ፈልግ

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያም ማኅበራዊ አስተምህሮ ክፍል ሦስት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያም ማኅበራዊ አስተምህሮ ክፍል ሦስት 

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያም ማኅበራዊ አስተምህሮ ክፍል ሦስት

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ በሚል አርእስት የተዘጋጀውን የክፍል ሦስት አስተምሮ እንደ ሚከተለው እናቀርብላችኋለን። በባለፈው ሳምንት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በማኅበራዊ ጉዳዮች ውስጥ ትሳተፋለች ሲባል በአንድ አገር ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ ትገባለች ማለት እንዳልሆነ ሊሰመርበት የሚገባው ጉዳይ መሆኑን መግለጻችን የሚታወስ ሲሆን፣ ነገር ግን በተለያዩ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ጫናዎች ምክንያት በሰው ልጆች ላይ የሚደርሱትን በደሎች፣ ኢፍታዊ ተግባሮችን፣ በተለይም ደግሞ ዝቅተኛ እና ድሃ በሚባሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም ለዓለም ድምጹዋን ታሰማለች ማለት እንደ ሆነ መገለጻችን ይታወሳል።

በዛሬው እለት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ የተሰኘውን አርእስት ጽነሰ-ሐሳቡን በጥልቀት እንመለከታለን። የካቶሊክ ማኅበራዊ አስተምህሮ (Social doctrine of the church) የሚለውን አርእስት በመጠቀም Social (ማኅበራዊ) Doctrine (በግርድፉ ሲተረጎም አስተምህሮ) Church (ቤተ ክርስቲያን) የሚሉትን ቃላት ትርጉባቸውን በአጭሩ እንመለከታለን።

1.     Social ወይም ማኅበራዊ፡ የሚለውን ቃል ስንመለከት ማኅበራዊ የሚለው ቃል በራሱ  የአንድ ማኅበረሰብ አመሰራረት እና ማኅበራዊ መዋቅሩን ለየት ባለ ሁኔታ የሚያመለከት ጽንሰ-ሐሳብ ሲሆን  በአጠቃላይ የአንድ ማኅበረሰብ መልካም የሆኑ የጋራ እሴቶቻችን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥን ነው። ማኅበረሰብ ስንል በተደራጀ ሁኔታ በጋራ የሚኖሩ በርካታ ሰዎችን የሚያመለክት ሲሆን፣ ይህም በእዚያ ማኅበረሰብ ውስጥ የሚፈጸሙ የጋራ ተግባሮች እና ሥራዎች እንዴት መከናወን እንደ ሚገባቸው በመወሰን የሥራ ክፍፍል በማድረግ የተለያዩ ማኅበራዊ ውሳኔዎች የሚወሰኑበት፣ ሰዎች በጋራ የሚሳተፉበት፣ የሰዎች ስብስብ የሚለውን ያሰማል። በተጨማሪም በአንድ አገር ውስጥ ወይም በአጠቃላይ በሌላ አገራት የሚኖሩ  ሰዎች ሁሉ ማህበረሰብ ተብለው ሊጠሩ ይችላሉ። በአጠቃላይ ሰዎች በጋራ የሚኖሩበት ሥፍራ እንደ ሆነም ያሳያል (Cambridge online dictionary፡ 2018፡ retrieved 02/02/2018) ይህ ትርጉም ከካብሪጂ መዝገበ ቃል የተወሰደ ነው። በአጠቃላይ ማኅበረሳባዊ የሆኑ ጉዳዮችን የሚያመለክት ነው። በዚሁ መሰረት ቤተ ክርስቲያን ማህበራዊ አስተምህሮ በተከታታይ የምትሰጥበት ምክንያት ቀደም ሲል ለመጥቀስ እንደ ማከርኩት “የሰው ልጆችን ማዕከል” ባደርገ መልኩ ነው። የሰው ልጆች ባሉበት ማኅበረሰብ አለ፣ ማኅበረሰብ ባለበት ደግሞ እመንት አለ፣ እምነት ባለበት ቦታ ደግሞ ቤተ ክርስቲያን አለች፣ ቤተ ክርስቲያን እና ማኅበረሰብ ባሉበት ደግሞ መልካም እና ክፉ የሆኑ ነገሮች ይንጸባረቃሉ፣ ቤተ ክርስቲያን ስነ-ምግባራዊ የሆኑ እሴቶች ተጠብቀው እንዲሄዱ፣ ሰዎች በስላም እና በመከባበር እንዲኖሩ መልካም የሆኑ ነገሮችን የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ እሴቶችን በማበረታታት በአተቃራኒው ደግሞ የማኅበርሰቡን ሰላም የሚነሳውን ክፉ ነገሮችን በብርቱ ትቃወማለች፣ እንዳይስፋፉም በወንጌል እና ሰብዓዊ ምርሆች ላይ የተመሰረቱ አስተምህሮችን ትሰጣለች።

2.     Doctrine (በግርድፉ ሲተረጎም አስተምህሮ)፡ Doctrine የሚለው ቃል መስረቱን ያደርገው Docere በሚለው የላቲን ቋንቋ ላይ ሲሆን ይህም ማስተማር የሚለውን ትርጉሜ ይሰጠናል። ይህም የፖለቲካ፣ የፍልስፍና እና ሃይማኖታዊ አስተሳሰቦችን የተመለከቱ ጽንሰ-ሐሳቦችን ማስተማር የሚለውን ቃል ያሰማል። በተወሰነ የማኅበረሰብ ክፍል ተቀባይነት ያገኙ ፖሌቲካዊ እና ሐይማኖታዊ የሆኑ አስተምህሮችን፣ ወይም የእመንት አንቀጾችን፣ ወይም የአንድ ማኅበረሰብ ክፍል ርዕዮተ ዓለም ተቀብሎ ማስተማር የሚለውን ያሰማል። በእዚህ መሰረት ቤተ ክርስቲያናችን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ፣ በሕገ ቀኖና፣ በእመንት እውነቶች ላይ፣ በትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ፣ የቤተ ክርስቲያን አባቶች በጻፉዋቸው ሐዋሪያዊ መልእክቶች እና ቃለ ምዕዳን ላይ በመመስረት በአጠቃላይ ክርስትያናዊ እና ሰብዓዊ፣ እንዲሁም ማኅበራዊ የሆኑ እሴቶች ይከበሩ ዘንድ፣ ማኅበረሰቡ በሰላም እና በደስታ በአንድነት ይኖር ዘንድ ታስተምራለች።

3.     Church በሦስተኛ ደረጃ ቤተ ክርስቲያን የሚለውን ቃል እናገኛለን።  ቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል  “Ecclesia” (ሄክሌዚያ) ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን አጠቃላይ የሆነ ትርጉሙ አንድ አዓይነት እመነት ያላቸው የሰዎች ስብስብን ያመለክታል። በእዚህም መሰረት አንድ ዓይነት እመነት ያላቸው ሰዎች የሚመሰርቱት የጋራ ስብስብ ማለት ነው። በአጠቃላይ አንድ እመነት፣ ተስፋ እና ፍቅር በጋራ የሚጋሩ የማኅበረስብ ክፍሎችን ያመልክታል።

20 February 2019, 09:51