እውነተኛውን አምላክ እንውደድ፡፡

ሰው እግዚአብሔርን የሚናፍቀው ለምንድነው?

እግዚአብሔር ራሱ ሰውን በራሱ አምሳል ስለፈጠረ፣ እርሱን የሚያይበትን ናፍቆት ብዙ ጊዜ ችላ ቢልም እንኳ እግዚአብሔር ሰውን ወደራሱ መሳቡን ከቶ አያቋርጥም፤ ምክንያቱም ያለማቋረጥ የሚፈገውን የእውነትና የደስታ ሙላት የሚያገኘውና በእርሱም የሚኖርበት በእግዚአብሔር ብቻ ነውና፡፡ ስለዚህ፣ በተፈጥሮም ሆነ በመንፈሳዊ ጥሪ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ሊኖረው የሚችል መንፈሳዊ ፍጡር ነው፡፡ ይህም ከእዚአብሔር ጋር ያለው ቅርብና ወሳኝ ትስስር ለሰው ልጅ መሠረታዊ ክብሩን ያጎናጽፈዋ።

በሰው አእምሮ ብቻ እግዚአብሔርን እንዴት ማወቅ ይቻላ?

ከፍጥረት ማለትም ከዓለምና ከሰው ልጅ መፈጠር ተነሥቶ ሰው በአእምሮው ብቻ እግዚአብሔር የዓለም መጀመሪያና መጨረሻ፣ ቸርነቱ የበዛ፣ ወሰን የሌለው እውነትና ውበት መሆኑን በእርጠኛነት ሊያውቅ ይችላ።

የአእምሮ ብርሃን ብቻ የእግዚአብሔርን ምስጢር ለማወቅ ያስችላ?

ሰው በአእምሮው ብቻ እግዚአብሔርን ለማወቅ ብዙ ችግሮች ያጋጥሙታ። በመሠረቱ፣ ሰው በራሱ ወደ መለኮታዊ ምስጢር መግባት አይችም። ለዚህም ነው ከዕውቀቱ በላይ የሆኑትን ነገሮች ብቻ ሳይሆን በራሳቸው ከሰው አእምሮ በላይ ያልሆኑትን መንፈሳዊና ግብረገባዊ እውነታዎችንም ለማወቅ የእግዚአብሔር የመገለጥ ብርሃን የሚያስፈገው። ያን ጊዜ የሰው ዘር አሁን ባለበት ሁኔታ እንኳ በቀላሉ፣ በእርግጠኝነትና ያለ ምንም ስሕተት በሁሉም ዘንድ ሊታወቁ ይችላሉ።

 ስለ እግዚአብሔር መናገር የምንችለው እንዴት ነው?

በውስን ደረጃም ቢሆን የእግዚአብሔር ወሰን የሌለው ፍጹምና ነፀብራቅ የሆኑትን የሰውንና የሌሎች ፍጥረታትን ፍጽምና መነሻ አድርገን ብንወስድ ከሰዎች ሁሉ ጋር ስለእዚአብሔር መነጋገር እንችላለን፡፡ ይሁን እንጂ፣ በሐሳብ የትጠረና ያልተሟላ እስከሆነ ድረስ ንግግራችንን ያለማቋረጥ ማጥራትና ወሰን የሌለውን የእግዚአብሔር ምስጢር ሙሉ በሙሉ መለጽ እንደማንችል መገንዘብ ይኖርብና።

02 May 2019, 17:32