ፈልግ

በቡርኪና ፋሶ በቤተክርስትያን ላይ በተቃጣ ጥቅት 4 ሰዎች መገደላቸቸው ተገለጸ በቡርኪና ፋሶ በቤተክርስትያን ላይ በተቃጣ ጥቅት 4 ሰዎች መገደላቸቸው ተገለጸ 

በቡርኪና ፋሶ በቤተክርስትያን ላይ በተቃጣ ጥቅት 4 ሰዎች መገደላቸቸው ተገለጸ

በቡርኪናፋሶ በአንድ የካቶሊክ ቤተክርስትያን ላይ በተቃጣው የአሸባሪዎች ጥቃት አራት ምዕመናን መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን በዚህ በግንቦት 18/2011 ዓ.ም እለት ሰንበት ላይ የመስዋዕተ ቅዳሴ በመታደም ላይ በነበሩ ምዕመናን ላይ በስምንት ታጣቂዎች በተከፈተው ተኩስ ሕይወታቸውን ካጡት አራት ሰዎች ባሻገር ሁለቱ በጥቃቱ በደረሰባቸው ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ የሕክምና አገልግሎት እየተሰጣቸው መሆኑም ተገልጹዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ይህ የአሸባሪዎች ጥቃት በእዚህ በመገባደድ ላይ ባለው የጎርጎሮሳዊያኑ የግንቦት ውር ውስጥ በቡርኪናፋሶ የተቃጣ አራተኛ ጥቃት እንደ ሆነ ተያይዞ ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በዚህ ተግባራቸው አሸባሪዎቹ በአገሪቷ በቡርኪናፋሶ የሚገኙ የተለያየ እመንት ተከታይ የሆኑ ሰዎች ለአመታት ተቻችለው እና ተከባብሮ የመኖር ባሕላቸውን ለመሻር ታስቦ በአሸባሪዎች የተቃጣ ጥቃት እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን ይህንን በተመለከተ ይህ ጥቃት የደረሰበት አከባቢ አገረ ስብከት ጳጳስ እንደ ገለጹት ምንም እንኳን አሸባሪዎቹ በአገሪቷ ሕዝቦች መካከል ያለውን አብሮነት እና የመከባበር መንፈስ ለመሻር አስበው የፈጸሙት ጥቃት ቢሆንም ቅሉ ይህ ዓላማቸው ግን ግቡን እንደ ማይመታ ጨምረው ገልጸዋል።

ይህ በግንቦት 18/2011 ዓ.ም በአሸባሪዎች የተቃጣው ጥቃት ከዚህ ቀደም እንደ ነበሩት ጥቃቶች ምዕመኑ የእግዚኣብሔር ቃል ለመስማት እና መስዋዕተ ቅዳሴን ለመካፈል በሚሰበሰብበት እለተ ሰንበት መፈጹም ደግሞ ጥቃቱ ሆን ብሎ የታቀደ እና በተቻለ መጠን ብዙ ሰዎችን ለማጥፋት ወይም ለመግደል ታስቦ የተፈጸመ ጥቃት እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን የዚህ ዓይነቱ በክርስትያኖች ላይ በእመነታቸው ምክንያት ብቻ የሚፈጸምባቸው ጥቃት በፍጹም ተቀባይነት እንደ ሌለው ተገልጹዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በግንቦት 04/2011 ዓ.ም እለተ ሰንበት ላይ በቡርኪና ፋሶ መስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስርዓት በማከናወን ላይ በነበረው በአንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ላይ በአሸባሪዎች በተቃጣው ጥቃት በምዕመናን እና በእለቱ መስዋዕተ ቅዳሴ በማስረግ ላይ ይገኙ በነበረው ካህን ላይ በደረሰው ከፍተኛ አደጋ ማዘናቸውን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንቸስኮስ ከ40 ሚልዮን በላይ ተከታዮች ባሉት እና @pontifex በመባል በሚታወቀው የቲውተር ገጻቸው በላኩት መልእክት ይፍ ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በቡርካና ፋሶ የሚገኙ አካራሪ የእስልምና ተከታዮች ይህንን በምንም ዓይነት መስፈር ተቀባይነት የሌለውን ጥቃት በመፈጸም ምዕመኑ እግዚኣብሔርን ለማመስገን በሚሰበሰብበት እለተ ሰንበ ሽብር ለመንዛት እና የንጹሐንን ደም ለማፍሰስ እለቱን መጠቀማቸው የሚያሳዝን ተግባር መሆኑን በመልእክታቸው ገልጸዋል። በእለቱ በተፈጸመው ጥቃት መስዋዕተ ቅዳሴ በማሳረግ ላይ የነበሩ አንድ ካህንን ጨምሮ ሌሎች አምስት ምዕመናን መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን አሸባሪዎቹ ይህንን ጥቃት ካደረሱ በኋላ ቤተ ክርስትያኑን በእሳት ማጋየታቸውም ከስፍራው ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

በቡርኪና ፋሶ በአንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ላይ በአሸባሪዎች የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቲውተር ገጻቸው ላይ ያስተላለፉትን የሐዘን መግለጫ በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት የቅዱስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ጽህፈት ቤት ምክትል ዳሬክተር የሆኑት አቶ አሌክሳንድሮ ጂዞቲ እንደ ገለጹት “በዚህ በአሸባሪዎች የተቃጣውን ጥቃት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራችስኮስ በሰሙበት ወቅት እጅግ ማዘናቸውን፣ የጥቃቱ ሰለባ ለሆኑት ሰዎች እና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም በአገሪቷ ለሚገኙ የክርስቲያን ማኅበርሰቦች ጸሎት  እንደ ሚያደርጉ ቅዱስነታቸው መግለጻቸውን” አውስተዋል።

የምዕራብ አፍሪካ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባሄ ተወካዮች በአሁኑ ወቅት በቀጠናው በአሸባሪዎች በቤተክርስትያን ላይ እየተቃጣ የሚገኘውን የሽብር ጥቃት ለመከላከል እና ሰላም እና አንድነት በክልሉ ይሰፍን ዘንድ ተቀናጅተው እንደ ሚሰሩ ገለጹ።

የምዕራብ አፍሪካ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪዎች በክልሉ በሚገኙ የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት እና ማህበረሰቦች ላይ የሚፈጸመውን ግፍ ለማስቆም እና ሰላማዊ ማህበረሰብ ለመገንባት ይቻል ዘንድ ሁሉም የማኅበርሰቡ አባላት በሂደቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው ተገልጹዋል። በቀጠናው ከሚገኙ አገራት ውስጥ በተለይም በቡርኪና ፋሶ እና በኒጀር በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ላይ በቅርቡ በአሸባሪዎች ጥቃት መፈጸሙ የሚታወስ ሲሆን በዚህ በአሸባሪዎች በተቃጣው ጥቃት የተነሳ በርካታ ሰዎች መገደላቸው፣ አብያተ ክርስቲያናት እና እንዲሁም የክርስትና እምነት መገለጫ የሆኑ ምልክቶች ያሉባቸው ስፍራዎች ላይ ሳይቀር ጥቃት መፈጸሙ ይታወሳል።

ባለፈው ሳምንት ብቻ አንድ ካህንን ጨምሮ ቢያንስ 10 ሰዎች በቡርኪና ፋሶ ባልታወቁ ታጣቂ ሰዎች መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን ቡርኪና ፋሶን ከኒጀር ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው በኒያሜይ አገረ ስብከት ውስጥ በሚገኘው አንድ ቁምስና ላይ በተከፈተው ጥቃት አንድ ካህን የመቁሰል አደጋ እንደ ደረሰባቸው መዘገባችን ይታወሳል።

የምዕራብ አፍሪካ የካቶሊክ ቤተክርስትያን ጳጳሳት ጉባሄ ሕብረት አባላት የቀጠናቸውን ሁኔታ በተመለከተ “በአንድነት እና በጋር የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ማሸነፍ እና ሕዝቡ ድል አድራጊ እንዲሆን ማድረግ ይቻላል” በሚል መሪ ቃል መወያየታቸው የገለጸ ሲሆን ይህ ስብሰባ በቡሪክና ፋሶ ዋና ከተማ ከባለፈው ግንቦት 04-10/2011 ዓ.ም ተካሂዶ እንደ ነበረም ከፍስራው ለቫቲካን ከደረሰው ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ጌታ እዚህ ከእኛ ጋር ስላለ እናሸንፋለን” የሚል መግለጫ ካወጡ በኋላ ጉባሄው መጠናቀቁ ተገልጹዋል።

26 May 2019, 18:13