ምዕመናን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሚሰጡት ክብር በኪነ-ጥበብ ሲገለጽ
የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሚሰጡትን ከፍተኛ ክብር እና እርሷ የክርስቲያኖች እናት እና አማላጅ እንደ ሆነች በማመን በታሪክ ሂደት ውስጥ ይህንን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያላቸውን ፍቅር እና አክብሮ በተለያየ መንገድ መግለጻቸው የሚታወቅ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ኪነ-ጥበባዊ በሆነ መልኩ የእመቤታችን ቅድስትድንግል ማርያም ምስል በመሳል እንደ ሆነ ይታወቃል።
“የማርያም ሕይወት ለቤተ ክርስቲያን ሕይወት ከፍተኛ የሆነ መሰረት የጣለ እና የቤተ ክርስቲያን ራስ የሆነውን ልጇን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለመገናኘት ድልድይ እና መንገድ በመሆን በማገልገል ላይ የምትገኘው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት” በማለት የተናገሩት በታሪክ ሂደት ውስጥ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ክብር የሚገልጹ የተለያዩ ቅብ ስዕሎችን የሚያመልክቱ የኪነ-ጥበብ ሥራዎችን በመገምገም “ማርያም በቅዱሳን ምስሎች ውስጥ” በሚል አርእስት መጽሐፍ ያሳተሙት የእኔታ አባ ቪንቼንሶ ፍራንችያ ናቸው።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን እና በአጠቃላይ ምድራዊ ሕይወቷን የሚያሳዩ በርካታ ቅዱሳን ምስሎች መኖራቸው የሚታወቅ ሲሆን ለምሳሌም በአንቶኒዮ ዳ ሜሲና የተሳለው መልአኩ ገብርኤል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ስያበሥራት የሚገልጽ የብስራተ ገብርኤል ቅዱስ የሆነ ምስል፣ አረማዊያን በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግር ሥር ሆኖው የሚያሳየው ቅዱስ የሆነ በሞዛይክ የተሠራ ምስል ደግሞ በሮቤርቶ ፉሮዞ ድንቅ የኪነ ጥበብ ሥራዎች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው። የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን መንፈሳዊ ሕይወት የምያመልክት ቅዱስ ምስል ማዞሊኖ በተባለ የጣሊያን የኪነ ጥበብ ሰው የተሳለ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ምስል ሲሆን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጅነቷ ጀምሮ ከቤተሰቦቿ አንስቶ እስከ መጨረሻው ጊዜ ድረስ ያለፈችባቸውን የትምህርት ጎዳናዎችን የሚያሳይ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ የሆነ ምስል ጃንባቲስታ ቴፖሎ በተባለ የኪነ ጥበብ ሰው መሳሉ ይታወቃል። እምቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በወላጆቿ በሀና እና በኢያቄም የእግዚኣብሔር ልጅ ማደሪያ ትሆን ዘንድ የተገባች እና የተቀደሰች ማደሪያ ትሆን ዘንድ ወደ ቤተ መቅደስ መወሰዱዋን የሚያሳየው ቅዱስ ምስል አንዴሬያ ማንቴኛ በተባለ የኪነ ጥበብ ሰው የተሳለ ቅዱስ ምስል እንደ ሆነ ይታወቃል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንደ ማንኛውም የሰው ልጅ በቤተልሄም በበረት ውስጥ ልጇን ስትወልድ የሚያሳየው ቅዱስ የሆነ ምስል ደግሞ ፍራንቸስካ ፒዬሮ የተሳለ ቅዱስ የሆነ ምስል ነው። ማርያም ልጇን ከወለደች በኋላ ጲላጦስ ሕጻኑን ልያስገድለው እንደ ሚፈልግ የሚገልጽ ሕልም ዮሴፍ ካለመ በኋላ ሕጻኑን ኢየሱስን ይዘወ ወደ ግብፅ ያደርጉትን የስደት ጉዞን የሚገልጸ ቅዱስ ምስል ደግም በታዋቂው የኪነ ጥበብ ሰው ሊዮናርዶ ዳቪንቺ የቀረበ ቅዱስ ምስል ነው። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ የሆኑ ምስሎች “ማርያም በቅዱሳን ምስሎች ውስጥ” በሚል አርእስት የእኔታ አባ ቪንቼንሶ ፍራንችያ ለንባብ ባበቁት መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱት ዋና ዋና የማርያም ቅዱስ ምስሎችን የምያመልክቱ ናቸው።