ፈልግ

የኒሃአመይ አገረ ስብከት ካቴድራል ኒጀር የኒሃአመይ አገረ ስብከት ካቴድራል ኒጀር  

በኒጀር በሚገኝ በአንድ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት መድረሱ ተገለጸ።

የምዕራብ አፍሪካ ሀገር በሆነችው በኒጀር በአንድ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ላይ በአሸባሪዎች ጥቃት መድረሱ ከስፍራው ለቫቲካን ዜና ከደረሰው መረጀ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህ ጥቃት የተፈጸመው በአገሪቷ በሚገኘው ኒያሜይ በመባል በሚታወቀው አገረ ስብከት ውስጥ እንደ ሆነም ተያይዞ ከወጣው መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል። ይህ ጥቃት በአገሪቷ ውስጥ በሚኖሩ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ላይ በተከታታይ እየደረሰ የሚገኘውን የተለያየ ዓይነት ጥቃት ጫፍ ላይ ምድረሱን እንደ ሚያሳይ ሲሆን በዚህ ጥቃት የቤተክርስቲያኒቷ ቆመስ ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱም ተገልጹዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በኒጀር የቅዱስ ወንጌል አገልግሎት በማከናወን ላይ የሚገኙ ሚሲዮናዊያን ጥቃቱን አስመልክተው እንደ ገለጹት ይህንን ጥቃት የፈጸሙት ማንነታቸው የማይታወቅ ሰዎች እንደ ነበሩ የገለጹ ሲሆን ይህ ጥቃት የተፈጸመው ደግሞ ከዋና ከተማይቱ 200 ኪሎሜትሮች ያህል ርቆ በሚገኘው ዶልበል በተባለው ቁምስና ላይ እንደ ነበረ የገለጹ ሲሆን በጥቃቱ የቤተክርስቲያኒቷ ቆመስ ላይ የመቁሰል አደጋ እንደ ደረሰባቸው ገልጸዋል።

ሚስዮናዊያኑ ይህንን ጥቃት በተመለከተ ጨምረው እንደ ገለጹት ይህ ጥቃት በቁምስናው ላይ በተለይም ደግሞ በቁምስናው ውስጥ እያገለገሉ በሚገኙ ካህናት ላይ እንደ ሚደርስ ቀደም ሲል መረጃው ስለነበራቸው እና በዚህም መሰረት ቀድመ ጥንቃቄ በማድረጋቸው የተነሳ የጥቃቱን ግዝፈት መቀነስ እንደ ተቻለ ገልጸው ይህ ጥቃት የሚያሳየው ደግሞ አገሪቷን ከቡርኪናፋሶ ጋር የሚያገናኘው ድንበር አከባቢ ያለው የጸጥታ ሁኔታ አሁንም ቢሆን አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደ ሚገኝ ያሳያል ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በግንቦት 04/2011 ዓ.ም እለተ ሰንበት ላይ በቡርኪና ፋሶ መስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስርዓት በማከናወን ላይ በነበረው በአንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ላይ በአሸባሪዎች በተቃጣው ጥቃት በምዕመናን እና በእለቱ መስዋዕተ ቅዳሴ በማስረግ ላይ ይገኙ በነበረው ካህን ላይ በደረሰው ከፍተኛ አደጋ ማዘናቸውን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንቸስኮስ ከ40 ሚልዮን በላይ ተከታዮች ባሉት እና @pontifex በመባል በሚታወቀው የቲውተር ገጻቸው በላኩት መልእክት ይፍ ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በቡርካና ፋሶ የሚገኙ አካራሪ የእስልምና ተከታዮች ይህንን በምንም ዓይነት መስፈር ተቀባይነት የሌለውን ጥቃት በመፈጸም ምዕመኑ እግዚኣብሔርን ለማመስገን በሚሰበሰብበት እለተ ሰንበ ሽብር ለመንዛት እና የንጹሐንን ደም ለማፍሰስ እለቱን መጠቀማቸው የሚያሳዝን ተግባር መሆኑን በመልእክታቸው ገልጸዋል። በእለቱ በተፈጸመው ጥቃት መስዋዕተ ቅዳሴ በማሳረግ ላይ የነበሩ አንድ ካህንን ጨምሮ ሌሎች አምስት ምዕመናን መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን አሸባሪዎቹ ይህንን ጥቃት ካደረሱ በኋላ ቤተ ክርስትያኑን በእሳት ማጋየታቸውም ከስፍራው ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

በቡርኪና ፋሶ በአንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ላይ በአሸባሪዎች የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቲውተር ገጻቸው ላይ ያስተላለፉትን የሐዘን መግለጫ በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት የቅዱስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ጽህፈት ቤት ምክትል ዳሬክተር የሆኑት አቶ አሌክሳንድሮ ጂዞቲ እንደ ገለጹት “በዚህ በአሸባሪዎች የተቃጣውን ጥቃት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራችስኮስ በሰሙበት ወቅት እጅግ ማዘናቸውን፣ የጥቃቱ ሰለባ ለሆኑት ሰዎች እና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም በአገሪቷ ለሚገኙ የክርስቲያን ማኅበርሰቦች ጸሎት  እንደ ሚያደርጉ ቅዱስነታቸው መግለጻቸውን” አውስተዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
14 May 2019, 16:09