ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ 34ኛው የወጣቶች ቀን ላይ የሚያደርጉትን ጉዞ በሳንታ ማሪያ ማጆሬ በጸሎት ጀመሩ። ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ 34ኛው የወጣቶች ቀን ላይ የሚያደርጉትን ጉዞ በሳንታ ማሪያ ማጆሬ በጸሎት ጀመሩ። 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ 34ኛው የወጣቶች ቀን ላይ የሚያደርጉትን ጉዞ በጸሎት ጀመሩ

ከጥር 14-19/2011 ዓ.ም “እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ” (ሉቃ 1፡38) በሚል መሪ ቃል 34ኛው ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን በፓናማ እንደሚከበር ይታወቃል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚሁ በ34ኛው የዓለም የወጣቶች ቀን ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ረፋዱ ላይ ወደ ፓናማ አቅንተዋል።
የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
እንደ ተለመደው ማነኛውንም ዓይነት ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ ከሮም ከተማ በሚወጡበት እና ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ቫቲካን በሚመለሱበት ወቅት በሮም ከተማ እምብርት ላይ በምትገኘው እና በአውሮፓ በማሪያም ስም ከተሰየሙት ባዚልካዎች መካከል በትልቅነቱ በሚታወቀው፣ በ18ኛው ክፍለ ዘመን ግንባታው እንደተጠናቀቀ በሚነገርለት በሳንታ ማሪያ ማጆሬ (Sanat Maria Maggiore) ባዚሊካ ተገኝተው ይህ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው የሰመረ ይሆን ዘንድ፣ በሚጎበኝዋቸው ሀገራት ውስጥም ሳይቀር ሰላም እና ፍቅር ይስፈን ዘንድ ጉዞዋቸውን ለማርያም በአደራ በመስጠት የእንደሚጀምሩ፣ በተመሳሳይ መልኩም ጉብኝታቸውን አጠናቀው በሚመለሱበት ወቅትም ሳይቀር በዚሁ ቤተ ክርስቲያን በመገኘት ለእግዚኣብሔር ምስጋና እንደሚያቀርቡ ይታወቃል።
በዚህም መስረት ቅዱስነታቸው በትላንትናው እለት ማለትም በጥር 14/2011 ዓ.ም አመሻሹ ላይ በዚሁ በሳንታ ማርያ ማጆሬ ባዚሊካ ተገኝተው ይህ 34ኛው ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን ላይ የሚያደርጉት ተሳትፎ የሰመረ እና ፍሬያማ ይሆን ዘንድ በእመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ጸሎታቸውን ወደ እግዚኣብሔር አምላክ አሳርገው ይህንን ጉዞዋቸውን ለማርያም በአደራ መስጠታቸውን ከስፍራው የደረሰ ዜና ያስረዳል።

 

Photogallery

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ 34ኛው የወጣቶች ቀን ላይ የሚያደርጉትን ጉዞ በሳንታ ማሪያ ማጆሬ በጸሎት ጀመሩ።
22 January 2019, 16:07