ፈልግ

ሲስተር ስንቅነሽ  ሲስተር ስንቅነሽ  

ሲስተር ስንቅነሽ ላበረከቱት በጎ ተግባር ተሸላሚ ሆኑ

እግዚአብሔር ያክብርልን አረጅም እድሜና ጤና ይስጥዎ ሲ/ር ስንቅነሽ ገብረማርያም በህይወት ዘመን የላቀ የሙያ አገልግሎት ተሸላሚ ሲስተር ስንቅነሽ ገብረማርያም ለረጅም ዓመታት በአለርት ሆስፒታል ሁለገብ አገልግሎት በመስጠት ይታወቃሉ፡፡ ከዚያ በፊት እኤአ ከ1973 እስከ 1977 በቢሲዲሞ ሆስፒታል የስጋ ደዌ ህክምና ሲሰጡ የቆዩ ናቸው፡፡

ሲስተር ስንቅነሽ እኤአ ከ1983 እስከ 2000 በአለርት ሆስፒታል በሶሻል ምክር ሙያ በማገልገል በስጋ ደዌ ታካሚዎች ላይ የነበረው መገለል እንዲቀንስ እንዲሁም ታካሚዎች ግንዛቤ ኖሯቸው ለህክምና 
እንዲበረቱ በማድረግ ረገድ ውጤታማ ስራ ሰርተዋል፡፡ በሆስፒታሉ፣ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎችና ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በመተባበር ተግባር ተኮር ስልጠና ህብረተሰቡ እንዲያገኝ በማድረግም ይታወቃሉ፡፡

ሲስተር ስንቅነሽ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን መድህን ማህበራዊ አገልግሎት ማዕከልን በማቋቋም ባለፉት 30 ዓመታት ከተለያዩ ሆስፒታሎች ህክምናቸውን ከጨረሱ በኋላ ወደ ማህበራዊ ህይወትና ወደ ማህበረሰቡ መቀላቀሉ ያልቻሉ ታካሚዎችን በማቋቋምና ስልጠና እንዲያገኙ በማድረግም የሰሩት ስራ ተጠቃሽ ነው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከ500 በላይ የሚሆኑ የስጋ ደዌ ተጠቂ ቤተሰብ ልጆችን ትምህርት እንዲማሩ በመደገፍ፣ የአዕምሮ ዝግመት ያለባቸውን ሰዎች የተለያዩ የሙያ ስልጠና አግኝተው ራሳቸውን እንዲችሉ በማድረግም ስማቸው በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡

የአለርት አህሪ የምርምር አድቫይዘሪ ኮሚቴ ሰብሳቢና አባል በመሆን ከአስር ዓመት በላይ በማገልገልና ችግር ፈቺ የሆኑ ምርምርና ጥናቶች እንዲተገበሩ ያደረጉ፣ የአለርት ማዕከል አሰራር ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን የሚያስችሉ የተለያዩ ማህበራዊ ተግባራትን በመምራትና በመተግበርም ይታወቃሉ፡፡ ለዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ማዘርቴሬዛ ያገኙትን የዲኤም ዳቱም አዋርድ / DM Datum Award/ እኤአ በ2010 ሽልማት ከእንግሊዝ ሀገር የቀበሉ ታታራና ትሁት ሰው ናቸው፡፡

ምንጭ፡- Ministry of Health,Ethiopia

13 November 2018, 15:01