ፈልግ

በሊጧኒያ የሚገኝ የቅድስት ድንግል ማርያም መንፈሳዊ ምስል፣ በሊጧኒያ የሚገኝ የቅድስት ድንግል ማርያም መንፈሳዊ ምስል፣ 

ክርስቲያኖችን እና ሙስሊሞችን የሚያገናኛቸው ለቅድስት ድንግል ማርያም ያላቸው ፍቅር ነው።

በእስልምና እምነት ተከታዮች እና በእመቤታች ቅድስት ድንግል ማርያም መካከል ያለው ግንኙት ምንድር ነው ለሚለው ጥያቄ ማብራሪያቸውን ከቅዱስ ቁራን መጽሐፍ በመጀመር ያስረዱት አባ እስጢፋኖስ በቅዱስ ቁርዓን መጽሐፍ ውስጥ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሚናገር አንድ ሙሉ ምዕራፍ መኖሩን አስረድተዋል። የእስልምና እምነት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን የጸነሰችው በድንግልና እንደሆነ፣ ወደ ቤተ መቅደስ እንደሄደች፣ በቅዱሳት መልአክትም እንደታገዘች፣ ለእግዚአብሔር የገለጸችለትን የታማኝነት ሕይወቷን የሚገልጽ የቅዱስ ቁርዓን ክፍል መኖሩን አስረድተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ዓለም አቀፍ ማርያማዊ ጥናት ጳጳሳዊ አካዳሚ ፕሬዚደንት የሆኑት ክቡር አባ እስጢፋኖስ ቼኪኒ ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በሚሰጡት አክብሮት ላይ የሚወያይ ጉባኤ በግንቦት ወር 2011 ዓ. ም. እንደሚካሄድ ገልጸዋል። አባ እስጢፋኖስ የጉባኤውን ዓላማ በማስመልከት ገለጻ በሰጡበት ጊዜ እንድተናገሩት ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ልባዊ ፍቅር እንዳላቸው አስረድተዋል።   

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለሁለቱ የእምነት ተቋማት መልካም የውይይት መንገድን እንደምትከፍትላቸው እና መልካም የመግባቢያ መንገድም እንደምትሆናቸው ገልጸዋል። ታሪክ እንደሚያስረዳው ቅድስት ድንግል ማርያም ከእጮኛዋ ቅዱስ ዮሴፍ ጋር ሆና ከኢየሩሳሌም ወደ ቤተልሔም ስትጓዝ ሳለ በቅድስት ድንግል ማርያም ጥያቄ መሠረት እረፍትን ለመውሰድ ብለው የተቀመጡበት ስፍራ መኖሩን ገልጸው፣ ማርያምም በዚህ ጊዜ በቦታው ከነበረው የቴምር ዛፍ ፍሬን መብላት ፈልጋ ለቅዱስ ዮሴፍ ጥያቄን ብታቀርብለም ከቴምር ዛፍ እጅግ መርዘም የተነሳ ፍሬውን ማግኘት እንዳልቻሉ፣ ነገር ግን አዲስ ለሕጻኑ ኢየሱስ ሲነግሩት ኢየሱስ ዛፉን ወደ መሬት እንዲያጎበድድ ባዘዘው ጊዜ ከቴምር ፍሬ መብላት እንደቻሉ የሚናገር ታሪክ መኖሩን አባ እስጢፋኖስ ተናግረዋል። ስፍራውም የማርያም የዕረፍት ስፍራ ተብሎ እንደሚጠራ እና ዛሬ በስፍራውም በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም የሚጠራ ቤተክርስቲያን ታንጾ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ተመሳሳይ ታሪክ በቅዱስ ቁርዓን መጽሐፍ ውስጥ ተጠቅሶ ይገኛል፣

ኢየሱስ ክርስቶስ ከዘንባባ ዛፍ ሥር እንደተወለደ፣ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መልአክ እንደታያት እና የዘንባባ ዛፍ በመነቅነቅ ከፍሬውም እንድትበላ እንደነገራት የሚያስታውስ የቅዱስ ቁርዓን ታሪክ መኖሩን የገለጹት አባ እስጢፋኖስ በእስልምና እምነት የራማዳን ጾም ሲያዝ የቴምር ፍሬ እንደሚዘጋጅ እና እንደሚበላ ገልጸው የቴምር ዛፍ ምስልም በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ወለል ላይ ተስሎ እንደሚገኝ አስረድተዋል። 

ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ባላቸው ፍቅር ይገናኛሉ፣

ይህን ታሪክ መሠረት በማድረግ በሁለቱ የእምነት ተቋማት መካከል ያለውን የቀረበ ግንኙነት የሚያጠና እና “የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቴምር ፍሬዎች” በሚል ርዕስ የሚወያይ የአንድ ቀን ጉባኤ በሮም ከተማ በሚገኝ አንቶኒያኑም ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በግንቦት 5 ቀን 2011 ዓ. ም. እንደሚካሄድ፣ የዓለም አቀፍ ማርያማዊ ጥናት ጳጳሳዊ አካዳሚ ፕሬዚደንት የሆኑት ክቡር አባ እስጢፋኖስ ቼኪኒ አስታውቀዋል። አባ እስጢፋኖስ በማከልም በክርስቲያኖች እና በሙስሊሞች መካከል ያለው ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር የሚያደርግ የጸሎት ሃይል እንደሆነ ገልጸው፣ “ሰብዓዊ ወንድማማችነት” በሚል መሪ ቃል ከጥር 26 – 28 ቀን 2011 ዓ. ም. ድረስ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ዋና ከተማ በአቡ ዳቢ የተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት መሪዎች በጋራ ባካሄዱትን ስብሰባ ላይ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መካፈላቸው አስታውሰው ቅዱስነታቸው ከአዛር ታላቁ ኢማም ከሆኑት ለአል ጣይብ ጋር “ሰብዓዊ ወንድማማችነት” ለዓለም ሰላም እና አብሮ ለመኖር በሚል ርዕስ የስምምነት ሰነድ መፈራረማቸውን አስታውሰው በዚህ የስምምነት ወቅት የገለጹት መሠረታዊ ጉዳይ ቢኖር ሁላችንም ወንድማማቾች እንድንሆን የሚያድረገን አቅማችን ወይም አንዳችን ለሌላው የሚያድረገው ቸርነት ተግባር ሳይሆን የእግዚአብሔር ጸጋ ነው ማለታቸውን አስታውሰው፣ ምዕራባዊያንን እና ምስራቃዊያንን፣ ክርስቲያኖችንን እና ሙስሊሞችን አንድ ሊያደርግ የሚችል የእግዚአብሔር ጸጋ መሆኑን አስረድተዋል። ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዘንድ የምናቀርበው የጋራ ጸሎት የበለጠ የሚያቀራርበን እንደሚችል አክለው ገልጸዋል።

ቅድስት ድንግል ማርያም በእስልምና እምነት ውስጥ መጀመሪያ የምትጠቀስ ናት፣

በእስልምና እምነት ተከታዮች እና በእመቤታች ቅድስት ድንግል ማርያም መካከል ያለው ግንኙት ምንድር ነው ለሚለው ጥያቄ ማብራሪያቸውን ከቅዱስ ቁራን መጽሐፍ በመጀመር ያስረዱት አባ እስጢፋኖስ በቅዱስ ቁርዓን መጽሐፍ ውስጥ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሚናገር አንድ ሙሉ ምዕራፍ መኖሩን አስረድተዋል። የእስልምና እምነት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን የጸነሰችው በድንግልና እንደሆነ፣ ወደ ቤተ መቅደስ እንደሄደች፣ በቅዱሳት መል አክትም እንደታገዘች፣ ለእግዚአብሔር የገለጸችለትን የታማኝነት ሕይወቷን የሚገልጽ የቅዱስ ቁርዓን ክፍል መኖሩን አስረድተዋል። እመቤታችን ቅድስት ማርያም በእስልምና እምነት ውስጥ የመጀመሪያ ስፍራ እንደሚሰጣት አስረድተው ከእርሷ ቀጥሎ ሌሎች ሴቶች ለምሳሌ ፋጢማ እና የፌሪዖን ሚስትም እንደሚገኙ አስረድተዋል።

ለማርያም አክብሮትን የሚሰጡት ሙስሊሞች ብቻ አይደሉም፣

ዓለም አቀፍ ማርያማዊ ጥናት ጳጳሳዊ አካዳሚ ፕሬዚደንት የሆኑት ክቡር አባ እስጢፋኖስ ቼኪኒ ለማርያም አክብሮትን የሚሰጡት ሙስሊሞች ብቻ ሳይሆኑ የሂንዱ እና የቡዳ እምነቶችም እንደሆኑ አስረድተው ለምሳሌ የቡዳ እምነት ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ግልጸት እውቅናን እንደሚሰጡ ተናግረዋል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
18 March 2019, 16:43