ፈልግ

የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ምርጫ ሂደት የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ምርጫ ሂደት 

የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ብጹዓን ጳጳሳት የምርጫ ድምጽ ውጤት ግልጽነት ይጎለዋል ይላሉ።

ብጹዓን ጳጳሳቱ ቅሬታቸውን ያሰሙት የምርጫ ኮሚሽኑ የሦስቱን ግንባር ቀደም ተወዳዳሪዎ የድምጽ ውጤት ይፋ ባደረገበት ማግስት መሆኑ ታውቋል። የምርጫ ኮሚሽኑ ይፋ ያደረገው የድምጽ ውጤት ትክክለኛ አይደለም ለማለት የበቁትም ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በበኩሏ ያሰማራቻቸው፣ ከአንድ ሺህ በላይ የምርጫ ታዛቢዎች ከመላው የአገሪቱ ክፍሎች ከሰበሰቡ የምርጫ ድምጽ ቁጥር ጋር ስለማይመሳሰል ነው ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

እሁድ ታሕሳስ 21 ቀን 2011 ዓ. ም. በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ የተካሄደውን ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የድምጽ ውጤት ግልጽ አለመሆኑን የአገሪቱ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ተናግረዋል። ብጹዓን ጳጳሳቱ ቅሬታቸውን ያሰሙት የምርጫ ኮሚሽኑ የሦስቱን ግንባር ቀደም  ተወዳዳሪዎ የድምጽ ውጤት ይፋ ባደረገበት ማግስት መሆኑ ታውቋል። የምርጫ ኮሚሽኑ ይፋ ያደረገው የድምጽ ውጤት ትክክለኛ አይደለም ለማለት የበቁትም ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በበኩሏ ያሰማራቻቸው፣ ከአንድ ሺህ በላይ የምርጫ ታዛቢዎች ከመላው የአገሪቱ ክፍሎች ከሰበሰቡ የምርጫ ድምጽ ቁጥር ጋር ስለማይመሳሰል ነው ብለዋል። የምርጫ ኮሚሽኑ በበኩሉ በሰበሰበው የምርጫ ድምጽ ቆጠራ፣ ለምርጫ ከወጡት 48 ከመቶ ድምጽ ሰጭዎች መካከል ሰባት ሚሊዮን ድምጽ ያገኙትንና የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ መሪ ፈሊክስ ሺሰከዲን አሸናፊ ናቸው ማለቱ ታውቋል።     

አመጽ እንዳይነሳ አስጠነቀቁ፣

የምርጫ ኮሚሽኑ ይፋ ያደረጋቸው የድምጽ ቆጠራ ውጤት እንደ ጊዜያዊነት ተይዘው ቀጣይነት ያለው ንጽጽር ቢደረግም ምርጫው አገሪቱ ከቤልጄም ቅኝ ግዛት ነጻ ከወጣችበት እንደ ጎርጎሮርሳዊያኑ አቆጣጠር ከ1960 ዓ. ም. ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ ነጻና ሰላማዊ ምርጫ ነው ተብሏል። ይህም አገሪቱ የወሰደችበት ብቸኛ አማራጭ፣ ሕዝባዊ መጎልበትም የታየበት በመሆኑ በዚያች አገር ሌላ ሕዝባዊ አመጽ መቀስቀስ የለበትም በማለት የመንግሥታቱ መሪዎች አስተያየታቸውን ገልጸዋል። በሌላ ወገንም የአገሪቱ ብሔራዊ ሕገ-መንግሥት ፍርድ ቤት፣ የአገሪቱ አዲስ ፕሬዚደንት የሚሆኑት ቃለ መሃላ የሚያደርጉበትን እለት ጥር 10 ቀን 2011 ዓ. ም. እንደሆነ መወሰኑን ይፋ አድርጓል። የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት በበኩላቸው የምርጫ ድምጽ የመጨረሻ ውጤት በምርጫ ኮሚሽኑ፣ ሕጋዊ መስፈርቶችን የተከተለ፣ የብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽን መመሪያን የተከተለ እንዲሆን ጠይቀው ያም ሆነ ይህ ከምርጫ ኮሚሽኑ በኩል ይፋ የሚደረገውን የድምጽ ውጤት ሕዝቡ በትዕግስት መጠበቅ እንዳለበት አሳስበው፣ የኮንጎ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የኮንጎን ሕዝብ ዴሞክራሲዊ እሴቶችን ስታስጠብቅና ስታስከብር መቆየቷን ገልጸዋል።

የምርጫ ኮሚሽኑ የድምጽ ቆጠራ ውጤት፣

የአገሪቱ ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን ይፋ ያደረገው የድምጽ ቆጠራ ውጤት እንደሚያሳየው፣ የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪ የሆኑት ፈሊክስ ሺሰኬዲ ሰባት ሚሊዮን ድምጽ በማግኘት ቀዳሚነታቸውን ሲያረጋግጡ፣ 6, 3 ሚሊዮን ድምጽ ያገኙት ሌላው ተቃዋሚ የፖለቲካ መሪ  የሆኑት ማርቲን ፋዩሉ 6.3 ሚሊዮን ድምጽ ማግኘታቸውን፣ ከመንግሥት የፖለቲካ ፓርቲ ወገን በኩል የተወዳደሩት አማኑኤል ራማዛኒ 4.3 ድምጽ ማግኘታቸውን የምርጫ ኮሚሺኑ ግልጽ አድርጓል። ምርጫውን የፕሬዚደንት ዮሴፍ ካቢላ አጋር የሆኑት አማኑኤል ራማዛኒ እንዲያሸንፉ በድምጽ አሰጣጥ ላይ ማጭበርበር ይደረግበታል የሚል ስጋት ሰፍኖ እንደነበር የተነገረ ሲሆን፣ የፕሬዚደንት ዮሴፍ ካቢላ አባታት ሎሬት ደዚሬ ካቢላ፣ በተቀናቃኛቸው እጅ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር በ2001 ዓ. ም. መገደላቸው ይታወሳል።   

እንደ መንግስት ባለስልጣናት ገለጻ መሠረት ከዚህ በፊት በሃገሪቱ ሊደረጉ የታቀዱት ምርጫዎች እንዲራዘሙ የተደረገበት ምክንያት በአገሪቱ በተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝና በጸጥታ መጓደል ምክንያት መሆኑ ታውቋል። ከካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በኩል የሆኑት ክቡር አባ ንሾሌ፣ በሃገሪቱ ሊካሄዱ የታቀዱት በርካታ የምርጫ ቀናት ላልተወሰነ ጊዜ ሲራዘሙ መቆየታቸውን ገልጸው ለዚህም ምክንያቶቹ በሃገሪቱ የሚታየው የጸጥታ አለመረጋጋት፣ በምርጫ ምዝገባ ሥርዓት አለመደሰትና የኤሌክትሮኒክ የድምጽ መስጫ ማሽኖች ስምሪት በፈጠረው ቅሬታ እንደነበሩ አስረድተዋል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
11 January 2019, 15:09