ፈልግ

 የኢትዮጲያ አየር መንገድ አውሮፕላን የተከሰከሰበት ስፍራ የኢትዮጲያ አየር መንገድ አውሮፕላን የተከሰከሰበት ስፍራ  

ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የተሰጠ የሐዘን መግለጫ

የአገራችን ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 በዛሬው እለት ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ኬንያ በሚጓዝበት ወቅት በደረሰበት አደጋ በውስጡ የነበሩት ተጓዦችና የበረራ ሰራተኞች ሕይወት በማለፉ እጅግ አዝነናል፡፡ በዚህ አስደንጋጭ አደጋ ቤተሰቦቻቸዉንና ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ ሁሉ ቤተክርቲያናችን ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔር መፅናናትን እንዲሰጥልን ትማፀናለች፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞችና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብም መፅናናትን እንመኛለን፡፡

በተለይም መላው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች የደረሰባቸውን ከባድ ድንጋጤና ሐዘን ተቋቁመው የተለመደውን አኩሪ አገልግሎት ለደንበኞቻቸው ማበርከት መቀጠል እንዲችሉ አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ራሱ ብርታት እንዲሰጣቸው እንጸልያለን፡፡

በአደጋው በሞት የተለዩንን የኢቲ 302 ተጓዥ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እግዚአብሔር በእመቤታችን ቅድስት ልደታ ማሪያም፣ በመላእክትና በቅዱሳን ሁሉ መካከል በሰላም እንዲያሳርፍልን እንማጠናለን፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!አባ ሐጎስ ሐይሽ
ጠቅላይ ጸሐፊ

11 March 2019, 08:42