ፈልግ

የፓናማ ታሪክ በአጭሩ የፓናማ ታሪክ በአጭሩ 

የፓናማ አገረ ስብከት ታሪክ በአጭሩ

የአተቃላይ የፓናማ ሕዝብ ብዛት 4,198428 ሲሆን ዋና ከተማዋ ፓናማ በመባል ይታወቃል። በዚህች ዋና ከተማ 1,783,490 ነዋሪዎች የሚገኙባት ሲሆን በታላቁ የፓናማ ካናል (ሰው ሰራሽ የመርከብ መተላለፊያ መስመር) አቅራቢያ የተቆረቆረች ከተማ ስትሆን ይህቺ ከተማ የተቆረቆረችው እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ1519 በወቅቱ ከእፔን በመጡ የቅኝ ገዢዎች እንደ ነበረ ከታሪክ ለመረዳት ይቻላል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

 በወቅት በርካታ የላቲን አሜሪካ አገራትን በቅኝ ግዛታቸው ስር አድርገው የነበሩ ስፔናዊያን ከእነዚህ የላቲን አሜሪካ አገራት ዘረፈው የሚወስዱዋቸውን ወርቅ፣ ነሐስ እና የመሳሰሉ የከበሩ ማዕድናትን በመርከብ ለማመላለስ የባሕር ላይ ጉዞ በጣም ስለረዘመባቸው ይህንን ጉዞ ለማሳጠር በማሰብ 8ኪሜ. ርቀት ያለው አዲስ ሰው ሰራሽ የመርከብ መተላለፊያ መስመር መክፈታቸውን ከታሪክ መዝገብ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ፓናማ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1903 ዓ.ም ከስፔን ቅኝ ግዛት ወጥታ ነጻነቷን ከተጎናጸፈች በኋላ በአዲስ መልክ ከአሜሪካ ጋር በተፈራረመችው ውል መሰረት 81 ኪሜ ርዝመት ያለው አዲስ ሰው ሰራሽ የመርከብ መመላለሻ መስመር መገንባቱ ያታወሳል።

አብዛኛው የፓናማ ሕዝብ ከተለያዩ አገራት በተውጣጡ ስደተኞች የተገነባ ማኅበረሰብ ሲሆን ብሔር ብሔረሰባዊነት በከፍተኛ ሁኔታ የሚንጸባረቅባት፣ ከፍተኛ የሥራ እድል ያለባት፣ ኢኮኖሚዋም በጣም ጠንካራ የሚባል እና ውብ የሆነ የተፈጥሮ መስህብ ያላት አገር ናት ፓናማ።

የፓናማ አገረ ስብከት

የፓናማ አገረ ስብከት 113,275 ስኩዌር ካሬ ሜትር ስፋት ያለው እና በዚህ አገረ ስብከት ውስጥ ከሚኖሩት አጠቃላይ 2,031,700 ሕዝቦች መካከል 1,727,900 ሰዎች የካቶሊክ እምነት ተከታዮች እንደ ሆኑ ለቫቲካን ዜና አገልግሎት ከደረሰን መረጃ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን 94 ቁምስናዎች፣ 173 የአገረ ስብከት ካህናት፣71 ቋሚ ዲያቆናት፣ 65 የዐብይ ዘረዐ ክህነት ተማሪዎች፣ 256 ደናግል፣ 63 የትምህር መስጫ ተቋማት የሚገኙበት እና በተጠናቀቀው የጎርጎሮሳዊያኑ 2018 ዓ.ም ላይ ብቻ 14,775 ሰዎች ምስጢረ ጥምቀት መቀበላቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

23 January 2019, 16:32