ፈልግ

የየካቲት 03/2011 ዓ.ም 4ኛው እለተ ሰንበት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ የየካቲት 03/2011 ዓ.ም 4ኛው እለተ ሰንበት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ 

የየካቲት 03/2011 ዓ.ም 4ኛው እለተ ሰንበት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ

ባለፈው እሁድ የነበረው የአምልኮ ሥነ-ስርዓት ኢየሱስ በናዝሬት ሙክራብ ውስጥ ተገኝቶ በነቢዩ ኢሳያስ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን አንድ ክፍል በማንበብ እና በመጨረሻም እነዚህ ቃላት "ዛሬ" ተፈጸሙ በማለት ተናግሮ እንደ ነበረ ማዳመጣችን ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ ኢየሱስ የጌታ መንፈስ በእርሱ ላይ እንዳረፈ፣ መንፈስ ቅዱስ እርሱን እንደ ቀደሰው እና የሰውን ዘር ለማዳን መንፈስ ቅዱስ እርሱን ወደ እዚህ ምድር እንደ ላከው አድርጎ ራሱን ሲያቀርብ እናያለን።

 “የኢየሱስ ደቀ-መዛሙርት ለመሆን የእመንት አመክንዮ (አስተዳደብ) መከተል ያስፈልጋል”

በእለቱ የተነበቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

1.     ት. ኤርሚያስ 1፡4-5, 17-19

2.    መዝ. 70

3.    1 ቆሮ 12፡31-13፡13

4.    ሉቃስ 4፡21-30

የእለቱ ቅዱስ ወንጌል

እርሱም “እነሆ ይህ አሁን ሲነበብ የሰማችሁት የመጽሐፍ ቃል ዛሬ ተፈጸመ” አላቸው። ስለእርሱም ሁሉም መልካም ይናገሩ ነበር። በሚናግረውም ውብ ቃል ተደንቀው “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን? ይሉ ነበር።

እርሱም እንዲህ አላቸው “’አንተ ሐኪም እስቲ ራስህን አድን’ የሚለውን ምሳሌ እንደ ምትጠቅሱብኝ እርግጠኛ ነኝ፣ እንዲሁም ‘በቅፍርናሆም አድርገሃል ሲባል የሰማነውን ሁሉ እዚህም በገዛ አገርህ አድርግ’ ትሉኛላችሁ አላቸው።  እውነት እላችኋለሁ፥ ነቢይ በገዛ አገሩ ከቶ አይከበርም።

ነገር ግን እውነት እላችኋለሁ፥ በኤልያስ ዘመን ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ሰማይ ተዘግቶ ሳለ በምድር ሁሉ ብርቱ ራብ በነበረ ጊዜ፥ በእስራኤል ብዙ መበለቶች ነበሩ፤  ኤልያስም በሲዶና አገር ወዳለች ወደ ሰራፕታ ወደ አንዲት መበለት እንጂ ከእነርሱ ወደ አንዲቱ አልተላከም።

በነቢዩ በኤልሳዕ ዘመንም በእስራኤል ብዙ ለምጻሞች ነበሩ፥ ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር ከእነርሱ አንድ ስንኳ አልነጻም። በምኵራብም የነበሩ ሁሉ ይህንን በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቆጡ። ተነሥተውም ኢየሱስን ጎትተው ከከተማ ውጭ አወጡት፥ ይጥሉትም ዘንድ ከተማቸው ተሠርታባት ወደ ነበረች ወደ ተራራው አፋፍ ወሰዱት፤  እርሱ ግን በመካከላቸው አልፎ ሄደ (ሉቃስ 4፡21-30)።

የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ

ባለፈው እሁድ የነበረው የአምልኮ ሥነ-ስርዓት ኢየሱስ በናዝሬት ሙክራብ ውስጥ ተገኝቶ በነቢዩ ኢሳያስ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን አንድ ክፍል በማንበብ እና በመጨረሻም እነዚህ ቃላት "ዛሬ" ተፈጸሙ በማለት ተናግሮ እንደ ነበረ ማዳመጣችን ይታወሳል። ኢየሱስ የጌታ መንፈስ በእርሱ ላይ እንዳረፈ፣ መንፈስ ቅዱስ እርሱን እንደ ቀደሰው እና የሰውን ዘር ለማዳን መንፈስ ቅዱስ እርሱን ወደ እዚህ ምድር እንደ ላከው አድርጎ ራሱን ሲያቀርብ እናያለን። የዛሬው ቅዱስ ወንጌል (ሉቃ. 4፡21-30) የዚያ ታሪክ ቀጣይ ክፍል ሲሆን የእነርሱ የአገራቸው ተወላጅ የሆነው "የዮሴፍ ልጅ" (ቁ .22) ራሱን የአብ መልእክተኛ የሆነው ክርስቶስ አድርጎ ሲያቀርብ የመለከቱታል።

ኢየሱስ አዕምሮንና ልብን ሰንጥቆ በመግባት ምን እንደ ሚያስቡ ማወቅ የሚያስችለውን ችሎታ ተጠቅሞ ወዲያው ወገኖቹ ምን እንደሚያስቡ መረዳት ችሎ ነበር። እርሱ ከእነርሱ አንዱ እንደሆነ አድርገው ስለቆጠሩት እርሱ በጎረቤት አገራት ውስጥ እንደ ፈጸመው ዓይነት ተዐምር በገዛ አገሩም ውስጥ ተዐምር እንዲፈጽም እንግዳ የሆነ “ጥያቄ” ማቅረባቸውን በግልጽ ተረድቶ ነበር። ይህ ጥያቄ ከእግዚአብሄር እቅድ/አመክንዮ ጋር የተጣጣመ ስላልነበረ ኢየሱስ ለዚህ ጥያቄ መልስ አልሰጠም ነበር፣ እግዚኣብሔር የሚፈልገው እመንት ነው፣ እነርሱ ደግሞ የፈለጉት ተዐምር ማየት ነበር፣ ምልክቶችን ማየት ፈልገው ነበር፣ እግዚኣብሔር ሁሉንም ሰው ማዳን ነው የሚፈልገው፣ እነርሱ ደግሞ የሚፈልጉት ለችግራቸው ጊዜያዊ የሆነ መፍትሄ የሚሰጥ መስህ ነበር የሚፈልጉት። በዚህም የተነሳ የእግዚአብሔርን አመክንዮ በሚገባ ለማብራራት በማሰብ እግዚኣብሔር ዕብራዊያን ያልሆኑ ወገኖችን፣ ነገር ግን በቃሉ የሚያምኑ ሰዎችን ሁሉ ለማዳን ወደ እዚህ ምድር  የላካቸውን የሁለት ታላላቅ ቀደምት ነቢያት የነበሩትን የኤሊያስን እና የኤልሳዕ ምሳሌ ኢየሱስ ሲያቀርብ እንመለከታለን።

ልባቸውን እና አእምሮዎቻቸውን በነጻ ለሚሰጠው ደኅንነት እና ይህም በነጻ የሚሰጠው ደህንነት ሁለንተናዊ እንደ ሆነ፣ በዚህም ምክንያት ልባቸውን በመክፈት እንዲረዱት ላቀረበላቸው ግብዣ የናዝሬት ነዋሪዎች የሰጡት ምላሽ አመጽ የተቀላቀለበት እና እንዲያውም ይህ አመጽ ኃይለኛ ወደ ሆነ ሁከት ተለውጦ መቆጣጠር ስላልቻሉ ተነስተው ኢየሱስን ለመጣል ይመቻቸው ዘንድ ከተማቸው ተሠርታበት ወደ ነበረው ወደ ተራራው አፋፍ ወሰዱት” (ሉቃስ 4፡29)ይለናል ቅዱስ ወንጌል። ቀደም ሲል እነርሱ ለእርሱ የነበራቸው አድናቆት ወደ ጠብ እና ወደ አመጽ ይቀየራል።

እናም ይህ የቅዱስ ወንጌል ክፍል የሚያሳየው የኢየሱስ የዚህ ምድር ይፋዊ አገልግሎት የተጀመረው በተቃውሞ እንደ ሆነ እና በተለይም ደግሞ ባልተለመደ ሁኔታ የእርሱ የሆኑ ወገኖች በእርሱ ላይ ባደረሱበት ከፍተኛ ተቃውሞ እና የመግደል ዛቻ እና ማስፈራሪያ በታከለበት መልኩ መጀመሩን ያሳያል። ኢየሱስ በአብ በሰጠው ተልዕኮ በመኖር እነዚህን ተቃውሞዎች፣ ስደትና የሽንፈት ስሜት መወጣት እንዳለበት በሚገባ ያውቃል። ልክ ትላንትና የነበረው እውነተኛ የነቢይነት ሚና እንደ ሚጠይቀው ሁሉ ዛሬም ቢሆን ዋጋ ለማስከፈል የቀረበ ጥያቄ ነው። ይሁን እንጂ እንዲህ ዓይነቱ ከፍተኛ ተቃውሞ ኢየሱስን ተስፋ አላስቆረጠም ነበር ወይም የነቢይነቱን ሥራ በመጉዳት ፍሬያማ እንዳይሆን አላደረገውም ነበር። በአባቱ ፍቅር በመታመን መንገዱን ይቀጥላል።

ዛሬም ቢሆን ለሕዝቡ እና ለዓለም መልእክቱን ለማዳረስ የሚችሉ ዳፋር እና ቆራጥ የሆኑ ነብያት እና የጌታ ደቀ-መዛሙርት ውስጥ ይህንን ወኔ ማየት ይፈልጋል። በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት "በመገፋፋት" ተስፋን ለማወጅ እና ድሆችን ለማዳን እንዲያገለግሉ የላካቸው ሰዎች፣ እምነትን እንጂ የተዓምራት አመክንዮ አይፈልጉም፣ ለሁሉም ሰዎች አገልግሎት ለመስጠት የተላኩ፣ ማንንም ሳያገሉ እና ያለምንም ልዩነት የሚያገለግሉ ሰዎች መሆንም ይኖርባቸዋል። በአጭሩ የአብ ፈቃድ ለመቀበል የተዘጋጁ እና ይህንንም ፈቃድ ለሌሎች በታማኝነት ለመመሥከር የተጠሩ ሰዎች ናቸው ማለት ነው።

በኢየሱስን የተልዕኮ መንፈስ በመታገዝ የእግዚአብሔር መንግሥት በተሳካ መልኩ መመስከረ የሚያስችለንን በሐዋሪያዊ ቅንዓት በመሞላት በዚህ መንፈስ እንድናድግ እና ወደ ፊት እንድንጓዝ ትረዳን ዘንድ ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎታችንን ማቅረብ ይኖርብናል።

ምንጭ፡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጥር 26/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ካደርጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ የተወሰደ።

09 February 2019, 10:20