ፈልግ

ክርስቲያኖች በሕንድ ክርስቲያኖች በሕንድ 

በዓለማችን ውስጥ ክርስቲያኖችን ጭቆናና አድልዎ እንደሚደርስባቸው ተነገረ።

በክርስቲያኖች እና በሌሎችም ዝቅተኛ ቁጥር ባላቸው የሐይማኖት ወገኖች ላይ የከፋ ስቃይን ያደርሳሉ

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በዓለማችን ውስጥ በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸሙትን የተለያዩ ስቃዮች፣ ጭቆናዎችና አድልዎችን የሚከታተል “ኦፐን ዶር”  የተባለ ዓለም አቀፍ ድርጅት በዓመታዊ ሪፖርቱ እንደገለጸው በዓለም ዙሪያ ከ245 ሚሊዮን በላይ ክርስቲያኖች ባለፈው ጎርጎሮርሳዊ 2018 ዓ. ም. ብቻ በአገራቸው ውስጥ የተለያዩ ስቃዮች እንደደረሰባቸው፣ 4305ቱ በእምነታቸው ምክንያት መገደላቸውን፣ 3150ዎቹ ደግሞ ተይዘው ለፍርድ መቅረባቸውንና መታሰራቸውንና በ1847 ቤተክርስቲያኖች ጥቃት እንደደረሰባቸው ድርጅቱ ገልጿል።

የሰሜን ኮሪያ መንግሥት የከፋ በደል ይፈጽማል፣

ዓለም አቀፉ ድርጅት በክርስቲያኖች ላይ የሚደርስ የስቃይና የግፍ መጠን በየዓመቱ በርሪፖር መልክ ይፋ ሲያደርግ የቆየ መሆኑ ሲታወቅ ያለፈው የጎርጎሮሳዊው 2018 ዓ. ም. 150 አገሮችን መርጦ በ50 አገሮች መካከል ባካሄደው ጥናት፣ በክርስቲያኖች ላይ ስቃይ፣ በእምነታቸው ምክንያት ብቻ ስቃይ፣ አድልዎ፣ ግድያና የመብት ጥሰት እንደሚደርስባቸው ገሃድ አድርጓል። በክርስቲያኖች ላይ እነዚህን የተለያዩ ጭቆናዎች የሚፈጽሙ አገሮችን በመለየት፣  ከእስያ 35 አገሮችን፣ ከአፍሪቃ 15 አገሮችን፣  ከላቲን አሜርካ ደግሞ 2 አገሮችን ጠቅሷል።

በክርስቲያኖች ላይ የከፋ ስቃይ የሚያደርሱ 11 አገሮች፣

በክርስቲያኖች እና በሌሎችም ዝቅተኛ ቁጥር ባላቸው የሐይማኖት ወገኖች ላይ የከፋ ስቃይ ያደርሳሉ ያሏቸውን 11 አገሮች፣ እነርሱም ሰሜን ኮሪያ፣ አፍጋኒስታን፣ ሶማሊያ፣ ሊቢያ፣ ፓክስታን፣ ሱዳን፣ ኤርትራ፣ የመን፣ ኢራን፣ ሕንድና ሶርያ መሆናቸውን ገልጿል።

አምባ ገነን፣ ብሔረተኝነትና እስላማዊ አክራሪነት፣

ድርጅቱ ከአምስት ዓመት በፊት ባወጣው ሪፖርቱ በክርስቲያኖች ላይ የከፋ ስቃይን በማድረስ የምትታወቅ ሰሜን ኮሪያ ብቻ እንደነበርች ያሳወቀ ቢሆንም ዘንድሮ ባወጣው ሪፖርት ነገር ግን ከኮሪያ በላይ አምባ ገነናዊ ስርዓትን የሚከተሉ፣ ብሔረተኝነትና እስላማዊ አክራሪነትን የሚከተሉ አገሮች እየታዩ በመምጣታቸው በዓለማችን ዙሪያ በክርስቲያኖች ላይ የሚደርስ ስቃይ ያንኑ ያህል መጨመሩን ገልጿል። በተጨማሪም በሕንድ የሃይማኖት አክራሪነት በሚታይበት በሕንዱ እና በቡዳ እምነቶች፣ በቻይናና በቪዬትናም ከኮሚኒስ ሥርዓት በፊትም ይሁን አሁን በክርስቲያኖች ላይ የሚደረግ አድልዎና የሚፈጸምባቸው በደል ከፍተኛ እንደሆነ፣ በደቡብ አሜርካ አገሮች በሜክስኮ እና በኮሎምቢያ ገጠራማው አካባቢ በክርስቲያኖች ላይ በደል እንደሚደርስብቸው ሪፖርቱ አመክቷል።   

17 January 2019, 17:18