ፈልግ

የሕማማት ሳምንት የሕማማት ሳምንት  

የኢየሱስ ሞት የእግዚአብሔር ዕቅድ አካል የሆነው ለምንድነው?

እግዚአብሔር በኃጢአት ምክንያት ሞት ተፈርዶባቸው ነበሩትን ሰዎች ሁሉ ከራሱ ጋር ለማስታረቅ ስለፈለገ ራሱን ስለኃጢአተኞች አሳልፎ የሚሰጥ ልጁን ለመላክ በፍቅሩ ወሰነ፡፡  በተለይ የመከረኛው አገልጋይ መሥዋዕት እንደሆነ ተደርጎ በብሉይ ኪዳን የተነገረው የኢየሱስ ሞት የተፈጸመው “በቅዱሳት መጻሕፍት” መሠረት ነው ።

ክርስቶስ ራሱን ለአብ የሠዋው በምን ዐይነት መንገድ ነው?

የክርስቶስ ሙሉ ሕይወት የደኅንነት ዕቅዱን ለመፈጸም ለአብ በፈቃደኝነት የተሰጠ

መሥዋዕት         ነው፡፡   እርሱ “ሕይወቱን ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ”   (ማር.   10፡45)   ሰጠ፡፡ በዚህም መንገድ የሰውን ዘር በሙሉ ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀ፡፡ ሰብአዊነቱ የሁሉንም ሰዎች ደኅንነት የሚመኘው የዚያ መለኮታዊ ፍቅሩ ነፃና ፍጹም መሣሪያ ለመሆኑ የእርሱ ሕማምና ሞት በግልጽ አሳየ፡፡

የኢየሱስ መሥዋዕት በመጨረሻው እራት የተገለጸው እንዴት ነው?

ኢየሱስ  በሕማማቱ  ዋዜማ  ከሐዋርያቱ  ጋር  ባደረገው የመጨረሻ  እራት  ላይ  ራሱን  በፈቃደኝነት  መሥዋዕት  አድርጎ ማቅረቡን መታሰቢያ ሲያደርግ “ይህ ስለ እናንተ የሚሰጥ ሥጋዬ  ነው”  (ሉቃ.  22፡19)፣  «ይህ  ....  የሚፈስ  ደሜ  ነው» (ማቴ.  26፡28)  አለ፡፡  በዚህም  ዐይነት  ቅዱስ  ቁርባንን የመሥዋዕቱ “መታሰቢያ”      (1ኛ     ቆሮ.     11፡25)         አደረገ፣ ደቀ-መዛሙርቱንም  የአዲሱ  ኪዳን  ካህናት  አደረጋቸው።

በጌተሰማኒ የአትክልት ስፍራ የደረሰው ሥቃይ ምን ሆነ?

ሞት “የሕይወት ጌታ”   (የሐዋ.   3፡15) በሆነው በኢየሱስ ቅዱስ ሰውነት ላይ ፍርሃትን ቢያሳድርበትም የእግዚአብሔር ልጅ ሰብአዊ ፈቃድ ስለደኅንነታችን ለአብ ፈቃድ ታማኝ ሆነ ። “እስከ ሞት ድረስ በመታዘዝ” (ፊልጳ. 2፡8)    ኢየሱስ ኃጢአታችንን በሥጋው የመሸከም ኃላፊነት ወሰደ፡፡

የክርስቶስ የመስቀል ላይ መሥዋዕት ፍሬዎች ምንድናቸው?

ኢየሱስ ሕይወቱን የማስተሰሪያ መሥዋዕት አድርጎ በፈቃደኝነት አቀረበ፤ ማለትም እስከ ሞት ድረስ በፍቅር በመታዘዙ የኃጢአታችንን ካሣ ከፈለ፡፡   ይህ   “እስከ መጨረሻ”   (ዮሐ. 13፡1) የጸናው የእግዚአብሔር ልጅ ፍቅር ሰውን ሁሉ ከአብ ጋር   አስታረቀ፡፡   ስለዚህ፣ የክርስቶስ የፋሲካ መሥዋዕት ዐይነተኛ ፍጹም እና እውነተኛ በሆነ መንገድ የሰውን ዘር ያድናል፤ ከእግዚአብሔር ጋር የመተባበርንም ዕድል ይሰጣቸዋል፡፡

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን መስቀላቸውን እንዲሸከሙ የጠራቸው ለምንድነው?

ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን መስቀላቸውን ተሸክመው እንዲከተሉት የጠራቸው ከአዳኝ መሥዋዕቱ የመጀመሪያ ጠቃሚዎች ከሚሆኑት ጋር ህብረት ለመፍጠር ስለፈለገ ነው።

የኢየሱስ ሥጋ በመቃብር ውስጥ ሳለ በምን ሁኔታ ላይ ነበር?

ክርስቶስ  እውነተኛ  ሞት  ሞተ፣  በእርግጥም  ተቀበረ፡፡  ነገር ግን  የእግዚአብሔር  ኃይል  ሥጋውን  ከመበስበስ  አዳነው። “ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሲኦል ወረደ፣ በሶስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ።”

 

ኢየሱስ የወረደበት « ሲኦል»  ምንድነው?

ይህ  “ሲኦል”   የተኮነኑት  ከሚገቡበት  ሲኦል  የተለየ  ነበር፡፡ ከክርስቶስ በፊት የሞቱ ጻድቃንና ክፉዎች ሁሉ የሚገኙበት ሁኔታ  ነበር፡፡  ኢየሱስ  ከመለኮታዊ  አካሉ  ጋር  በተዋሐደችው ነፍሱ  በመጨረሻ  እግዚአብሔርን  ፊት  ለፊት  ወደሚያዩበት ለመግባት   የአዳኛቸውን   መምጣት   ወደሚጠባበቁና   በሲኦል ወደሚገኙ   ጻድቃን   ዘንድ   ወረደ፡፡   ኢየሱስ   በሞቱ   ሞትንና “በሞት  ላይ  ሥልጣን  ያለውን”  (ዕብ.  2፡14)  ዲያብሎስን  ድል አድርጎ መድኃኒታቸውን የሚጠባበቁ ጻድቃንን ነፃ አወጣቸው፣  የመንግሥተ  ሰማይንም  በሮች  ከፈተላቸው፡፡

የክርስቶስ ትንሣኤ በእምነታችን ውስጥ ያለው ስፍራ ምንድነው?

የክርስቶስ ትንሣኤበክርስቶስ ያለንእምነት ትልቁ እውነታ ሲሆን፣ ከመስቀሉ ጋር ሆኖ የፋሲካ ምስጢር ዋና አካል ነው፡፡

25 April 2019, 12:42