ፈልግ

የፓክስታን ክርስቲያኖች፣ የፓክስታን ክርስቲያኖች፣  

በፓክስታን ውስጥ ክርስቲያኖች የአገራቸውን ሰማዕታት በጸሎታቸው አስታወሱ።

የሞት አደጋ የደረሰባቸው ምእመናን በቤተክርስቲያናቸው ውስጥ በጸሎት ስነ ስርዓት ላይ እያሉ መሆኑን የገለጹት ሊቀ ጳጳሳት ብጹዕ አቡነ ሰባስቲያን ሾው ድርጊቱ አሳዛኝ እንደነበር ተናግረዋል። በአደጋው ሕይወታቸውን ካጡት ሰዎች ወላጆች እና ቤተሰቦች ጋር ሕመማቸውን እና ሐዘናቸውን በመካፈል ሰማዕታቱንም በጸሎት ለማስታወስ መታደላቸውን አስረድተዋል። በወቅቱ ከተሰነዘረው ጥቃት ለተረፉት ለ1,500 ምእመናን ያህል እግዚአብሔርን ማመስገናቸውን ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በፓክስታን ውስጥ የላሆረ ካቶሊካዊ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሰባስቲያን ሾው፣ ከሃገረ ስብከቱ ምእመናን ጋር ሆነው በቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ባሳረጉት የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት፣ በዩሐናባድ በሚገኙ ሁለት ቤተ ክርስቲያኖች፣ በ2007 ዓ. ም. የተገደሉ ምእመናንን አስታውሰዋል። በመስዋዕተ ቅዳሴው ጸሎት፣ በኒዩዚላድ በሚገኙ ሁለት መስጊዶች ላይ በደረሰው ጥቃት የሞቱትንም አስታውሰዋል። ፊደስ ከተሰኘ የቤተክርስቲያን የዜና አገልግሎት ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት በፓክስታን የላሆረ ካቶሊካዊ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳሳት ብጹዕ አቡነ ሰባስቲያን ሾው በ2007 ዓ. ም. በምእመናኖቻቸው ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ዘወትር እንደሚያስወሱት ገልጸው በገዛ አገራቸው በሰላም ተወጥቶ በሰላም የመግባት ዋስትና እንደሌለ ገልጸዋል። ሊቀ ጳጳሳት ብጹዕ አቡነ ሰባስቲያን ሾው በመስዋዕተ ቅዳሴው ስነ ስርዓት ላይ የአደጋው ሰለባ የሆኑ ምዕመናን ወላጆችን እና በአደጋው የቆሰሉትንም ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

ለላሆሬ ሰማዕታት የጸሎት ስነ ስርዓት ተከናውኗል፣

የሞት አደጋ የደረሰባቸው ምእመናን በቤተክርስቲያናቸው ውስጥ በጸሎት ስነ ስርዓት ላይ እያሉ መሆኑን የገለጹት ሊቀ ጳጳሳት ብጹዕ አቡነ ሰባስቲያን ሾው ድርጊቱ አሳዛኝ እንደነበር ተናግረዋል። በአደጋው ሕይወታቸውን ካጡት ሰዎች ወላጆች እና ቤተሰቦች ጋር ሕመማቸውን እና ሐዘናቸውን በመካፈል ሰማዕታቱንም በጸሎት ለማስታወስ መታደላቸውን አስረድተዋል። በወቅቱ ከተሰነዘረው ጥቃት ለተረፉት ለ1,500 ምእመናን ያህል እግዚአብሔርን ማመስገናቸውን ገልጸዋል። የላሆረ ሊቀ ጳጳሳት ብጹዕ አቡነ ሰባስቲያን ሾው የአካባቢያቸው የጥበቃ ሃይል ላሳየው ድፍረት የተሞላበት የነፍስ ማዳን አገልግሎት ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል። በአደጋው የሞቱትን ምዕመናን ያስታወሱት ሊቀ ጳጳሳት ብጹዕ አቡነ ሰባስቲያን ሾው፣ የተቀደሱት የሀገረ ስብከታቸው ሰማዕታት ሕይወታቸውን የሰውት ለእምነታቸው ምስክርነት እና በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ለነበሩ ሌሎች ምእመናን ደህንነት ሲሉ እንደነበር ገልጸዋል።

ለኒዩዚላንድ የአደጋ ሰለባዎች ተጸልዮላቸዋል፣

ሊቀ ጳጳሳት ብጹዕ አቡነ ሰባስቲያን ሾው የፓክስታንን የጸጥታ ሃይል ካመሰገኑ በኋላ ሠራዊቱ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች የዜጎችን ደህንነት ለማስጠብቅ ተሰማርቶ እንደሚገኝ ገልጸው ምዕመናኑ ለእነዚህ የጸጥታ ሃይሎች እና ለቤተሰቦቻቸው እንዲጸልዩላቸው አደራ ብለዋል። ብጹዕ አቡነ ሰባስቲያን ሾው ከዚህም ጋር አያይዘው በኒዩዚላንድ በሚገኙ መስጊዶች ለጸሎት በተሰበሰቡት ሰዎች ላይ በተጣለው አደጋ ሕይወታቸውን ያጡትን እና በጥልቅ ሐዘን ላይ የሚገኙ ቤተሰቦቻቸውን በጸሎታቸው እንዲያስታውሷቸው ምዕመናንን አደራ ብለው በወላጆቻቸው ላይ የደረሰውን ዓይነት ጥልቅ ሕመም እና ሐዘን የፓክስታን ክርስቲያኖችም  ቀምሰነዋልና በሚገባ እናውቀዋለን ብለዋል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!

       

20 March 2019, 16:30