ፈልግ

ብጹዕ ካ.ብርሃነ እየሱስ ብጹዕ ካ.ብርሃነ እየሱስ  

ብጹዕ ካ.ብርሃነእየሱስ የብሄራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን ሰብሳቢ ሆነው ተመረጡ

የኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብልክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ሊቃነ ጳጳስት ዘካቶሊካዊያን የኢትዮጲያ ካቶሊካዊያን ጳጳሳት ጉባሄ ፕሬዚዳንት የሆኑትን ብጽዕ ካርዲናል ብርሃነ የሱስን የብሄራዊ እርቅና ሰላም ኮሚሽን ሰብሳቢ አድርገው መሾማቸው ተገለጸ።

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የህግ ባለሙያ የሆነችውን የትነበርሽ ንጉሴን የኮሚሽኑ ምክትል ሰብሳቢ አድርገው መሾማቸው ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን በሃገሪቱ የተጀመረውን ሁለንተናዊ ለውጥ በማስቀጠል ለውጡን ተቋማዊ ለማድረግ እና አገራዊ አንድነትን ለመገንባት በርካታ ስራዎች እንደሚጠበቅበት የኢትዮጲያ ፌደራላዊ ሪፖብልክ ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል፡፡

14 February 2019, 15:21