ፈልግ

በፓናማ የሚከበረው 34ኛው ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን በፓናማ የሚከበረው 34ኛው ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን  

በፓናማ የሚከበረው 34ኛው ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ

ከጥር 15-19/2011 ዓ.ም “እነሆኝ  የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ” (ሉቃ 1፡38) በሚል መሪ ቃል 34ኛው ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን በፓናማ እንደ ሚከበር ይታወቃል። በዚህ በፓናማ በሚካሄደው 34ኛው ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እንደ ሚገኙ ለመረዳት ተገኝተሉዋል። በዚህ መሰረት ለቅዱስነታቸው ከወጣው የጉዞ መረሃ ግብር ለመረዳት እንደ ተቻለው ቅዱስነታቸው ረቡዕ ጥር 15/2011 ዓ.ም በሮም ከተማ ከሚገኘው እና በሊዮናርዶ ዳቪንቺ ስም ከተሰየመው ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ተነስተው በፓናማ በሚገኘው ቶኩሜን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደ ሚደርሱ ከቅድስት መንበር የህትመት እና የዜና ክፍል ካወጣው መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መበራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የዚህ በፓናማ በሚከበረው 34ኛው ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን የዝግጅት አስተባባሪ ኮሚቴ የሆኑት የፓናማ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጆዜ ዶሚንጎ በሮም በኅዳር 03/2011 ዓ.ም በሰጡት መገለጫ እንደ ገለጹት ይህ 34ኛው ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን “ታላቅ የእመንት በዓል” እንደ ሚሆን ያላቸውን ተስፋ መግለጻቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በዚህ ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን ውይይት ከሚደረግባቸው ሐሳቦች መካከል የስደተኞች ጉዳይ ቀዳሚውን ስፍራ እንደ ሚይዝ ጨምረው ገለጸዋል። በዚህ 34ኛው ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን ላይ ከአምስት አህጉራት የተውጣጡ ከ200 ሺ በላይ ወጣቶች በዓሉን ለመካፈል የምያስችላቸውን ሕጋዊ የሆነ መስፈርት ማሟላታቸውን ጨምረው ገልጸዋል። እነዚህን 200 ሺ ወጣቶች ለማስተናገድ ይቻል ዘንድ ከብራዚል፣ ከኮስታሪካ፣ ከፈረንሳይ እና ከፖላንድ የተውጣጡ 37ሺ የበጎ ፈቃደኞች ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ጨምረው የገለጹ ሲሆን እነዚህ በጎ ፈቃደኞች ከ200 ሺ በላይ የዝግጅቱ ተካፋይ ወጣቶችን በተገቢው ሁኔታ ለማስተናገድ ይቻል ዘንድ የተቻላቸውን አስተዋጾ እንደ ሚያደርጉም ጭመሮ ተገልጹዋል። 

ሐሙስ ጥር 16/2011 ዓ.ም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በፓናማ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት በመገኘት ከሀገሪቷ ርዕሰ ብሔር እና ከምንግሥት ባለስልጣናት ጋር ይገናኛሉ። ከዚያ በመቀጠል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከተለያዩ ከመካከለኛው አሜሪካ ከተውጣጡ ብጹዕን ጳጳሳት ጋር ይገናኛሉ።

ዐርብ ጥር 17/2011 ዓ.ም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በፓናማ የሚገኘውን የወጣቶች መዓከል ይጎበኛሉ፣ በዚያ የሚካሄደው የሚስጢረ ንስሐ ስነ-ስረዓት ላይ ይሳተፋሉ። በተመሳሳይ ቀን ከሰዓት በኋላ ላይ ወጣቶች በፓናማ ከተማ በሚያደርጉት የወጣቶች የመስቀል መንገድ ጸሎት ላይ ቅዱስነታቸው እንደ ሚሳተፉ ከወጣው የጉዞ መረሃ ግብር ለመረዳት ተችሉዋል።

ቅዳሜ ጥር 18/2011 ዓ.ም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በፓናማ ከተማ በሚገኘው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ባዚሊካ ውስጥ መስዋዕተ ቅዳሴ ያሳርጋሉ። ከመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት በመቀጠል ቅዱስነታቸው ከወጣቶች ጋር የምሳ ግብዣ ይቋደሳሉ። አመሻሹ ላይ ቅዱስነታቸው ወጣቶች ባዘጋጁት የዋዜማ የጸሎት ፕሮግራም ላይ ይገኛሉ፣ ከወጣቶች ጋር በጋራ ጸሎት ያደርሳሉ።

እሁድ ጥር 19/2011 ዓ.ም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በፓናማ ከተማ በርካታ ወጣቶች በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴን ያሳርጋሉ። በመቀጠል ደጉ ሳምራዊ በመባል የሚታወቀውን ተቋም ከወጣቶች ጋር በመሆን ይጎበኛሉ። ከዚያም አመሻሹ ላይ ቅዱስነታቸው ወደ ሮም እንደ ሚመለሱ ለዚህ ለ34ኛው ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን ከወጣው የጉዞ መረሃ ግብር ለመረዳት ተችሉዋል።

13 December 2018, 16:06